Get Mystery Box with random crypto!

አልጀሪያ የ 1.5 ሚሊዮን ሰማእታት ሀገር ነች ። ሀገር ካለደምና አጥንት አይሰራምና አልጀሪያ ነፃ | Seid Social

አልጀሪያ የ 1.5 ሚሊዮን ሰማእታት ሀገር ነች ። ሀገር ካለደምና አጥንት አይሰራምና አልጀሪያ ነፃነቷን ያስከበሩላት ወራሪና ባንዳዎቿን የቀበሩላት በርካታ ሚሊዮናት ጀግኖችን የታደለች ሀገር ናት ። በዚህም ከኢትዮጵያ ጋር ያመሳስላታል ።
ታዲያ መሪያችን ዶክተር አብይ አህመድ ለነዚያ ሰማእታት መታሰቢያ የአበባ ጉንጉን ማስቀመጣቸው አጋጣሚውም ትርጉሙም ትልቅ ነው ።

አልጀሪያ ሚሊዮን ጀግኖቿን ስትገብር የተዋጋቺው ከወራሪዋ ፈረንሳይ ጋር ብቻ አልነበረም ይልቁንስ ከማህፀኗ ከወጡ ተላላኪ ባን*ዳዎችም ጋር ጭምር እንጅ ። እናም ዞሮ ዞሮ አልጀሪያ ስታሸነፍ ስለርሷ የሞቱላት ስለርሷም የኖሩላት ዘልአለም በክብር ሲወሱ ይኖራሉ ።

እነዚያ ጥቅመኛ ባንዳ*ዎቿ ግን እንኳንስ አልጀሪያ ላኪያቸው ፈረንሳይ እንኳ ተፀይፋቸው የውርደት ሞትን ሞተዋል ።

ድሮስ ለባን*ዳ ከውርደት ያለፈ ምን ክብር ኖሮት ያውቅና !!

#Seid_Mohammed_Alhabeshiy

ቴሌግራም
t.me/Seidsocial