Get Mystery Box with random crypto!

በቅጣት ምክንያት የተሽከርካሪዎችን ሰሌዳ የመፍታት እርምጃ እንዲቆም ጥያቄ ቀረበ። የአዲስ አበባ | ሰሌዳ | Seleda

በቅጣት ምክንያት የተሽከርካሪዎችን ሰሌዳ የመፍታት እርምጃ እንዲቆም ጥያቄ ቀረበ።

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የመንገድ ደህንነት ምክር ቤት የተጠናቀቀው የበጀት አመት እቅድ አፈፃፀምን አስመልክቶ ከሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት ጋር ባደረገው ዉይይት ወቅት የትራፊክ ደንብ በተላለፉ አሽከርካሪዎች ላይ ለቅጣት በሚል ምክንያት የተሽከርካሪዎችን ሰሌዳ የመፍታት እርምጃ ህግን ካለማስከበሩም ባሻገር ለሀገር ሀብት ብክለት ምክንያት በመሆኑ እርምጃው ሊጤንና ሊቆም እንደሚገባ ጥያቄ ቀርቧል።

በመድረኩ እርምጃው ለሌላ አደጋ ስለሚዳርግ ሁሉም ባለድርሻ አካላት መፍትሔ ሊያበጁለት ይገባል የተባለ ሲሆን በተጨማሪም አቅጣጫ ለመያዝ ብቻ ተብሎ ተቆርጠው የሚወጡ ሰሌዳዎች በርካታ በመሆናቸው በዚህ መሀል የሀገር ሀብት እንደሚባክን ተጠቁሟል። አገሪቱ በተጠናቀቀው በጀት አመት በግብአት እጥረት ምክንያት ሰሌዳ ለማምረት ተቸግራ እንደነበርም በመድረኩ ተነስቷል።

via - Reporter