Get Mystery Box with random crypto!

ከ ኢስላም Gallery

የቴሌግራም ቻናል አርማ real66gallery — ከ ኢስላም Gallery
የቴሌግራም ቻናል አርማ real66gallery — ከ ኢስላም Gallery
የሰርጥ አድራሻ: @real66gallery
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 1.62K

Ratings & Reviews

2.00

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

0

3 stars

0

2 stars

3

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች

2023-05-11 08:12:34
የአፕልኬሽን ጥቆማ 4፦ [ 120+ የኡስታዝ ወሒድ ዑመር ]

ለአጠቃቀም ምቹ የሆነ ኢስላሚክ አፕ ነው። የአፕልኬሽኑ መተግበሪያ የሚሰጠው አገልግሎት፦

አፑ በውስጡ አራት ማህደሮች ያሉት ሲሆን እያንዳንዱ ማህደር የራሱ የሆነ ሰፋ ያለ ማብራሪያ አለው።

ስለ ኢስላም፦

* ሰለ ሰላት
* ስለ አቂዳ
* ስለ ፊቂህ
* ስለ ተውሂድ
* ስለ ሽርክ ወ.ዘ.ተ… ይዟል።

እንዲሁም ስለ ክርስቲያን፦

* ስለ ስላሴ
* እየሱስን ጨምሮ ሰለ ነብያቶች አምላክ፣
* ሴቶች በባይብል ያላቸው ቦታ
* ስለ ነብያቶች ከበቂ ማስረጃ እና ማብራሪያ ጋር ከጥያቄዎች ጋር በብዙ አጭቆ የያዘ አፕ ነው።

መጠን፦ 3.1 Mb
______________

አፕልኬሽኑን በዚህ ቴሌግራም ቻናል ላይ ታገኙታላችሁ
||
https://t.me/Abu_Umair2
141 viewsAbu Umair, 05:12
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-08 07:07:44
የአፕልኬሽን ጥቆማ 3፦ [ Ayah ]

ለአጠቃቀም ምቹ የሆነ ሙሉ የቁርዓን አፕ ነው። የአፕልኬሽኑ መተግበሪያ የሚሰጠው አገልግሎት፦

1. 30 ጁዝ ቁርአን ከተፍሲር ጋር ይዟል።

2. ቦተውን የማናስታውሰው የቁርአን አያ ካለ ምን ሱራህ ላይ ስንተኛው አያህ ላይ እንደሆነ Search አርገን እንድናገኝ ያስችለናል።

3. ቁርአን መቅራት ካቆምንበት ቦት ላይ በየቀኑ ቁርአን መቅራታችንን እንድንቀጥል ያስታውሰናል (በፈለግነው ሰአት ሞልተን)።

4. በቀን አንደ ወሳኝ አጭር የቁርአን አያህ ያስታውሰናል። በጁምዐ ቀን ደግሞ ሱረቱል ካህፍን መቅራት እንዳለብን ይነግረናል።

5. እንዲሁም በውስጡ የሂጅሪ አቆጣጠርን ይዟል።

መጠን፦ 124 ሜጋባይት
___________________

አፕልኬሽኑን በዚህ ቴሌግራም ቻናል ላይ ታገኙታላችሁ
||
https://t.me/Abu_Umair2
81 viewsAbu Umair, 04:07
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-04 07:53:46 የአፕልኬሽን ጥቆማ 2 ፦ [ نختم ]

ብዙዎቻችን በየቀኑ በመቶዎች ለሚቆጠሩ ጊዜያት ሞባይሎቻችንን እንከፍታለን። ታዲያ ስልካችንን በከፈትን ቁጥር አንድ የአላህን ቃል አንቀፅ መቅራት እንችላለን ብንባልስ? እንዴት ካልን መልሱ ነኽተም ጋር አለ።

አፕልኬሽኑ መተግበሪያ የሚሰጠው አገልግሎት፦

1. በየትኛውም አጋጣሚ ስልካችንን በከፈትን ቁጥር አንድ የቁርአን አያህ ከነ ትርጉሙ በስልካችን ስክሪን ፊት ለፊት ላይ ያመጣልናል

ታዲያ ይሄን App መተግበሪያ ስልካችን ላይ ከጫንን ቡኃላ ስልካችንን በቀን ለመቶ ጊዜ ያህል ከከፈትን በቀላሉ ሱረቱል መርየምን ከነትርጉሙ ቀራን ማለት ነው።

2. በአፑ ከ3ዐ በላይ ቃሪኦች በውስጡ ስለተካተቱበት በምንወደው ቃሪዕ በበተጅዊድ ቁርአንን አሳምረን እንድንቀራ ያግዘናል።

3. የአፕ ፕሮግራሙን ከተጠቀምንበት ጊዜ ጀምሮ በየእለቱ የመጀመሪያ ቀን ላይ በቀን፣ በሳምንታ እና በወር ምን ያህ የቁርአን አያዎችን እንደቀራን ያሳየናል።

መጠን፦ 8.1 Mb
_

ፕልኬሽኑን በዚህ ቴሌግራም ቻናል ላይ ታገኙታላችሁ
||

https://t.me/Abu_Umair2
193 viewsAbu Umair, edited  04:53
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-01 08:44:12
የአፕልኬሽን ጥቆማ 1፦ [ Muslim Pro ]

አፕልኬሽኑ መተግበሪያ የሚሰጠው አገልግሎት፦

1. የሰላት ወቅት ሲደርስ በድምፆ እና በምስል የተደገፈ የአዛን ጥሪን ከስልካችን መቀበል ያስችለናል። በውስጡም በተለያዩ ሙዐዚኖች የተመዘገቡ ድምጾች ስላሉት በወደድነው ድምፅ አዛን መስማት እንችላለን።

2. የፆም ወቅቶችን በማስታወስ ለፆም እንድንነሳሳ ያረገናል።

3. 3ዐ ጁዝ ቁርአን ከድምፅ እና ከትርጎም ጋር ይዟል።

4. የተለያዩ ዱዐዎችን ከነትርጉማቸው ይዟል።

5. ቁርአንን በእቅድ እንድናኸትም ያግዘናል።

6. ቂብላ ጠቋሚ ኮምፓስ አለው።

7. እንደ ሙስበሀ ያገለግላል።

መጠን፦ 42.3 Mb
______


አፕልኬሽኑን በዚህ ቴሌግራም ቻናል ላይ ያገኙታል
||
https://t.me/Abu_Umair2
147 viewsAbu Umair, edited  05:44
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-22 08:36:31 መላእክት ለምን ለኣደም ሱጁድ ወረዱ?
~
የላቀው አላህ እንዲህ ይላል:-
{ وَإِذۡ قُلۡنَا لِلۡمَلَـٰۤىِٕكَةِ ٱسۡجُدُوا۟ لِـَٔادَمَ فَسَجَدُوۤا۟}
''ለመላእክትም ለአደም ስገዱ ባልናቸው ጊዜ (አስታውስ)፡፡ ወዲያውም ሰገዱ።" [አልኢስራእ፡ 61]

"ለፍጡር ሱጁድ መደፋት ሺርክ ሆኖ ሳለ እንዴት ይሄ ሆነ?" ከተባለ መልሱ እንዲህ የሚል ነው፦

ሱጁድ ለሁለት ይከፈላል።
1- አምልኮታዊ ሱጁድ
2- የሰላምታ (የአክብሮት) ሱጁድ።
የመጀመሪያው ለአላህ እንጂ ፈፅሞ ለፍጡር አይሰጥም። ለፍጡር ከተፈፀም ከኢስላም የሚያስወጣ ትልቁ ሺርክ ይሆናል።
ሁለተኛው ማለትም የሰላምታ ሱጁድ ግን ኋላ ተከልክሎ እንጂ ቀደምት ህዝቦች ዘንድ የተፈቀደ ነበር። መግቢያዬ ላይ ባሰፈርኳት አንቀፅ የተገለፀው መላእክት ለኣደም የፈፀሙት ሱጁድ ይሄ አክብሮትን መግለጫ የሰላምታ ሱጁድ ነው። የነብዩላህ ዩሱፍ ወላጆች ለዩሱፍ የወረዱት ሱጁድም ይሄው አክብሮትን መግለጫ የሰላምታ ሱጁድ ነው። ስለዚህኛው ጉዳይ የላቀው አላህ እንዲህ ይላል፦
{ إِذۡ قَالَ یُوسُفُ لِأَبِیهِ یَـٰۤأَبَتِ إِنِّی رَأَیۡتُ أَحَدَ عَشَرَ كَوۡكَبࣰا وَٱلشَّمۡسَ وَٱلۡقَمَرَ رَأَیۡتُهُمۡ لِی سَـٰجِدِینَ }
"ዩሱፍ ለአባቱ፡- 'አባቴ ሆይ! እኔ አስራ አንድ ከዋክብትን፣ ፀሐይንና ጨረቃንም (በህልሜ) አየሁ፡፡ ለእኔ ሰጋጆች ሆነው አየኋቸው' ባለ ጊዜ (አስታውስ)።" [ዩሱፍ፡ 4]

ከዘመናት በኋላ ይህ ህልማቸው እውን እንደሆነ ሲገልፅ ደግሞ እንዲህ ብሏል፦
{ وَرَفَعَ أَبَوَیۡهِ عَلَى ٱلۡعَرۡشِ وَخَرُّوا۟ لَهُۥ سُجَّدࣰاۖ وَقَالَ یَـٰۤأَبَتِ هَـٰذَا تَأۡوِیلُ رُءۡیَـٰیَ مِن قَبۡلُ قَدۡ جَعَلَهَا رَبِّی حَقࣰّاۖ }
"ወላጆቹንም በዙፋኑ ላይ አወጣቸው። ለእርሱም ሰጋጆች ሆነው ወረዱለት። 'አባቴ ሆይ! ይህ ፊት ያየኋት ሕልሜ ፍች ነው። ጌታ በእርግጥ እውነት አደረጋት።' " [ዩሱፍ፡ 100]

ይሄ የሰላምታ ወይም የአክብሮት መግለጫ ሱጁድ በነብያችን ሙሐመድ ﷺ ሸሪዐ ተሽሯል፣ ተከልክሏል። ይህንን የሚጠቁመን ተከታዩ ዐብዱላህ ብኒ አቢ አውፋ ያስተላለፉት ሐዲሥ ነው።
ሙዓዝ (ብኑ ጀበል - ረዲየላሁ ዐንሁ -) ከሻም ሲመለሱ ጊዜ ለነብዩ ﷺ ሱጁድ ወረዱ።
"ምንድነው ይሄ ሙዓዝ?" አሉ።
ሙዓዝም፡ "ሻም በሄድኩኝ ጊዜ (ክርስቲያኖች) ለጳጳሶቻቸውና ለፓትሪያርኮቻቸው ሱጁድ ሲወርዱ አገኘኋቸው። እናም ይህንን ላንተ ልፈፅመው በነፍሴ ወደድኩኝ" አሉ።
የአላህ መልእክተኛ ﷺ በዚህን ጊዜ እንዲህ አሉ፦
فَلَا تَفْعَلُوا، فَإِنِّي لَوْ كُنْتُ آمِرًا أَحَدًا أَنْ يَسْجُدَ لِغَيْرِ اللَّهِ، لَأَمَرْتُ الْمَرْأَةَ أَنْ تَسْجُدَ لِزَوْجِهَا ...
"እንዲህ አታድርጉ። ከአላህ ሌላ ላለ ሱጁድ እንዲወርድ አንድንም የማዝዝ ቢሆን ኖሮ ሴት ለባሏ ሱጁድ እንድትወርድ አዝ ነበር። ... " [ኢብኑ ማጀህ፡ 1853]
ሐዲሡን ሸይኹል አልባኒይ - ረሒመሁላህ - "ሐሰኑን ሶሒሕ" በማለት ለማስረጃነት የሚያበቃው ጥንካሬ እንዳለው ገልፀዋል። [ሶሒሕ ኢብኒ ማጀህ፡ 1515]
በተመሳሳይ ለሰላምታ ከጀርባ ሰበር ብሎ ማጎንበስም የተከለከለ ነው።
=
(ኢብኑ ሙነወር፣ ሚያዚያ 14/ 2015)
የቴሌግራም ቻናል :-
https://t.me/IbnuMunewor
6 viewsibrahim omif, 05:36
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-20 22:48:27
128 viewsibrahim omif, 19:48
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-11 22:50:47 የዘካህ አወጣጥ

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ፥ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው።

2፥110 ሶላትንም አስተካክላችሁ ስገዱ፡፡ ዘካንም ስጡ፡፡ وَأَقِيمُوا الصَّلَاةَ وَآتُوا الزَّكَاةَ

የዘካ ገንዘብ ከተቀማጭ ላይ ከመቶ 2.5 % የሚሰጥ ነው፥ ነቢያችን”ﷺ” ከሁለት መቶ ዲርሀም 5 ዘካህ እንደሚወጣ ተናግረዋል። ያ ማለት የዘካህ ሒሳብ በመቶ ዲርሀም 2.5 ይሆናል፥ ስሌቱ 5፥2=2.5 ነው፦
ሡነን አቢ ዳውድ መጽሐፍ 9, ሐዲስ 18 ዐሊይ”ረ.ዐ” እንደተረከው፦ “ነቢዩም”ﷺ” እንዲህ አሉ፦ ”ሁለት መቶ ዲርሀም ለአንተ በሆነች ጊዜና ዓመት ከሞላች አምስት ደራሂም ይወጣል፥ በአንተ ምንም ነገር አይሆንም ሃያ ዲናር እስኪሆን ድረስ”። عَنْ عَلِيٍّ، – رضى الله عنه – عَنِ النَّبِيِّ صلى الله عليه وسلم بِبَعْضِ أَوَّلِ هَذَا الْحَدِيثِ قَالَ ‏”‏ فَإِذَا كَانَتْ لَكَ مِائَتَا دِرْهَمٍ وَحَالَ عَلَيْهَا الْحَوْلُ فَفِيهَا خَمْسَةُ دَرَاهِمَ وَلَيْسَ عَلَيْكَ شَىْءٌ – يَعْنِي فِي الذَّهَبِ – حَتَّى يَكُونَ لَكَ عِشْرُونَ دِينَارًا

በዚህ ሐዲስ መሠረት የአንድ ሰው ካፒታል 20 ዲናር ወይም 200 ዲርሀም ሲሆን ዘካህ ይወጅበታል። በሸሪዓህ የዘካህ አነስተኛ የክፍያ መጠን “ኒሷብ” نِصاب ይባላል፥ ይህም ኒሷብ የሚለካው 20 ዲናር ወይም 200 ዲርሀም ሲሆን ነው። “ዲናር” دِينَار‎ ማለት “የወርቅ ሳንቲም”gold coin” ማለት ሲሆን “ዲርሀም” دِرْهَم‎ ማለት ደግሞ “የብር ሳንቲም”silver coin” ማለት ነው። ይህ በጥንት ጊዜ የሸቀጥ ገንዘብ”commodity money” ነው። “ዲናር” እና “ዲርሀም” የሚለኩት በሚስቃል ነው፥ “ሚስቃል” مِثْقَال የሚለው ቃል “ሰቀለ” ثَقَلَ ማለትም “ከበደ” ከሚል ሥርወ-ቃል የመጣ ሲሆን “ክብደት” ማለት ነው።
1 ሚስቃል ወርቅ 4.25 ግራም ነው፥ 20 ሚስቃል ወርቅ ደግሞ 4,25x 20 = 85 ግራም ወርቅ ይሆናል ማለት ነው።
1 ሚስቃል ብር 2.975 ግራም ነው፥ 200 ሚስቃል ብር ደግሞ 2.975x 200= 595 ግራም ብር ይሆናል ማለት ነው።

በዘካህ ላይ የሚወጅበው ኒሷብ 85 ግራም ወርቅ ወይም 595 ግራም ብር ነው።
አንድ ሙሥሊም ያስቀመጠው ካፒታል ዓመት ከሞላው እና ያም ካፒታል 85 ግራም ወርቅ ወይም 595 ግራም ብር ያክል ከሆነ ዘካህ ማውጣት ግዴታው ነው።
ዘካቱል ማል የሚወጣበት አነስተኛ ዋጋ የብር ኒሷብ ስለሆነ አብላጫው ምሁራን የብር ኒሷብን መሠረት ባደረገ መልኩ ከዚያ እንዲወጣ ፈትዋ ሰተዋል፥ ስለዚህ አንድ ሰው ዓመት የተቀመጠ 89,250 ብር(ገንዘብ) እና ከዛ በላይ ካለው ዘካህ ማውጣት ግዴታ አለበት።

እንዴት? ካላችሁ የብር ኒሷብ ወደ ወረቀት ገንዘብ”Fiat money” ለመቀየር ብርን ዛሬ ባለው የወቅቱ ግብይት ለናሙና ያክል መሥራት ይቻላል። በኢትዮጵያ አንድ ግራም ብር"silver" አሁን ባለኝ መረጃ 150 ብር"ገንዘብ" ነው፥ ስናሰላው 150×595= 89,250 ብር(ገንዘብ) ይሆናል።
ለምሳሌ፦ እኔ 100 ሺህ ብር ቢኖረኝ ከ 100 ሺህ ብር ላይ 2.5 % ዘካህ ሲሰላ 2,500 ይወጅብብኛል፥ ስናሰላው 100,000×2.5፥100= 2,500 ይሆናል።
ዘካህን መስጠት አንርሳ፦
2፥110 ሶላትንም አስተካክላችሁ ስገዱ፡፡ ዘካንም ስጡ፡፡ وَأَقِيمُوا الصَّلَاةَ وَآتُوا الزَّكَاةَ

አምላካችን አሏህ ዘካን ከሚሰጡ ባሮቹ ያድርገን! አሚን።

ከዐቃቢ ኢሥላም ወሒድ
https://t.me/Wahidcom

ወሠላሙ ዐለይኩም
142 viewsibrahim omif, 19:50
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-11 07:38:47 Join us / ተቀላቀሉን



https://t.me/Abu_Umair2
25 viewsAbu Umair, 04:38
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-11 07:38:36የረመዷን ቲላዋ ግብዣ•​

በየቀኑ 1 ጁዝእበ30 ቃሪኦች

ረመዷን 17 []  ጁዝእ : 17

ቃሪእ:  ዓሊይ ጃቢር

ደቂቃ : 47:29

በፉርቃን ኦንላይን ቁርኣን ማዕከል ተመዝግቦ ለመቅራት ያመልክቱ
@FurqanOnlineQuran
⇩⇩⇩⇩⇩⇩⇩⇩⇩⇩⇩⇩⇩
https://t.me/furqan_school
27 viewsAbu Umair, 04:38
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-09 13:16:28 Join us / ተቀላቀሉን



https://t.me/Abu_Umair2
107 viewsAbu Umair, 10:16
ክፈት / አስተያየት ይስጡ