Get Mystery Box with random crypto!

ሳፋሪኮም 5ጂ ለማስጀመር ቢያንስ እስከ ሶስት አመት እንደሚጠብቅ አስታወቀ። ኩባንያው እስካሁን | ሰሌዳ | Seleda

ሳፋሪኮም 5ጂ ለማስጀመር ቢያንስ እስከ ሶስት አመት እንደሚጠብቅ አስታወቀ።

ኩባንያው እስካሁን አገልግሎቱን በጀመረባቸው አካባቢዎች ያቀረበው 4ጂ ድረስ ያለውን የኢንተርኔት አገልግሎት ሲሆን የ5ጂ አገልግሎት ለማስጀመር የሚያስችለውን ስፔክትረም ምደባ ለማግኘት ለኢትዮጵያ ኮሚኒኬሽን ባለስልጣን ጥያቄ ማቅረቡ ተሰምቷል። ባለስልጣኑ ጥያቄውን በማየት ላይ እንደሚገኝና ማብራሪያ የሚፈልጉ ጉዳዮች ላይ ጥያቄ ማቅረቡን ገልጿል።

እንደ ኩባንያው ስራ አስፈፃሚ አንዋር ሶላ ገለፃ ሳፋሪኮም 5ጂ የሚያስጀምርበት ጊዜ የሚወሰነው በሀገሪቱ ውስጥ ምን ያህል 5ጂ የሚያስጠቅሙ መሳሪያዎች አሉ በሚለው ላይ ተመስርቶ ነው። 5ጂ የሚጠቀሙ ሰዎች ቁጥር አነስተኛ በመሆኑ 5ጂ የሚያስጠቅሙ መሳሪያዎች በብዛት እስከሚገኝ ድረስ እንደሚጠብቅ ገልፀዋል።

via - Reporter