Get Mystery Box with random crypto!

ዥ ን ጉ ር ጉ ር . . .

የቴሌግራም ቻናል አርማ samuel_dereje — ዥ ን ጉ ር ጉ ር . . .
የቴሌግራም ቻናል አርማ samuel_dereje — ዥ ን ጉ ር ጉ ር . . .
የሰርጥ አድራሻ: @samuel_dereje
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 972
የሰርጥ መግለጫ

ሽ ራ ፊ : ቃ ላ ት
ስ ባ ሪ ፡ ተ ረ ኮ ች
@Samvocado
https://linktr.ee/samueldereje

Ratings & Reviews

2.00

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

0

3 stars

1

2 stars

1

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች

2022-12-09 12:47:36
204 viewsSαmuel, 09:47
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-12-06 12:59:43
339 viewsSαmuel, 09:59
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-12-03 18:52:13
427 viewsSαmuel, 15:52
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-12-02 11:37:47 ይበለኝ!
ቀለምኩ ፥ ደመኩ ብዬ አንቺን ገፋዉ።
ለካ ነጸብራቅ ነበርኩ ፥ በብርሃንሽ የፈካዉ . . .
464 viewsSαmuel, 08:37
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-12-01 20:41:44
456 viewsSαmuel, 17:41
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-11-30 13:11:19 ልቤ እስከዚም ናት ፥ አትሆነኝም እንዳላለ . . .

ሳቅሽን የሰማ ቀን ፥ የሚወደዉን ዜማ ለየ። የካሳ ክራር ጎረበጠዉ ፥ ሲናትራ ያስቆጣዉ ጀመር። በሚያወሩ አይኖችሽ ከከዋክብት ፥ በሚያፈዝ ጉንጭሽ ከጨረቃ ተኳረፈ። ጠረንሽ ከሽቱ ፥ መአዛሽ ከጽጌ አወደዉ። ተሸነፈ!
በእርጋታሽ ችኩል አለምን ፥ በእቅፍሽ ራሱን ካደ . . .

አልፎ ገባዉ!
ዉበት አይደል ፥ መላመድ ነዉ።
ሰበብንም ፥ ትናንትንም የሚያስክደዉ።


@samuel_dereje
450 viewsSαmuel, edited  10:11
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-11-27 18:06:44 እቃዣለሁ!

ጊዜ ነፋስ ፥ እድሜ ገለባ ሆኖ በሚነፍስ ጊዜ የሚበር እድሜ ታቅፌ አያለሁ። ነፋስ ገለባዉን ሲያተን ፥ እኔ ልይዝ ስከተል...

ስነቃ ደግሞ ተክዛለሁ።

ስለሞት ፥ ስለማለፍ አስባለሁ። መኖሬን የሚተዝት እራፊ ምልክት ሳልተዉ ፤ በረሃ መሃል እንዳረፍ ኮቴ በጊዜ ልተን ፥ ልጠፋ ነዉ ብዬ

አስባለሁ ፥ አስባለሁ . . .
እዉነት! እውኔን ከህልሜ ምን ለየዉ?



@samuel_dereje
522 viewsSαmuel, edited  15:06
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-11-23 20:09:50
785 viewsSαmuel, 17:09
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-11-22 07:48:54 ሲ ጀ ም ሩ

እሱ ... እንዳሻው የሚተወዉ ፍቅር እንዳለ ያስብ ነበር። ቀን አብራዉ ውላ ሲጨልም "ደና ሁን" ብትለዉ ልቡ ሳይዳምን እንደሚያበቃ...

እሷ ... ከዚህ ሁሉ ህመም ኋላ የምትከፍተዉ የልብ በር እንደሌለ ታስብ ነበር ። ልትከፍተዉ ብትሻ እንኳ ቁልፉ በአለማመን ጥልቅ ዉስጥ እንደወደቀ. . .

ሲ ጀ ም ሩ

እሱ .... እሷን ሊተካ የሚችልበት እልፍ ምክንያት እንዳለ ያስብ ነበር። ይሁን ብሎ ሊወዳት እንደጀመረ

እሷ ... እሱ እስካልከፋ የሷ ልብ ነጭ እርግብ እንደሆነ ታስብ ነበር። ልትጎዳዉ አቅም እንደሌላት

ሲ ጀ ም ሩ

እሱ ... አብሮ መሆን ብቻ ላለመሆን የሚሹት መጣመር ነዉ ብሎ ያምን ነበር። የምርጫ ጉዳይ እንጂ የሚያስር ዉቃቢ እንደሌለዉ

እሷ ... ለልብ ጋሻ ይዘዉ "ማፍቀር" ፤ ከመሟሟት የሚያድን ጥላ ነዉ ብላ ታምን ነበር። ከመድማት የሚታደግ እንጂ ለራስ ለወዳጅ የሚተርፍ ጦር እንዳልሆነ

ይሄ ሁሉ ሀ ሲሉ የመተሩት ስሌት ነዉ። ቀን ዉለዉ ፥ ቀን ቆጥረዉ ሲከርሙ የተረሳቸዉ . . .

ሲ ቋ ጩ ት

እሷ . . . ዘግታ የኖረቸዉ ልብ ብትከፍተዉ ከሚቆስለዉ በላይ እንደቆሰለ ገባት። መክፈት ከዚህ አያብሰዉ እንደነበር ... እርግብ ልብ እንዳልነበራት ... አለማመን ከመክዳት በላይ እንዳጸለማት

እሱ . . . ልቡ ገና መለየትን ሲያስብ ዳምኖ እንደነበር ገባዉ። ችላ ሚባል መጣመር እንደሌለ ... "ሰው" ለክተዉ ሰፋኝ ብለዉ የሚያወልቁት ሸበጥ እንዳልሆነ . . . በለኩ ቁጥር ለሁሉ ህመም እንደሚተዉ


ግን ቋጭተዉትም ፍቅር ምን መልክ እንዳለዉ አልተረዱም። አስልተዉ እንደምያደርሱበት ፣ ተርትረዉ እንደማይሰፉት...

ሰዉ አይደሉ . . .

ፍ ቅ ር ስ "ፍቅር" አይደል . . .






@samuel_dereje
574 viewsSαmuel, edited  04:48
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-11-21 07:51:04 በማለዳ ወይራ እንደለኮሱበት ጎጆ ጭስ ያፈነዉ ከተማ ሳይ . . .

እንደሁሉ ያገሬዉ ሰዉ ደጁን ጠርጎ ጥራጊዉን በእሳት እንደሚያነድ ፤ ትዝታሽን ብርታት ኖሮኝ ከሳሎኔ ገፍቼ በራፌ ላይ ባነደዉ ፥

ስማቅቅ "ምን መሆኑ ነዉ" ያለኝ መንደር
ባንቺ ፍቅር መታፈንን ያየዉ ነበር ....
441 viewsSαmuel, 04:51
ክፈት / አስተያየት ይስጡ