Get Mystery Box with random crypto!

ሁሉንም ዓይነት የጥበብ ስራዎችን በቀላሉ ማግኘት የሚያስችል “ሰዋሰው” የተሰኘ መተግበሪያ ይፋ ሆነ | ሰሌዳ | Seleda

ሁሉንም ዓይነት የጥበብ ስራዎችን በቀላሉ ማግኘት የሚያስችል “ሰዋሰው” የተሰኘ መተግበሪያ ይፋ ሆነ።

በቱ ኤፍ ካፒታል ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማህበር የተመሰረተው መተግበሪያው የተለያዩ የጥበብ ስራዎችን በክፍያም ሆነ ያለክፍያ አማራጮች መከታተል የሚያስችል ነው ተብሏል። ወደ 80 ገደማ የሚሆኑ አንጋፋና ወጣት ድምጻውያን ከአንድ ሺህ በላይ ሙዚቃዎችን ብሎም በመቶዎች የሚቆጠሩ የኪነጥበብ የፈጠራ ውጤቶችን ለማዘጋጀት ከድርጅቱ ጋር ውል አስረዋል።

የስነ ጥበብ ሰዎች ከቅጂ እና ተዛማጅ መብቶች ጋር በተያያዘ የሚገጥማቸውን ችግር ይቀርፋል የተባለው ይህ መተግበሪያ ለባለመብቶች የሮያሊቲ ክፍያ በአግባቡ የሚከፈልበት ስርዓት እንዳለውም ተገልጿል። ቱ ኤፍ ካፒታል በይፋ ካስመረቀው የሰዋሰው መልቲሚዲያ መተግበሪያ በተጨማሪ የፕሮዲዩሰርነት ስራ እንደሚሰራም የገለጸ ሲሆን በዚህም ተሰጥኦ ላላቸው የጥበብ ሰዎች ቅድመ ክፍያ በመክፈልና ወጪያቸውን በመሸፈን ሙዚቃቸውን እንዲያሳትሙ እንደሚያደርግ ሰምተናል ።