Get Mystery Box with random crypto!

ግዙፉ የብስኩት ፋብሪካ ቱ ብራዘርስ ፉድ ኮምፕሌክስ በግብዓት እጥረት ምክንያት ስጋት ላይ መሆኑን | ሰሌዳ | Seleda

ግዙፉ የብስኩት ፋብሪካ ቱ ብራዘርስ ፉድ ኮምፕሌክስ በግብዓት እጥረት ምክንያት ስጋት ላይ መሆኑን አስታወቀ።

የፋብሪካው የፕሮዳክሽን ኃላፊ አቶ አደም ከማል የፋብሪካው በርካታ የማምረቻ መሳሪያ ጥሬ እቃዎች ከውጭ እንደሚገቡ ገልፀው የውጭ ምንዛሬ እጥረቱ ሥራውን በአግባቡ እንዳይሰራ ከፍተኛ ተግዳሮት እንደሆነበትና ይህንንም በተቻለ መጠን የሚመለከተው የመንግሥት አካል ትኩረት እንዲሰጠው መጠየቃቸውን ለኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት ተናግረዋል።

እንደ ሀላፊው ገለፃ ፋብሪካው አሁን ላይ 34 የብስኩት አይነቶችን ለአገር ውስጥ ገበያ ለማምረት የሚያስችል ማሽነሪዎች ቢኖሩትም፤ በቅርቡም ከኢትዮጵያ አልፎ የብስኩት ምርቱን ወደ ጎረቤት ሀገራት ኤክስፖርት ለማድረግ ለያዘው እቅድ የተፈጠረው የዶላር ችግር ከውጭ የሚያስፈልጉ ጥሬ ዕቃዎችን እንዳያስገባ ከፍተኛ የሆነ ተግዳሮት ሆኖበታል ብለዋል።

በኢንዱስትሪ ሚኒስቴር የወጪ ምርቶች መሪ ሥራ አስፈጻሚ አቶ ዘሪሁን አበበ በበኩላቸው፤ የውጭ ምንዛሬ ፍላጎቱ ከአጠቃላይ አገራዊ ጉዳይ ጋር ተያይዞ የመጣ ተጽእኖ መሆኑን ተናግረው ከውጭ ምንዛሬ ፍላጎት ጋር ተያይዞ ኤክስፖርት የሚያደርጉ እንዱስትሪዎችና ስትራቴጂ ተኪ ኢንዱስትሪዎች እንደ የሁኔታቸው እየታየ ቅድሚያ የሚያገኙበት ሁኔታ ለማመቻቸት ውይይት መደረጉንና አቅጣጫ እስኪሰጥበት እየተጠበቀ መሆኑን አስታውቀዋል።

via - ENA