Get Mystery Box with random crypto!

ፋይናንስ ደህንነት አገልግሎት ከወንጀል ተግባር ጋር ግንኙነት ያላቸው የባንክ ሂሳቦችን አገደ:: | ሰሌዳ | Seleda

ፋይናንስ ደህንነት አገልግሎት ከወንጀል ተግባር ጋር ግንኙነት ያላቸው የባንክ ሂሳቦችን አገደ::

ከህገ-ወጥ የውጭ አገራት ገንዘብ ማስተላለፍ ወንጀሎች ጋር ግንኙነት እንዳላቸው የተጠረጠሩ 665 የባንክ ሂሳቦች የታገዱት ህጋዊ የውጭ አገራት ገንዘብ ማስተላለፍ ፈቃድ ሳይኖራቸው፣ በህገ-ወጥ መንገድ በአገር ውስጥ እና በውጭ አገራት ከሉ አካላት ጋር ትስስር በመፍጠር በህገ-ወጥ መንገድ የገንዘብ ማስተላለፍ ተግባር ላይ ተሰማርተው የተገኙ መሆናቸውን የኢፌዲሪ የፋይናንስ ደህንነት አገልግሎት አስታዉቋል፡፡

የተለያዩ የወንጀል ድርጊቶችን በመፈፀም የተገኘን ሃብት ከህጋዊ ምንጭና በህጋዊ መንገድ የተገኘ በማስመሰል የመጠቀም ወንጀሎች አፈፃፀም በየጊዜው እየተቀያየረ ያለ ወንጀል ከመሆኑም ባሻገር፣ ከወንጀል ድርጊቶቹ የተገኘው ሃብት ሽብርተኝነትን በገንዘብ የመርዳት ወንጀል መፈፀሚያ ጭምር የሚውል በመሆኑ የመከላከልና መቆጣጠር ስራው በተጠናከረ አግባብ በመከናወን ላይ ነዉ ብሏል አገልግሎቱ።