Get Mystery Box with random crypto!

ኢትዮጵያ ለጎረቤት ሀገራት ከሸጠችው የኤሌክትሪክ ሃይል ከ13 ሚሊየን ዶላር በላይ ገቢ ማግኘቷ ተገ | ሰሌዳ | Seleda

ኢትዮጵያ ለጎረቤት ሀገራት ከሸጠችው የኤሌክትሪክ ሃይል ከ13 ሚሊየን ዶላር በላይ ገቢ ማግኘቷ ተገለፀ።

የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ባለፉት ሁለት ወራት ለሱዳን እና ጂቡቲ 232 ነጥብ 76 ሚሊየን ኪሎ ዋት ሰዓት የኤሌክትሪክ ኃይል በማቅረብ የ13 ነጥብ 04 ሚሊየን የአሜሪካ ዶላር ሽያጭ በማከናወን የዕቅዱን 70 በመቶ ማሳካት መቻሉን አስታውቋል፡፡ ምንም እንኳን ለኹለቱ አገራት የተከናወነው ሽያጭ በጥቅል ሲታይ ከዕቅዱ በታች ቢሆንም፤ ከጅቡቲ የተገኘው ገቢ ግን ከዕቅዱ የ15 ነጥብ 38 በመቶ ብልጫ ያሳየ እንደነበር ተገልጿል፡፡
 
ለሱዳን 112 ነጥብ 36 ሚሊየን ኪሎ ዋት ሰዓት ኃይል በማቅረብ የ5 ነጥብ 61 ሚሊየን ዶላር የተገኘ ሲሆን ለጂቡቲ ደግሞ 120 ነጥብ 39 ሚሊየን ኪሎ ዋት ሰዓት የኤሌክትሪክ ኃይል በማቅረብ የ7 ነጥብ 42 ሚሊየን ዶላር መገኘቱ ተጠቁሟል፡፡ በሁለቱ ወራት ለጎረቤት ሀገራት የኤሌክትሪክ ኃይል በማቅረብ ከተገኘው ገቢ በተጨማሪ ከሀገር ውስጥ የኃይል ሽያጭና ከፋይበር ኦፕቲክስ ኪራይ ከ2 ነጥብ 74 ቢሊየን ብር በላይ መገኘቱ ተጠቁሟል፡፡

via - ENA