Get Mystery Box with random crypto!

ኦርቶዶክስ ተዋህዶ

የቴሌግራም ቻናል አርማ enabib — ኦርቶዶክስ ተዋህዶ
የቴሌግራም ቻናል አርማ enabib — ኦርቶዶክስ ተዋህዶ
የሰርጥ አድራሻ: @enabib
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 1.42K
የሰርጥ መግለጫ

ኦርቶዶክስ ተዋህዶ
ለማንኛውም አስተያየት @ermo13 ይጠቀሙ
በግሩፑ ለመወያየት
@Bestoom
ይህን ይጠቀሙ

Ratings & Reviews

2.33

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

1

3 stars

0

2 stars

1

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች

2022-09-01 23:56:49
እንኳን ደስ አላችሁ በዩቲዩብ የምናውቀው #ማኅቶት_ቲዩብ አሁን ደግሞ በቴሌግራም መጥቷል ለመቀላቀል ከስር ያለውን ሊንክ ንኩት።




https://t.me/+SLPMr-p0D_QzRyzI
https://t.me/+SLPMr-p0D_QzRyzI
https://t.me/+SLPMr-p0D_QzRyzI




.
7 viewsመንፈሳዊ 1K, 20:56
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-01 23:19:31 ከአክራሪ እስልምና ወደ ክርስትና
#በእውነተኛ_ታሪክ_ላይ_የተመሰረተ
ክፍል 2
#ባለታሪክ_እና_ጸሀፊ
ናሕድ ማሕሙድ ሙቱዋሊ
#ተርጓሚ ዲ/ን ዳንኤል ክብረት

ናታኒም ቲዩብ SUBSCRIBE በማድረግ አገልግሎቱን ያበረታቱ ናታኒም ማለት የእግዚአብሔር ቤት ጠራጊ ታናሽ አገልጋይ ማለት ነውና።






10 viewsማኔ ቴቄል ፋሪስ, 20:19
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-30 23:46:52 አንድም አውሬ ከባሕር ሲወጣ አየሁ፤ አሥር ቀንዶችና ሰባት ራሶች ነበሩት፥ በቀንዶቹም ላይ አሥር ዘውዶች በራሶቹም ላይ የስድብ ስም ነበረ።  ያየሁትም አውሬ ነብር ይመስል ነበር፥ እግሮቹም እንደ ድብ እግሮች፥ አፉም እንደ አንበሳ አፍ ነበሩ። ዘንዶውም ኃይሉንና ዙፋኑን ትልቅም ሥልጣን ሰጠው።  ከራሶቹም ለሞት እንደ ታረደ ሆኖ አንዱን አየሁ፥ ለሞቱ የሆነውም ቍስል ተፈወሰ። ምድርም ሁሉ አውሬውን እየተከተለ ተደነቀ፥  ለዘንዶውም ሰገዱለት፥ ለአውሬው ሥልጣንን ሰጥቶታልና፤ ለአውሬውም። አውሬውን ማን ይመስለዋል፥ እርሱንስ ሊዋጋ ማን ይችላል? እያሉ ሰገዱለት።  ታላቅንም ነገርና ስድብን የሚናገርበት አፍ ተሰጠው፥ በአርባ ሁለት ወርም እንዲሠራ ሥልጣን ተሰጠው።  እግዚአብሔርንም ለመሳደብ ስሙንና ማደሪያውንም በሰማይም የሚያድሩትን ሊሳደብ አፉን ከፈተ።  ቅዱሳንንም ይዋጋ ዘንድ ድልም ያደርጋቸው ዘንድ ተሰጠው፥ በነገድና በወገንም በቋንቋም በሕዝብም ሁሉ ላይ ሥልጣን ተሰጠው።  ከዓለምም ፍጥረት ጀምሮ በታረደው በግ ሕይወት መጽሐፍ ስሞቻቸው ያልተጻፉ በምድር የሚኖሩ ሁሉ ይሰግዱለታል። 

ጆሮ ያለው ቢኖር ይስማ። 

               የዩሐንስ ራዕይ 13÷1-9


የ 666 ትርጉሙ ምንድ ነው

ማይክሮ ቺፕስ የሚባለውስ ምንድ ነው

የአለም ፍፃሜስ መቼ ነው

ስለ አለም ፍፃሜ የሚያትተው የራዕይ መፅሐፍስ ትርጉሙ ምንድነው

የዩቲዩብ ቻናላችንን ሰብስክራይብ ያድርጉ
Ŝúbŝčŕibé our youtube channel













.
15 viewsመንፈሳዊ 1K, 20:46
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-30 21:11:57 ከአክራሪ እስልምና ወደ ክርስትና
#በእውነተኛ_ታሪክ_ላይ_የተመሰረተ
ክፍል 1
#ባለታሪክ_እና_ጸሀፊ
ናሕድ ማሕሙድ ሙቱዋሊ
#ተርጓሚ ዲ/ን ዳንኤል ክብረት

ናታኒም ቲዩብ SUBSCRIBE በማድረግ አገልግሎቱን ያበረታቱ ናታኒም ማለት የእግዚአብሔር ቤት ጠራጊ ታናሽ አገልጋይ ማለት ነውና።






38 viewsማኔ ቴቄል ፋሪስ, 18:11
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-29 18:19:16 በረከታቸው በኛ ላይ ይደርብን
አሜን
1.2K viewsJERMI, 15:19
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-29 18:17:59
"አቡነ ቄርሎስ ግብፃዊ ናቸው፤ ስለ ኢትዮጵያና ስለ ኢትዮጵያውያን የሚገዳቸው ነገር የለም። እኔ ግን ኢትዮጵያዊ ነኝ። ኃላፊነትም ያለብኝ የቤተ ክርስቲያን አባት ነኝ። ስለዚህ ስለ ሀገሬና ስለ ቤተ ክርስቲያኔ እቆረቆራለሁ። ከዚህ በቀር ለእናንተ ችሎት የማቀርበው ነገር የለኝም። ለፈጣሪዬ ብቻ የምናገረውን እናገራለሁ። እኔን ለመግደል እንደወሰናችሁ አውቃለሁ። ስለዚህ በእኔ ላይ የፈለጋችሁትን አድርጉ። ግን ተከታዮቼን አትንኩ።"
(ብፁዕ አቡነ ጴጥሮስ ሊቀ ጳጳስ ሰማዕተ ጽድቅ ዘኢትዮጵያ)

https://t.me/zikirekdusn
754 viewsJERMI, 15:17
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-29 14:27:00 ከብጹእ አቡነ ጼጥሮስ ረድኤት በረከት ያሳትፈን
689 viewsJERMI, 11:27
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-29 14:26:28 አንድ አምላክ በሆነ በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም ዛሬ ሐምሌ 22 በዚህች ቀን ኢቲዮጲያዊው ሊቀ ጳጳስ አቡነ ጴጥሮስ በሰማዕትነት አረፉ::

የ20ኛው ክፍለ ዘመን ታላቅ ሰማዕት የሆኑት አቡነ ጴጥሮስ በ1875 ዓ.ም በሰሜን ሸዋ ሀገረ ስብከት ሰሌላ አውራጃ ፍቼ ከተማ ተወለዱ::

አቡነ ጴጥሮስ በሰማዕትነት እንደሚሞቱ አስቀድመው መምህራቸው በትንቢት ነግረዋቸው ነበር።

"አለቃ ተጠምቀ" የተባሉ ቅድስናን ከሊቅነት ጋራ አስተባብረው የያዙ የቅኔ መምህራቸው አንድ ቀን አቡነ ጴጥሮስን ጠርተው "ኃይለ ማርያም አንተ ወደፊት ጳጳስ ትሆናለህ፤ በወቅቱም አረመኔ በዚህች ሀገር ይሰለጥናል። ታዲያ ያኔ አንተ ለነፍስህ ሳትሰቀቅ በሰማዕትነት እለፍ፤ ሰማዕትነት ክፍልህ ነው፣ አደራ" ብለዋቸው ነበር። ይኸውም ትንቢት ደርሶ አቡነ ጴጥሮስ በሰማዕትነት ለማረፍ በቅተዋል።

ብፁዕ አባታችን የጵጵስና ስማቸውን ከማግኘታቸው በፊት መምህር ኃይለ ማርያም ይባላሉ ነበር።

በልጅነታቸው ወላጆቻቸው ወደ ደብረ ሊባኖስ በመውሰድ በሃይማኖትና በምግባር ተኮትኩተው እንዲያድጉ አድርጎቸዋል።

የቤተ ክርስቲያንን ትምህርት ከንባብ እስከ ቅኔ ያሉትን ትምህርቶች በሚያስገርም ፍጥነት ከተማሩ በኋላ ወደ ቅኔ አውድማ ጎጃም በመሔድ በዋሽራ የቅኔ ትምህርታቸውን ፈጽመው መምህር ሆነዋል።

የዜማውንም ትምህርት ወደ ጎንደር ሔደው ተምረዋል። ወሎ ቦሩ ሜዳ ከሊቁ አካለ ወልድ የብሉያትን፤ ሐዲሳትንና የሊቃውንት ትምህርት በሚገባ አሒዱ።

በ1900 ዓ.ም ወሎ አማራ ሳይንት ሔደው ምስካበ ቅዱሳን ገዳም ገብተው ወንበር ዘርግተው ለ9 ዓመታት ቅኔንና መጻሕፍትን አስተማሩ።

በ1910 ዓ.ም ወደ ደብረ ሊባኖስ መጥተው ሥርዓተ ምንኩስና ፈጸሙ። በመምህርነት ተሾመው ደብረ መንክራት ምሁር ኢየሱስ ገዳም ለ6ዓመታት፤ በ1916 ዓ.ም በዝዋይ ደብረ ጽዮን ቅድስት ገዳም ለ3ዓመታት፤ በ1919 ዓ.ም አ.አ ማርቆስ በመምህርነትና የዓፄ ኃይለ ሥላሴ መምህረ ንስሐ ሆኑ።

ኢትዮጵያ የራሷን ጳጳሳት ስትሾም በስነ ምግባር ከተመሰከረላቸውና ከተመረጡ ጳጳሳት አንዱ ሆነው ግንቦት 18 ቀን 1921 ዓ.ም ጵጵስና ተሾሙ።

ብፁዕ አባታችን "አቡነ ጴጥሮስ ጳጳስ ዘምሥራቅ ኢትዮጵያዊ ተላዌ አሠሩ ለአቡነ ኢየሱስ ሞዐ" ተብለው መንዝና ወሎ አገረ ስብከት ተሾሙ።

ቅዱስ አባታችን ቅድስት ቤተክርስቲያናችንና ቅድስት ሀገራችንን በጸሎታቸው፣ ሕዝቡን በትምህርታቸው እየጠበቁ በተጋድሎ እየኖሩ ሳለ አረመኔው የኢጣሊያ ፋሺስት በ1928 ዓ.ም በኢትዮጵያ ላይ የግፍ ጦርነትን አውጆ ሕዝቡን በግፍ ይገድል ቤተ ክርስቲያንን ያቃጥል ጀመር።

በየገዳማቱ በርካታ ካህናትና መነኮሳት ተገደሉ፣ ብርቅዬ የቤተ ክርስቲያን ቅርሶች ተዘረፉ።

አቡነ ጴጥሮስ ይህን ግፍ በማየታቸው ከሀገራችን አርበኞች ጋር በመሆን በጸሎታቸው ሊዋጉት ተነሡ።

አባታችን ዓፄ ኃይለ ሥላሴ በመከተል ወደ ማይጨው ሔደዋል። በዚያም በመርዝ የተደገፈ ጦርነትን ፋሺስት እያደረገ ሕዝቡን ሲገል ሥራዊቱን ሲበትን ተመለከቱ።

ወደ አ.አ ከተመለሡ በኋላ ደብረ ሊባኖስ ሔደው ለሀገርና ለነፃነት መሞት ቅዱስ ተግባር መሆኑን ለሠላሌ በሚገባ አስተምረዋል።

በደብረ ሊባኖስ ገዳም በጾምና በጸሎት ተጠምደው እግዚአብሔር የኢትዮጲያን ሕዝብ በምሕረቱ እንዲታደጋት እየተማጠኑ ወደፊት ለሚመጣባቸው ተጋድሎ መዘጋጀት ጀመሩ::


ወደ አ.አ በመመለስም ይህን ተግባራቸውን ይፈጽሙ ነበር። ጠላት በመላዋ ከተማ ያሰማራቸው ባንዳዎችን አባታችንን ይቃወሟቸው ይፈለጉም ጀመረ።

አባታችን ግን "የሀገሬ ሕዝብ ለጠላት እንዳይገዛ በአደባባይ አውግዤ ጠላትን ረግሜ ባልፍ ይሻለኛል" ብለው ወሰኑ።

በግዜው የፋሽስት ኢጣልያ እንደራሴ የሆነው ራስ ኃይሉ በጥብቅ ይፈልጋቸው ያድናቸው ነበር።

እሱም ብፁዕ አባታችንን ወስዶ ለግራዚያኒ ሐምሌ 22 ቀን 1928 ዓ.ም አሳልፎ ሰጣቸው። ግራዚያኒን አጥብቆ ሲፈልጋቸው ነበርና ተደሰተ።

በኋላ ተይዘው ታሰሩ ሕዝቡንም ለፋሽሽት ለጣሊያን መንግስት እንዲገዛ ስበክ ተናገር ተባሉ።

ለዚህም መደለያ የተቀናጣ ቤት፣ ዘመናዊ መኪና፣ ከሮም መንግስት ዕውቅና ይሰጧታል ቢላቸው አሻፈረኝ አሉ።

ነገር ግን ሊገደሉ ሲፈረድባቸው በአደባባይ የእሳቸ ፍርድ ለሚጠባበቀው ሕዝብ መስቀላቸውን አንስተው በ4 አቅጣጫ ባረኩ።

በፍርድ ወንበር ላይ የተቀመጠው ዳኛም አቡነ ጴጥሮስን " ሕዝቡን ቀስቅሰዋል ራሶም አምፀዋል ሌሎችም እንዲያምጹ አድርጎዋል" አላቸው።

ቀጥሎም "ካህናቱም ሆነ የቤተ ክህነት ባለስልጣናት ሊቀ ጳጳሱም አቡነ ቄርሎስ የጣሊያን ገዢነት አምነው አሜን ብለው ሲቀበሉ እርሶ ለምን አመፁ? ለምን ብቻዋን አፈንጋጭ ሆኑ?" ሲል ጠየቃቸው።

ብፁዕ አቡነ ጴጥሮስ በቆራጥነት የሚከተለውን መለሱ፦

"አቡነ ቄርሎስ ግብፃዊ ናቸው፤ ስለ ኢትዮጵያና ስለ ኢትዮጵያዊያን የሚገዳቸው ነገር የለም፤ እኔ ግን ኢትዮጵያዊ ነኝ ሕዝቤም ጭምር፤ ሓላፊነትም ያለብኝ የቤተ ክርስቲያን አባት ነኝ፤ እኛ ኢትዮጵያዊያን ስንሞትም ስንኖርም ኢትዮጵያዊ ነን" ብለው በቁርጠኝነት ተናገሩ።

ቀጠል አድርገውም "ለፈጣሪዬ ብቻ የምናገረውን እናገራለሁ። እኔን ለመግደል እንደወሰናችሁ ዐውቃለሁ።ስለዚህ በኔ ላይ የፈለጋችሁትን አድርጉ። ግን ተከታዮቼን አትንኩ።" አሉ።

ወደ ሕዝቡ ዞር ብለውም "አረማዊ የሆነው የፋሺስት መንግስት ቤተ ክርስቲያን ለማቃጠል፣ ሕዝበ ክርስቲያን ለመግደል፣ ሃይማኖትን ለማጥፋት፣ ታሪካችንን ለማበላሸት የመጣ ነው፤ እንጂ በጎ ለመሥራት ስላልመጣ ለዚህ ግፈኛ አትገዙ። ስለ ውድ አገራችሁ፣ ስለ ቀናች ሃይማኖታችሁ ተከላከሉ። ነጻነታችሁ ከሚረክስ ሙታችሁ ስማችሁ ቢቀደስ ታላቅ ዎጋ ያለው ክብር ታገኛላችሁ። የኢትዮጵያ ሕዝብ ለዚህ ለጣላት እንዳይገዛ አውጋዣለሁ፤ የኢትዮጵያ መሬት ጠላትን ብትቀበል የተረገመች ትሁን። በፈጣሪዬ በኢየሱስ ክርስቶስ ስም የተገዘተች ትሁን።" በለው አወገዙ።

ችሎት ላይ ያለውን ሕዝብ በሙሉ ስለ እርሳቸው ሲያለቅስ አሳቸው ግን መስቀላቸውን አውጥተው እየጸለዩ ሕዝቡን ባረኩ።

ወደ መግደያ ቦታም ወሰዷቸው በዚህ ጊዜ በዛሬዋ ዕለት ከአራዳ ጊዮርጊስ ዝቅ ብሎ ባለው ቦታ በአደባባይ በጥይት ሩምታ ዘንቦባቸው በሰማዕትነት አረፋ::

ቤተ ክርስቲያንም ጥቅምት 12 ቀን 1998 ዓ.ም "አቡነ ጴጥሮስ ሰማዕተ ጽድቅ ዘኢትዮጵያ" ተብለው እንዲጠሩ ቅዱስ ሲኖዶስ ወስኗል።

ጻድቁ በተወለዱበት ሥፍራም በፍቼ ከተማ ግንቦት 1 ቀን 2001 ዓ.ም ጽላት ተቀርጾላቸው ቤተ ክርስቲያን በስማቸው ታንጾላቸው መታሰቢያ ሐውልትም ቆሞላቸዋል።

ያልተነገረላቸው ሰማዕታት ያልተዘመረላቸው ጀግና የደብረ ሊባኖስ ኮከብ ብጹዕ ወቅዱስ አቡነ ጴጥሮስ በረከቶ ይድረሰን።

ዛሬ ያሉ የቤተ ክርስቲያን ልሂቃን ሆይ መንፈሳዊ ጀግንነትን ከአባታችን ይዛችሁ የሀገር አንድነትን አስጠብቁልን የቤተ ክርስቲያን ርስት ጉልትን አትስጡብን።

የእግዚአብሔር ቸርነት የድንግል ማርያም አማላጅነት የአባታችን በረከት ይድረሰን ይደርብን ለዘላለሙ አሜን!

መልዕክት!
ዛሬ ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትር አንድ አባት እንዲህ ብለዋል ብለው ስማቸውን መጥራት ያልፈለጉትና የኢትዮጵያን አንድነትና ኢትዮጵያዊነትን በዚያ ጊዜ ያንጸባረቁበትን ቃል የወሰዱት ከብፁዕ አቡነ ጴጥሮስ እንደሆነ አንባቢ ልብ ይሏል!


ቤተ ተክለ ሃይማኖት
ወኢያኅጥኦሙ እምዘ ፈቀዱ።
አሁኑኑ join ያድርጉ ሁሌ መረጃ ይደርሶታል
@beteteklehaimanot24
734 viewsJERMI, 11:26
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-29 11:55:28 ንኢ ሃቤየ ኦ ድንግል
ምስለ ኤልያስ ወኤልሳእ ነቢይ
ወምስለ እዝራ ሱቱኤል ጽውአ ልቡና ዘአስተዮ ኡርኤል መልአክ
እንኳን አደረሰን
447 viewsJERMI, 08:55
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-22 07:32:22
"መንግሥተ ሰማያት ቀርባለችና ንስሐ ግቡ::"
/(ማቴ ፫:፫/)

እንኳን አደረሰን!!

ዝክረ ቅዱሳን ላልደረሳቸው እናድርስ እናስፋ ስለ ሃገራችን እንጸልይ ንስሃ እንግባ!!

"መንግሥተ ሰማያት ቀርባለችና ንስሐ ግቡ::" /ማቴ ፫:፫/

ዝክረ ቅዱሳንን ተማሩ ብለን እንለምናችኋለን!!

ስለ ንስሃ

ከቅዱስ ሙሴ ጸሊም የምንማራቸው 7 ነገሮች።

፩, ቅዱስ አብረሃምን መምሰል( ፈጣሪውን ተመራምሮ አገኘ)::

፪, ዓለምንና የዓለምን ነገሮች መታው።

፫, የንስሃ ሕይወት( ንስሃን በትጋት መፈጸም)።

፬, መታዘዝ (የሚታዘዘውን ሳያጓድል መስራትን)።

፭, ለሌሎች መኖርን።

፮, በሰው አለመፍረድን።

፯, ትሕትናን።
እነዚህን እናስተውላቸው!!!

ዝክረ ቅዱሳንን ተማሩ ብለን እንለምናችኋለን!!

እናስተውል!!
1፡ ጥሩ ክርስትና ፈጥኖ የሚገኝ አይደለም፡፡ ትእግስትን ይጠይቃል፡፡
2፡ ሰይጣን እኛን ኃጢአት በማሠራት አይረካም፡፡ የሚፈልገው ተስፋ ማስቆረጥ ነው፡፡
3፡ በእምነት የሚደረግ የትኛውም ጸሎት መፍትሔ አለው፡፡
4፡ የበጎ ለውጥ እናት *ዓላማና ቁርጥ ውሳኔ* ናቸው

5 ነገሮችን በደንብ ያዙ።
1, አላማ

2 , እምነት

3, ጥረት

4 ጥንቃቄ

5 ጽናት
=>እነዚህን ያዟቸው ተጠቀሙባቸዉ ኑሯቸው።

ዝክረቅዱሳን (ማኅበረ ቅዱስ ዳዊት)

" ፍቅር ያጌብረኒ ከመ እንግር ዜናሆሙ ለቅዱሳን"::/የቅዱሳንን ዜና(ታሪክ) እንድመሰክር ፍቅር ያስገድደኛል::
አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ /መጽሐፈ ምሥጢር/
https://t.me/zikirekdusn
612 viewsJERMI, 04:32
ክፈት / አስተያየት ይስጡ