Get Mystery Box with random crypto!

ከአዲስ አበባ ወደ ኦሮሚያ ክልል የተካለሉ አካባቢዎች የቤት ግብይት አገልግሎት ተቋረጠ። የአዲስ | ሰሌዳ | Seleda

ከአዲስ አበባ ወደ ኦሮሚያ ክልል የተካለሉ አካባቢዎች የቤት ግብይት አገልግሎት ተቋረጠ

የአዲስ አበባ እና ኦሮሚያ ክልል ወሰን መካለሉን ተከትሎ ከአዲስ አበባ ወደ ኦሮሚያ ክልል የተካለሉ አካባቢዎች ላይ የቤት ግብይት እና እግድ አገልግሎት መቋረጡን አዲስ ማለዳ ዘግባለች። በተካለሉት አካባቢዎች የመንግሥት መሥሪያ ቤቶች፤ የቤት ሽያጭ፣ ግዢ፣ ሥም ዝውውርና እግድ አገልግሎት ከተቋረጠ በኋላ በአካባቢዎቹ የቤት ግብይት ቆሟል።

ከአዲስ አበባ ወደ ኦሮሚያ ክልል የተካለሉ አካባቢዎች ፋይል የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር እና ኦሮሚያ ክልል ርክክብ ማድረጋቸውም ተሰምቷል። ምንም እንኳን የፋይል ርክክቡ የተከናወነ ቢሆንም፣ የኦሮሚያ ክልል አገልግሎት መስጠት አልጀመረም። ክልሉ ከአዲስ አበባ ከተማ ለተረከባቸው አካባቢዎች መቼ አገልግሎት መስጠት እንደሚጀምር እና አገልግሎቱ የት እንደሚሰጥ በውል የታወቀ ነገር የለም።

via - አዲስ ማለዳ