Get Mystery Box with random crypto!

መንግስት የገንዘብና የበጀት ፖሊሲውን ለመከለስ ውይይት እያደረገ መሆኑን ተነገረ። መንግስት የገ | ሰሌዳ | Seleda

መንግስት የገንዘብና የበጀት ፖሊሲውን ለመከለስ ውይይት እያደረገ መሆኑን ተነገረ።

መንግስት የገንዘብ፣ የበጀት እና ሌሎች ዘርፎችን የሚነኩ ፖሊሲዎችን ክለሳ በማድረግ ለመተግበር ዝግጅት እያደረገ መሆኑን ዋዜማ ዘግባለች። በቁጥጥር ስር ሊውል ያልቻለው የዋጋ ንረት ፣ የውጭ ምንዛሬ እጥረት ፣ እንዲሁም እጥረቱን ተከትሎ በባንክ እና በጥቁር ገበያ መካከል የተፈጠረውን የተጋነነ የዋጋ ልዩነት ምክንያት ሆኖ በቅርቡ አዲስ የፖሊሲ ማሻሻያዎች እንደሚኖሩም ዘገባው ጠቅሷል።።

መንግስት የገንዘብ ፖሊሲን አሁን የሚያሻሽል ከሆነ በአንድ ዓመት ለሶስተኛ ጊዜ ይሆናል። ከዚህ ቀደም የኢትዮጵያ ብሄራዊ ባንክ የዋጋ መረጋጋት ያመጡልኛል ያላቸውን ሁለት የገንዘብ ፖሊሲ ማሻሻያዎችን ቢተገብርም የዋጋ ንረቱ የመቀነስ አዝማሚያን አላሳየም። በተቃራኒው ማሻሻያዎቹ የዋጋ ንረቱን ያባብሳሉ የሚሉ ትችቶች በኢኮኖሚ ባለሙያዎች ሲቀርቡበትም ቆይቷል።

ባለፈው አመት በጥቁር ገበያው የአንድ አሜሪካ ዶላር ዋጋ 65 ብር ደርሶ ከባንክ ምንዛሬ ጋር የ20 ብር ልዩነትን ማሳየቱን ተከትሎ መንግስት የኢኮኖሚ አሻጥር ውጤት ነው በሚል የተለያዩ እርምጃዎችን መውሰዱ ይታወሳል።  በዚህም የቤት ሽያጭን እንዲሁም የባንክ ብድርን ወዲያው ነበር ያገደው።

እርምጀውን ተከትሎም የጥቁር ገበያው ዋጋ ወርዶ ከባንክ ጋር ያለው ልዩነት ጠቦ ቢቆይም በሂደት የተቀመጡ እግዶች ሲነሱ የሰሜኑም ጦርነት ለሶስተኛ ጊዜ ሲያገረሽ የውጭ ምንዛሬ መዛነፎች እንደገና አገርሽተዋል። አሁን መንግስት እያደረገ ያለውን ምክክር ሲያጠቃልል ከፖሊሲ እርምጃዎችና ከገንዘብ ባለፈ የበጀት እና ሌሎች ማእቀፎችን አካቶ ተግባራዊ እንደሚሆን ይጠበቃል ።

via - wazema