Get Mystery Box with random crypto!

7 ቁጥር

የቴሌግራም ቻናል አርማ sebat_kutr — 7 ቁጥር 7
የቴሌግራም ቻናል አርማ sebat_kutr — 7 ቁጥር
የሰርጥ አድራሻ: @sebat_kutr
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 1.98K
የሰርጥ መግለጫ

፯ ቁጥር ሰው የመሆን ሚስጥር መፍቻ
✔በመፅሀፍ ቅዱስ ውስጥ 7 ቁጥር 735 ጊዜ የተጠቀሰ ሲሆን በዚህም ቻናል ጠቅለል ተደርጎ የሚዳሰስ እንዲሁም ኢትዮጵያና ሰባት ቁጥርን ከቀደምት አባቶቻችን እውቀት በመጨለፍ ምን እንደሚያገናኛቸው በስፋት የሚዳሰስበት በተጨማሪም ስለ አውሬው ቁጥር፣ስለ መናፍስቶች ድብቅ ሴራ የሚቀርብበት ቻናል በመሆኑ ይህን ቻናል በመቀላቀል በቂ ግንዛቤን ይያዙ !

Ratings & Reviews

2.33

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

1

3 stars

0

2 stars

1

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች

2022-08-28 13:51:36
#ሰውን_የሚጎዳው_ክፉ_ልብ_ነው!

ሰው ሆይ! የሚጎዳህ ሀብትህ አይደለም፤ ድኽነትህም አይደለም። ሰውን የሚጎዳው ክፉ ልብ ነው። ክፉ ልብ ደግሞ በሀብትም፣ ሀብት በማጣትም የሚመጣ አይደለም። ክፉ ልብ ሌሎች ክፉ ልቦችን ይወልዳል። እሳት እሳትን እየወለደ ብዙ እንጨቶችን እንደሚበላ ኹሉ ክፉ ልብም እንደዚህ ነው።

አንተ ሰው! ይህን ማወቅ ትወዳለህን? ክፉ ምግባር ወይም በጎ ምግባር በተፈጥሮ የሚገኙ አይደሉም። እነዚህ ኹለቱ ከክፉ ልብ ወይም ከመልካም ልብ የሚገኙ ናቸው።

ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ

አምስቱ የንስሐ መንገዶች
198 viewsNatnael, 10:51
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-03 17:35:37
#ላንተ_ከሰጠሁህ_ትጠፋለህ!

ሁለት ሰዎች በአንድ ጉዳይ አብረው ይጸልያሉ። አንደኛው ጸሎቱ ተመለሰለት፣ አንደኛው ሳይመለስለት ቀረ። በዚህ ጊዜ ጸሎቱ ያልተመለሰለት፡- “ጌታ ሆይ ሁለታችንም እኩል ጸለይን ለእርሱ ሰጥተኸው ለእኔ የከለከልከኝ ለምንድን ነው?” አለው። እግዚአብሔርም፡- “ለእርሱ ባልሰጠው ይጠፋል፣ ላንተ ከሰጠሁህ ትጠፋለህ” አለው።

እግዚአብሔር ከራሳችን በላይ እኛን ያውቀናል። ለአንዳችን በመስጠት፣ አንዳችንን በመከልከል ዕድሜያችንን ያረዝመዋል። መስጠቱም መንሣቱም ሁለቱም ለፍቅር ነውና ስለሆነልን ስለሚሆንልንና ስላልሆነልን ነገር ሁሉ ተመስገን ማለትን አንርሳ፡፡
506 viewsNatnael, 14:35
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-16 09:06:24
#ከማውራት_ይልቅ_መስማትን_ምረጥ!

አባ ዮሴፍ አባ ንስጥሮስን እንዲህ ሲል ጠየቀው "እርሱን መቆጣጠር አልቻልሁምና ስለ አንደበቴ ምን ባደርግ ይሻለኛል?"

አረጋዊው ንስጥሮስም "በምትናገርበት ጊዜ ሰላምን ታገኛለህን?" ሲል ጠየቀው እርሱም "አላገኝም" ብሎ መለሰ። አረጋዊውም "ሰላምን የማታገኝ ከሆነ ስለምን ትናገራለህ? ዝም በል፣ ንግግርም በሆነ ጊዜ ከማውራት ይልቅ መስማትን ምረጥ!"

ምንጭ፦ Paradise of the holly fathers
2.2K viewsNatnael፲፪, 06:06
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-10 14:59:03
#ወደ_እግዚአብሔር_በመጸለይሽ_ምን_አተረፍሽ?

አንዲት ሴት በአንድ ወቅት እንዲህ ተብላ ተጠየቀች፦

አዘውትረሽ ወደ እግዚአብሔር በመጸለይሽ ምን "ትርፍ" ታገኛለሽ?

እሷም መለሰች፦ ብዙውን ጊዜ "ምንም አላገኘሁም" ይልቁንም "ነገሮችን አጣለሁ"

እናም ወደ እግዚአብሔር በመጸለይ ያጣችውን ሁሉ ጠቀሰች፦
"ኩራቴን" አጣሁ።
"ትዕቢቴን" አጣሁ።
"ስግብግብነቴን" አጣሁ።
"ክፉ ፍላጎቴን" አጣሁ።
"ቁጣዬን" አጣሁ።
"ራስ ወዳድነቴን" አጣሁ።
"ተንኮለኛነቴን" አጣሁ።
"ምቀኝነቴን" አጣሁ።
"ፍትወትን" አጣሁ።
"የመዋሸት ደስታን" አጣሁ።
"የኃጢአትን ጣዕም" አጣሁ።
"ትዕግስት ማጣትን" አጣሁ።
"ተስፋ መቁረጥን" አጣሁ።

አንዳንድ ጊዜ የምንጸልየው አንድን ነገር ለማግኘት ብቻ ሳይሆን በመንፈሳዊ ህይወታችን እንድናድግ የማይፈቅዱልንን ክፉ ነገሮች እንድናጣ ነው።

ጸሎት ያስተምራል፣ ያጠናክራል እናም ይፈውሳል።*ጸሎት መልስ ይዞ ከመምጣቱ በፊት ለጸሎታችን መልስ ምቹ አድርጎ ይሰራናል። ጸሎት በቀጥታ ከእግዚአብሔር ጋር የሚያገናኘን ድልድይ ነው!

“ሳታቋርጡ ጸልዩ፤ በሁሉ አመስግኑ፤ ይህ የእግዚአብሔር ፈቃድ በክርስቶስ ኢየሱስ ወደ እናንተ ነውና።” 1ኛ ተሰሎንቄ 5፥17-18
3.2K viewsNatnael, 11:59
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-02 08:29:34
#ከሰው_ብትጣላ

ወይ ታሸንፋለህ አልያም ትሸነፋለህ። ቤተ ክርቲያንን ግን ብትጣላ፣ ታሸነፍ ዘንድ የሚቻልህ አይደለም። እግዚአብሔር በደሙ መስርቷታል፤ እንግዲህ ማን ሊነቀንቃት ይችላል?
2.5K viewsNatnael፲፪, 05:29
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-04-29 10:14:49
#ብልጡ_ዲያብሎስ

"ከዲያብሎስ ዘዴዎች አንዱ በመከራችን ሰዓት እንድንፈዝ ማድረግ ነው፡፡በዚህ ጊዜ በእግዚአብሔር ላይ ያለን ተስፋ ይሟጠጣል፡፡ እግዚአብሔር በእርሱ ተስፋ የምታደርገውን ነፍስ እግዚአብሔር አይረዳኝም እስክትል ድረስ በመከራ እንድትንገላታ አይተዋትም፡፡"

#አባ_መቃርዮስ

" እግዚአብሔርን በተስፋ ለሚጠብቁት ለምትሻውም ነፍስ መልካም ነው።"
(ሰቆቃው ኤርምያስ 3፥25)
2.1K viewsNatnael, 07:14
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-04-21 17:32:39 #ጸሎተ_ሐሙስ_እና_ሥርዓተ_ቤተከርስቲያን

በጸሎተ ሐሙስ በቤተ ክርስቲያን የሚፈጸም ሥርዓት በዚህ ዕለት ስግደቱ፣ ጸሎቱ፣ ምንባባቱ እንደ ተለመደው ይከናወናሉ፡፡ መንበሩ (ታቦቱ) ጥቁር ልብስ ይለብሳል፡፡ ጸሎተ ዕጣን ይጸለያል፤ ቤተ ክርስቲያኑም በማዕጠንት ይታጠናል፡፡ ሕጽበተ እግር ይደረጋል፡፡ ቅዳሴ ይቀደሳል፡፡ በየቤቱ ደግሞ ጉልባን ይዘጋጃል፡፡

#ሕጽበተ_እግር ከቀኑ በዘጠኝ ሰዓት ዲያቆኑ ሁለት ኵስኵስቶችን ውኃ ሞልቶ ያቀርባል፤ አንዱ ለእግር፣ አንዱ ለእጅ መታጠቢያ፡፡ 'ጸሎተ አኰቴት' በመባል የሚታወቀው የጸሎት ዓይነት ይጸለያል፡፡ ወንጌል ተነቦ ውኃው በካህኑ (በሊቀ ጳጳሱ) ይባረክና የሕጽበተ እግር ሥርዓት ይከናወናል፡፡ ይኸውም ጌታችን የደቀ መዛሙርቱን እግር በማጠብ ያሳየውን የተግባር ትምህርት ለማሳየት ነው (ዮሐንስ. ፲፫፥፲፬)፡፡ ከውኃው በተጨማሪ የወይራና የወይን ቅጠልንም ለሥርዓተ ሕጽበቱ ማስፈጸሚያነት እንጠቀምባቸዋለን፡፡ ምሥጢሩም የሚከተለው ነው፤ ወይራ ጸኑዕ ነው፡፡ ወይራ ክርስቶስም ጽኑዕ መከራ መቀበሉን ከማስረዳቱ በተጨማሪ እኛም (እግራችንን የሚያጥቡን አባቶች እና የምንታጠበው ምእመናን) መከራ ለመቀበል ዝግጁ ነን ለማለት ሥርዓተ ሕጽበቱን በወይራ እንፈጽማለን፡፡ የወይኑ ቅጠልም መድኃኒታችን ክርስቶስ በወይን የተመሰለ ደሙን አፍስሶ ለምእመናን የሕይወት መጠጥ አድርጎ መስጠቱን ለማዘከር በወይን ሥርዓተ ሕጽበትን እናከናውናለን (ማቴዎስ. ፳፮፥፳፮)፡፡ በቀኝና በግራ የቆሙ ሊቃውንትም "ሐዋርያቲሁ ከበበ እግረ አርዳኢሁ ሐጸበ" እያሉ ይዘምራሉ፡፡ ይህ ሥርዓት ከተጠናቀቀ በኋላ ሥርዓተ ቅዳሴው ተከናውኖ ቅዱስ ሥጋውን ክቡር ደሙን ምእመናን ይቀበላሉ፡፡

#ቅዳሴ የጸሎተ ሐሙስ ቅዳሴ የሚከናወነው በተመጠነ ድምፅ ሲኾን፣ እንደ ደወል (ቃጭል) የምንጠቀመውም ጸናጽልን ነው፡፡ ልኡካኑ የድምፅ ማጉያ ሳይጠቀሙ በለኆሣሥ (በቀስታ) ይቀድሳሉ፡፡ ምክንያቱም ይሁዳ በምሥጢር ጌታችንን ማስያዙን ለመጠቆም ሲኾን፣ በሌላ በኩል ደግሞ የዘመነ ብሉይ ጸሎት ዋጋው ምድራዊ እንደ ነበር ለማስታወስ ነው፡፡ በመቀጠል ክብር ይእቲ፣ ዕጣነ ሞገር፣ ዝማሬ የተባሉ የድጓ ክፍሎች ተዘምረው አገልግሎቱ ይጠናቀቃል፡፡ ሕዝቡም ያለ ኑዛዜና ቡራኬ ይሰናበታሉ፡፡

#ጉልባን፦ ጉልባን ከባቄላ ክክ፣ ከስንዴ ወይንም ከተፈተገ ገብስ ጋር አንድ ላይ ተቀቅሎ የሚዘጋጅና የጸሎተ ሐሙስ ዕለት የሚበላ ንፍሮ ነው፡፡ በጸሎተ ሐሙስ በቤት ውስጥ ከሚፈጸሙ ተግባራት አንዱ ጉልባን ማዘጋጀት ነው፡፡ ጉልባን እስራኤላውያን ከግብጽ ባርነት ሲወጡ በችኮላ መጓዛቸውን የምናስታውስበት ከእስራኤላውያን የመጣ ትውፊታዊ ሥርዓት ነው፡፡ በአገራችን ኢትዮጵያ አብዛኞቹ የትውፊት ክንዋኔዎች የብሉይ ኪዳን መነሻ ስላላቸው ይህ ሥርዓት ዛሬም በኢትዮጵያውያን ምእመናን ዘንድ ይከበራል፡፡ ጉልባን እስራኤላውያን ከባርነት በወጡ ጊዜ አቡክተው፣ ጋግረው መብላት አለመቻላቸውን ያስታውሰናል፡፡ በወቅቱ ያልቦካውን ሊጥ እየጋገሩ ቂጣ መመገብ፤ ንፍሮ ቀቅለው ስንቅ መያዝ የመንገድ ተግባራቸው ነበርና፡፡ ይህን ታሪክ ለማሰብም በሰሙነ ሕማማት በተለይም በጸሎተ ሐሙስ ቂጣና ጉልባን ይዘጋጃል፡፡ በጸሎተ ሐሙስ የሚዘጋጀው ጉልባንና ቂጣ ጨው በዛ ተደርጎ ይጨመርበታል፡፡ ይኸውም ጨው ውኃ እንደሚያስጠማ ዅሉ፣ ጌታችንም በመከራው ወቅት ውኃ መጠማቱን ለማስታወስ ነው፡፡
ወስብሐት ለእግዚአብሔር፡፡

ምንጭ፦ ስምዐ ተዋሕዶ (ልዩ ዕትም ዘሰሙነ ሕማማት)፣ ፳፻፬ ዓ.ም
2.2K viewsNatnael, 14:32
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-04-17 07:07:57 #በዓለ_ሆሣዕና

ሆሣዕና ማለት መድኃኒት ማለት ነው። አንድም ሆሣዕና ማለት አሁን አድን ማለት ነው። በዳዊት መዝሙር ቃሉ ተጠቅሷል "ኦ እግዞኦ አድህንሶ አቤቱ አሁን አድን (መዝሙር 117÷25) በአርያም የእግዚአብሔር ማደሪያ የሆነውን ሰማይ ያመለክታል።

የመጀመሪያው ከሮማውያን ቀኝ አገዛዝ አድነን የሚል የሥጋ ጩኸት ሲሆን ምስጢሩ ግን ከሞተ ሥጋ እና ከሞተ ነፍስ አድነን ማለታቸው ነበር።

ይህ በዓል ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ወደ ኢየሩሳሌም ገብቶ በመቅደሱ ዙሪያ ያሉትን ለዋጮችንና ሻጮችን ያስወጣበት፤
ቤተ መቅደሱ የጸሎት ቤት መሆኑን ያወጀበትና ክብሩን የገለጸበት በዓል ነው። ከዘጠኙ ዐበይት በዓላትም አንዱ ነው።

በዚህ ዕለት የእስራኤል ሕዝብ የዘንባባ ዝንጣፊ በመያዝ ሆሣዕና በማለት እየጮኹ ኢየሱስ ወደ ኢየሩሳሌም ሲገባ አጅበውታል። ትንቢቱም ይፈፀም ዘንድ ውርንጫውን በወይን ግንድ ያስራል ተብሎ እንደተፀፈ (ዘፍጥረት 49 ዘካርያስ 11 9÷9 ኢሳይያስ 40÷20) ማለት ነው።

ቀደምት ነቢያት ዘመነ መዓት መምጣቱን ለማሰታወስ በፈረስ ተቀምጠው ዘገር ነጥቀው በከተማ ሲዘዋወሩ ዘመነ ሣህል (ዘመነ ምሕረት) መምጣቱን ለማሳየት ደግሞ በአህያ ላይ ተቀምጠው ይታዩ ነበር። ይህ ምሥጢርም በቅዱሳት መጻሕፍት በልዩ ልዩ መንገድ ተመዝግቦ ይገኛል፡፡ በማቴዎስ ፳፩፥፩-፲፩፤ በማርቆስ ፲፩፥፩-፲፤ በሉቃስ ፲፱፥፳፰-፵ እና በዮሐንስ ፲፪፥፲፪-፲፭ በተጻፈው ኃይለ ቃል መሠረት መመልከት ይገባል።

ያን ጊዜ ጌታ ከደቀ መዛሙርቱ ሁለቱን ላከና "በፊታችሁ ወደ አለ ሀገር ሂዱ አህያዋን ከውርንጭላዋ ጋር ታስራ ታገኛላችሁ ፈትታችሁ አምጡልኝ" አላቸው። (ሉቃስ ፲፰÷28)

ሰው ሁሉ ከማዕሠረ ኃጢአት ለመፈታተ እንደ ደረሰ ለማጠየቅ ነው። የሐዋርያት አገልግሎት የታሰሩትን በወንጌል ቃል መፍታት ነው። ሌቦች አጋንንት ያሠሯቸው ብዙ የኃጢአት እስረኞች አሉ። ጌታ የታሰሩትን እንደ እሱ እንዲፈቱ ደቀ መዛሙርቱን አዟቸዋል።

አህያ የተናቀች ናት ራሳቸውን ዝቅ ባደረጉ መንፈሳቸው ወደ ተሰበረ አምላክ እንደሚመለከት ያስተምራል (ኢሳይያስ 53÷23 ማቴዎስ 11÷29) አንተም የማትቆረቁር ሕገ ወንጌል ሰጠህን ሲሉ ልብሳቸውን ጎዝጉዘው ተቀብለውታል። "እም አፈ ደቂቅ ወሕፃናት አስተዳሎከ ስብሐት በእንተ ጸላዒ።,ከመ ትንስቶ ለጸላዒ ወለገፋዒ" (መዝሙር ፰÷፪)
ባለ አእምሮ ነን የሚሉት ልብ ሲታወር አንደበታቸው በሰይጣን ምክር ሲዘጋ የሕፃናት አንደበት ምስጋናን ያዘንብ ነበር።

ቤተ ፋጌ ማለት ደግሞ "የበለስ ቤት" ማለት ነው። በእኛ አባቶች ደግሞ "የተመሳቀለ ጎዳና" ተብሎ ተተርጉሟል። ጌታችን ከደብረ ዘይት ተራራ አካባቢ ወደ ኢየሩሳሌም ሲገባ አዕሩግና ሕፃናት ልብሳቸውን እንዲሁም የዘንባባ ዝንጣፊ በማንጠፍ "ሆሣዕና ለዳዊት ልጅ በጌታ ስም የሚመጣ የተባረከ ነው" እያሉ ክብሩንና መድኃኒትነቱን ገልጠዋል (ሉቃስ 19÷38 መዝሙር ፰÷፪)።

በዚህም ዕለት ዘንባባ እየተባረከ ለሕዝብ ይታደላል።
2.0K viewsNatnael፲፪, 04:07
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-04-04 15:13:43
#እግዚአብሔርን_እንዲህ_በለው..!

አንተን ሊያሳስብህ የሚገባው ነገር ከእግዚአብሔር ጋር መታረቅህ ብቻ ነው። አንተ መምሰል የሚገባህ ከቅጣቱ ነፃ መሆን የሚፈልግ ባሪያ ብቻ ሳይሆን በመጀመሪያ የአባቱን ልብ ደስ ማሰኘት የሚፈልግ ልጅ ነው። ለአምላክህ እንዲህ በለው “አንተን ደስ ማሰኘት፣ ከአንተ በረከት ማግኘቴ፣ ለእኔ እጅግ አስፈላጊዬ ነው። አንተን በልቤ ውስጥ አገኝህ ዘንድ ከአንተ ጋር መታረቅ እፈልጋለሁ። እኔን የሚያሳስበኝ ከአንተ ጋር መታረቄ ብቻ ሳይሆን የመስቀሉ ፍቅርህ በልቤ ውስጥ መሳሉና በቀጣይ ህይወቴ ከአንተ ጋር የሚኖረኝ ህብረት ነውና አንተም ልሆንልህ እንደምትፈልገው አድርገኝ” በለው።

#አቡነ_ሺኖዳ_ሣልሳ
2.0K viewsNatnael, 12:13
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-03-29 17:43:49
#ከእጅህ_ተቀብሎ_የለበሰው_ክርስቶስ_ነው!!

በገነተ አበው እንደ ተጻፈ፣ አንድ መነኩሴ ታርዞ በብርድ ይሰቃይ ለነበረ ምስኪን የለበሰውን የመነኩሴ መጎናጸፊያ አውልቆ ሰጠው። ከጥቂት ጊዜ በኋላም በገዳም ሆኖ የሰፋቸውን ሰሌኖች ለመሸጥና የእለት ምግቡን ገዝቶ ለመመለስ ወደ ገበያ ሲወጣ፣ በመንገድ ዳር የቆመች አንዲት ዘማ ያን ለምስኪኑ ሰው የሰጠውን የመነኩሴ መጎናጸፊያ ለብሳው ያያታል።

ባየው ነገር የተደናገጠው መነኩሴ "የምድር መላእክት የሚለብሱትን ይህን የክብር ልብስ በከንቱ ቦታ እንዲውል አደረግኹት" እያለ ማልቀስና መቆጨት ጀመረ። ሲያዝንም ሳለ የእግዚአብሔር መልአክ ተገልጦ "አይዞህ አትዘን፤ መጎናጸፊያህን ለዚያ ምስኪን በሰጠህበት ቅጽበት ከእጅህ ተቀብሎ የለበሰው ክርስቶስ ነው። ከዚያ በኋላ ለሆነው ሁሉ አንተ ተጠያቂ አይደለህም" ሲል አጽናናው።
1.9K viewsNatnael, 14:43
ክፈት / አስተያየት ይስጡ