ፓኪስታን በታሪኳ አይታው የማታውቀው የጎርፍ መጥለቅለቅ አጋጥሟታል ። የጎርፉ አደጋ አብዛኛውን የሀገሪቱ ክፍል ያካለለ ሲሆን በሚሊዮን የሚቆጠሩ ህዝቦችን መውጫ መግቢያ አሳጥቶ የበርካቶችን ህይወት እየቀጠፈ ነው ።
እስካሁን ከ 1,100 በላይ ፓኪስታናዊያን ህይወታቸው አልፏል ። ከ ግማሽ ሚሊዮን ህዝብ በላይ ተፈናቅሏል ። በርካታ ከተሞች ከነ ህንፃዎቻቼው በጎርፉ ሰጥመዋል ።
ይህ ከባድ ዝናብ ያስከተለው ጎርፍ በፓኪስታን 100 ኪሎሜትር ሀይቅ መፍጠር ችሏል ። ጎርፉን ለማምለጥ ወላጆች ህፃናት ልጆቻቼውን ልጆች አዛውንት ወላጆቻቼውን ይዘው ሲታገሉ ሲታይ በጣም ያሳዝናል ።
ለህዝቧ በአደጋ ጊዜ በፍጥነት መድረስ የሚያስችል አቅም ያልገነባችው ፓኪስታን ለአለም አቀፉ ማህበረሰብ የእርዳታ ጥሪ አቅርባለች ።
የፓኪስታን ወንድሞቻችንን አላህ ከዚህ መከራ በቃችሁ ይበላቸው !
#Seid_Mohammed_Alhabeshiy
ቴሌግራም
t.me/Seidsocial