Get Mystery Box with random crypto!

#ከእጅህ_ተቀብሎ_የለበሰው_ክርስቶስ_ነው!! በገነተ አበው እንደ ተጻፈ፣ አንድ መነኩሴ ታርዞ በብ | 7 ቁጥር

#ከእጅህ_ተቀብሎ_የለበሰው_ክርስቶስ_ነው!!

በገነተ አበው እንደ ተጻፈ፣ አንድ መነኩሴ ታርዞ በብርድ ይሰቃይ ለነበረ ምስኪን የለበሰውን የመነኩሴ መጎናጸፊያ አውልቆ ሰጠው። ከጥቂት ጊዜ በኋላም በገዳም ሆኖ የሰፋቸውን ሰሌኖች ለመሸጥና የእለት ምግቡን ገዝቶ ለመመለስ ወደ ገበያ ሲወጣ፣ በመንገድ ዳር የቆመች አንዲት ዘማ ያን ለምስኪኑ ሰው የሰጠውን የመነኩሴ መጎናጸፊያ ለብሳው ያያታል።

ባየው ነገር የተደናገጠው መነኩሴ "የምድር መላእክት የሚለብሱትን ይህን የክብር ልብስ በከንቱ ቦታ እንዲውል አደረግኹት" እያለ ማልቀስና መቆጨት ጀመረ። ሲያዝንም ሳለ የእግዚአብሔር መልአክ ተገልጦ "አይዞህ አትዘን፤ መጎናጸፊያህን ለዚያ ምስኪን በሰጠህበት ቅጽበት ከእጅህ ተቀብሎ የለበሰው ክርስቶስ ነው። ከዚያ በኋላ ለሆነው ሁሉ አንተ ተጠያቂ አይደለህም" ሲል አጽናናው።