Get Mystery Box with random crypto!

በአዲስ አበባ ከ18 ሺህ በላይ የንግድ ተቋማት ላይ እርምጃ ተወሰደ። በመዲናዋ የዋጋ ንረቱን በ | ሰሌዳ | Seleda

በአዲስ አበባ ከ18 ሺህ በላይ የንግድ ተቋማት ላይ እርምጃ ተወሰደ።

በመዲናዋ የዋጋ ንረቱን በማባባስና የንግድ ህጎችን በመጣስ ከ 18 ሺህ በላይ የንግድ ተቋማት ላይ ህጋዊና አስተዳዳራዊ እርምጃ መወሰዱን የከተማዋ ንግድ ቢሮ አሳውቋል። ቢሮው ከ95 ሺህ በላይ በሚሆኑ ተቋማት ላይ ክትትል አድርጎ ነው ከ18ሺህ በላይ ተቋማት ላይ እርምጃ የወሰደው። ከአስተዳደራዊ እርምጃው ባሻገር በ182 ተቋማት ላይ ህጋዊ እርምጃ ለመውሰድ ክስ መስርቷል።

ቢሮው የዋጋ ንረቱን ለማረጋጋት ከአንድ ቢሊዮን ብር በላይ ለህብረት ስራ ማህበራት የስራ እንቅስቃሴ መመደቡን የገለፀ ሲሆን የሸማቾች ህብረት ስራ ማህበራትን ቀጥታ ከአርሶ አደሮች ጋር በማገናኘት ምርት በብዛት ወደ አዲስ አበባ እንዲገባ መደረጉን ገልጿል። ከዚህም በተጨማሪ በከተማዋ 97 የእሁድ ገበያዎችን በማቋቋም ህብረተሰቡ በተመጣጣኝ ዋጋ እንዲገበያይ ማድረጉን አሳውቋል።

via - Reporter