Get Mystery Box with random crypto!

#እግዚአብሔርን_እንዲህ_በለው..! አንተን ሊያሳስብህ የሚገባው ነገር ከእግዚአብሔር ጋር መታረቅህ | 7 ቁጥር

#እግዚአብሔርን_እንዲህ_በለው..!

አንተን ሊያሳስብህ የሚገባው ነገር ከእግዚአብሔር ጋር መታረቅህ ብቻ ነው። አንተ መምሰል የሚገባህ ከቅጣቱ ነፃ መሆን የሚፈልግ ባሪያ ብቻ ሳይሆን በመጀመሪያ የአባቱን ልብ ደስ ማሰኘት የሚፈልግ ልጅ ነው። ለአምላክህ እንዲህ በለው “አንተን ደስ ማሰኘት፣ ከአንተ በረከት ማግኘቴ፣ ለእኔ እጅግ አስፈላጊዬ ነው። አንተን በልቤ ውስጥ አገኝህ ዘንድ ከአንተ ጋር መታረቅ እፈልጋለሁ። እኔን የሚያሳስበኝ ከአንተ ጋር መታረቄ ብቻ ሳይሆን የመስቀሉ ፍቅርህ በልቤ ውስጥ መሳሉና በቀጣይ ህይወቴ ከአንተ ጋር የሚኖረኝ ህብረት ነውና አንተም ልሆንልህ እንደምትፈልገው አድርገኝ” በለው።

#አቡነ_ሺኖዳ_ሣልሳ