Get Mystery Box with random crypto!

ሕይወተ መነኮሳት ወመነኮሳይያት

የቴሌግራም ቻናል አርማ hiwotemenekosat — ሕይወተ መነኮሳት ወመነኮሳይያት
የቴሌግራም ቻናል አርማ hiwotemenekosat — ሕይወተ መነኮሳት ወመነኮሳይያት
የሰርጥ አድራሻ: @hiwotemenekosat
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 940
የሰርጥ መግለጫ

✝በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሕዱ አምላክ አሜን።✝
ይህ ሕይወተ መነኮሳት የተሰኘው ስለ ነገረ ምንኩስና ተባህትዎ የምንነጋገርበት የምንማማርበት የቴሌግራም ቻናል ነው። ኑ እንደ አባቶቻችን በጥብዓት በተባሕትዎ እንኖር ዘንድ ሕይወታቸውን እንመርምር ሥርዓታቸውንም እንማር በፍኖተ አበው እንጓዝ በረከታቸውንም እናግኝ። 🔆 @hiwotemenekosatgroup @hiwotemenekosatbot ሃሳብመስጫ

Ratings & Reviews

2.00

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

0

3 stars

1

2 stars

1

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች

2022-07-27 10:13:10
375 views07:13
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-22 23:49:03
468 views20:49
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-16 00:07:14
አባ እጓለ ብርሃን (ቆሞስ)

በከተማ ውስጥ የነበሩ እውነተኛ አረጋዊ መነኩሴ ከሚወዱት ከፈጣሪያቸው ጋር ይኖሩ ዘንድ ወደ ሰማዩ ቤታቸው ሔደዋል። አባታችንን በአጸደ ገነት ያኑርልን። ቡራኬያቸው ይድረሰን።

@Hiwotemenekosat
503 views21:07
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-01 06:44:22 ሕይወተ መነኮሳት ወመነኮሳይያት pinned «​​#ዝክረ_መነኮሳት #ተሳሕያን_መነኮሳት ቅዱስ ሙሴ ጸሊም ኢትዮጵያዊ °°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°° በዚህች ቀን ሕይወቱ እጅግ ታላቅ የሆነ ሙሴ ጸሊም በሰማዕትነት አረፈ። ይህ ቅዱስ መንግስተ ሰማያትን በኃይል ነው የወሰደው። ልክ ጌታችን በወንጌል እንዳለ:- "...መንግስተ ሰማይ ትገፋለች ግፈኞችም ይናጠቋታል(በኃይል ይወስዷታል")__ማቴ 11:12 ቅዱስ ሙሴ በቀደመው ሕይወቱ…»
03:44
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-01 06:44:14 ​​#ዝክረ_መነኮሳት
#ተሳሕያን_መነኮሳት

ቅዱስ ሙሴ ጸሊም ኢትዮጵያዊ
°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°

በዚህች ቀን ሕይወቱ እጅግ ታላቅ የሆነ ሙሴ ጸሊም በሰማዕትነት አረፈ። ይህ ቅዱስ መንግስተ ሰማያትን በኃይል ነው የወሰደው። ልክ ጌታችን በወንጌል እንዳለ:-

"...መንግስተ ሰማይ ትገፋለች ግፈኞችም ይናጠቋታል(በኃይል ይወስዷታል")__ማቴ 11:12

ቅዱስ ሙሴ በቀደመው ሕይወቱ ፀሐይን ለሚያመልኩ ሰዎች ባሪያ ነበር። አብዝቶ መብላት እና መጠጣት የሚወድ ኃያል ሰው ነበር። በመግደል፣ በመዝረፍ እና በክፋት ስራ ሁሉ ውስጥ ነበር፤ ማንም ሰው በፊቱ ሊቆምም ሆነ ሊቃወመው አይችልም ነበር። ብዙ ጊዜም አይኑን ወደ ፀሐይ አንስቶ "ኦ ፀሐይ አንተ አምላክ ከሆንክ አሳውቀኝ" ይል ነበር። ከዚያም በኋላ "የማላውቅህ ሆይ ራስህን ግለጥልኝ" ይል ነበር።

ከዕለታት አንድ ቀን የሆነ ሰው በገዳም ያሉ አባቶች እውነተኛውን አምላክ ያውቃሉ፣ ወደነርሱም ሂድ ይነግሩኃል ሲል ሰማ። ፈጥኖም ተነሳ ሰይፉን ታጠቀ ወደ አስቄጥስ በረሃ ተጓዘ። አባ ኤስድሮስንም አገኛቸው፣ ባዩትም ጊዜ ስለ አመጣጡ ፈርተው ነበር። ቅዱስ ሙሴ ግን መነኮሳቱ ስለ እውነተኛው አምላክ ለማወቅ እንዲያስተምሩት እንደመጣ ነገሮ አረጋጋቸው። ቅዱስ ኤስድሮስ ወደ አባ መቃሪዮስ ታላቁ ወሰደው፤ እርሱም ሃይማኖት አስተምሮ አጠመቀው። ካመነኮሰው በኃላ በገዳም መኖርን አስተማረው።

ቅዱስ ሙሴ በብዙ አምልኮ መትጋት ጀመረ፣ ከብዙዎቹ ቅዱሳን የበለጠ ጽኑ ተጋድሎን ተጋደለ። ነገር ግን ዲያብሎስ በቀደሙት ልማዶቹ አብዝቶ በመብላት፥ በመጠጥ እና ዝሙት ክፉኛ ተዋጋው። ሁሉንም በተጋድሎው የመጣበትን ነገር ለቅዱስ ኤስድሮስ ይነግረው ነበር። እርሱም ያበረታታዋል፥ የጠላትን ደባ እንዴት እንደሚያሸንፍ ይነግረዋል።

የገዳሙ አረጋውያን በተኙ ጊዜ እንስራቸውን ወስዶ ከገዳሙ ረዥም ርቀት ተጉዞ ውሃ ይቀዳላቸው ነበር። ከብዙ አመታት መንፈሳዊ ትግል በኃላ ሰይጣን ቀንቶበት እግሩን አሳመመው በዚህም የተነሳ አልጋ ቁራኛ አደረገው። ይህም ከሰይጣን መሆኑን ሲያውቅ አምልኮቱን እና ትሕርምቱን ጨመረ፥ በዚህም ሰውነቱ እንደ ተቃጠለ እንጨት ሆነ።

እግዚአብሔር ትዕግስቱን ተመልክቶ ሕመሙን እና መከራውን አራቀለት። የኢየሱስ ክርስቶስ በረከትም በርሱ ላይ ሆነ። ከተወሰነ ጊዜ በኃላ የ500 ወንድሞች አባት እና መንፈሳዊ መሪ ሆነ። እነርሱም ካህን እንዲሆን መርጠውት ነበር። ክህነት ሊቀበል ወደ ፓትርያርኩ ሲመጣ ትዕግስቱን ለመፈተን አረጋውያኑን " ይህን ጥቁር ማነው እዚህ ያመጣው? ከዚህ አውጡት" አሏቸው። ሙሴም ታዞ ወጣ ለራሱም እንዲህ አለ "አንተ ጥቁር ያደረጉልህ ነገር መልካም ነው(የውስጤን ጥቁረት ቢያዩስ ኖሮ እያለ በትህትና)"። ፓትርያርኩም መልሰው ጠርተውት ካህን አድርገው ሾሙት፥ እንዲህም አሉት "ሙሴ አሁን ውስጥህም ውጭህም ነጭ ሆነ"።

ከዕለታት በአንዱ ቀን ከአረጋውያን ጋር ወደ አባ መቃርዮስ ታላቁ ሄደ። እርሱም "ከእናንተ መሃል የሰማዕትነት አክሊል የሚቀበል እንዳለ አያለሁ" አላቸው። ቅዱስ ሙሴም መልሶ "ምናልባት እኔ እሆንን? 'ሰይፍን የሚያነሱ በሰይፍ ይጠፋሉ' ማቴ 26:52 ተብሎ ተጽፏልና። ወደ ገዳሙ ከተመለሱ በኃላ ብዙም ሳይቆይ በርበሮች ገዳሙን አጠቁት። ወንድሞችን "መሸሽ የሚፈልግ ይሽሽ" አላቸው። ወንድሞችም "አንተስ አባታችን ለምን አትሸሽም?" አሉት። እርሱም ይህን ጊዜ(ሰማዕትነቱን) ለረዥም ጊዜያት ሲጠብቀው እንደነበረ ነገራቸው።

በርበሮች ወደ ገዳሙ ገብተው ከሌሎች ሰባት ወንድሞች ጋር ገደሉት። ከወንድሞች አንዱ ተደብቆ ነበር፥ የጌታ መልአክ አክሊል ይዞ እየጠበቀው መሆኑን ሲመለከት ከተደበቀበት ወጥቶ ሰማዕትነትን ተቀበለ።

ተወዳጆች ሆይ በንስሐ ሀይል ላይ ተመሰጡ እንዲሁም ምን እንዳደረገ ተመልከቱ። አንድ አረማዊ፥ ነፍሰ ገዳይ፥ ዘማዊ እና ዘራፊ ባሪያ የነበረን ሰው ወደ ታላቅ አባት፣ መምህር፣ አጽናኝ እና ለመነኮሳት ስርዓትን የጻፈ ካህን እንደለወጠው። ስሙም ዘውትር በጸሎታት ሁሉ ይጠራል። ቅዱስ አጽሙ አሁን በወንድማማቾች ማክሲሞስ እና ዶማዲዮስ ገዳም(ኤል-ባራሙስ) ይገኛል።

ጸሎቱ ከኛ ጋር ትሁን፤ ለእግዚአብሔርም ምስጋና ይሁን፤ ለዘላለሙ አሜን።

@hiwotemenekosat
473 views03:44
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-22 10:24:15 የምንኩስና አንድነት ኑሮን ለመሠረተው ለቅዱሱ አባታችን አባ ጳኩሚስ በዓለ ዕረፍት እንኳን አደረሰን።
ከቅዱሱ ረድኤት በረከት ይክፈለን!


@hiwotemenekosat
763 views07:24
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-22 10:22:01 #ክብረ_መነኮሳት

ጣማፍ ኄራኒ በአባ ጳኩሚየስ የአንድነቱን ሥርዓት እንዴት እንደ ተቀበለች እንዲህ በማለት ነግራናለች:-

"በክብር ጌታ ፊት ተንበረከኩ፡፡ ድንግል እናቱ በቀኝ ቆማለች፡፡ ጌታችንም ሊቀ መልአኩን 'ስለ ገዳማዊ ቀኖና ትረዳ ዘንድ ወደ አባ ጳኩሚየስ ይዘኻት ሂድ ስላለው፣ በረጅም እና ብርሃናማ መተላለፊያ በኩል ይዞኝ ሄደ፡፡ እንደ አልማዝ የሚያበራና በመስቀል የተዋበ ዙፋን አየሁ፡፡ በዙፋኑ ላይ ግርማው የሚያበራ ሰው ተቀምጧል፡፡ የለበሰው ልብስ በወርቅ መስቀሎች ያሸበረቀ እና
ልዩ፣ግሩም፣ ዐይንን የሚማርክ ነው፡፡ በእጁም መስቀል ይዟል፡፡

ሊቀ መልአኩም 'ሂጂና ለአባ ጳኩሚየስ ሰላምታ አቅርቢ' አለኝ፡፡ ስሄድ በመተላለፊያው ግራና ቀኝ በሺዎች የሚቆጠሩ መነኮሳትና መነኮሳይያት ነጭ ለብሰው ቆመዋል..."


*ቀሪውን ከመጽሐፉ እንድታነቡ እናበረታታለን፡፡ መጽሐፉን ከዚህ ቻናል በ'pdf' መልክ አውርደው ይጠቀሙ፡፡

https://t.me/hiwotemenekosatgroup/199


@hiwotemenekosat
620 views07:22
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-21 06:56:08 እንኳን ለቅዱሱ አባታችን አባ አርሳንዮስ በዓለ ዕረፍት አደረሰን።
ከቅዱሱ ረድኤት በረከት ይክፈለን!


@hiwotemenekosat
549 views03:56
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-21 06:50:47 አባ ዳዊት አንድ ጊዜ አርሳንዮስ የነገራቸውን ታሪክ እንዲህ ያወጉናል “እርግጥ አባ አርሳንዮስ ይህንን ታሪክ የተናገረው ሌላ ሰው አደረገው ብሎ ነው፡፡ በርግጥ ግን የታሪኩ ባለቤት እርሱ ራሱ ነው፡፡

አንድ አረጋዊ መነኩሴ ከበኣቱ ወጥቶ ሳለ ‹የሰው ልጆችን ሥራ አሳይህ ዘንድ ና› የሚል ድምፅ ሰማ፡፡ እርሱም ከበኣቱ ወጥቶ የጠራውን ድምፅ ተከትሎ ተጓዘ፡፡ ያ ድምፅ ወደ አንድ ቦታ አደረሰውና አንድ
.ኢትዮጵያዊ እንጨት እየፈለጠ ሲከምር አሳየው፡፡ ያ እንጨት የሚፈልጥ .ኢትዮጵያዊ ሊሸከመው ሞከረና አቃተው፤ ይሁን እንጂ በመቀነስ ፋንታ አሁንም እየቆረጠ መከመር ቀጠለ፡፡

ጥቂት አለፍ ብሎ ደግሞ አንድ ሰው በሐይቅ አጠገብ ቆሞ በተሠበረ ማሰሮ ውኃ ሲቀዳ ተመለከተ፡፡ ማሰሮው የተሰበረ በመሆኑ ውኃው እንደገና ወደ ሐይቁ ይመለስ ነበር፡፡

ያ ድምፅ በድጋሚ ‹ና ሌላ ነገር ደግሞ አሳይሃለሁ› ብሎ ወሰደው፡፡

በአንድ ሥፍራ ላይ መቅደስ አሳየው፡፡ ሁለት ሰዎች በፈረስ ጐን ለጐን ሆነው መጡ፡፡ በትከሻቸውም በትራቸውን ጫፍና ጫፍ ላይ አጋድመው ይዘውት ነበር፡፡ በበሩ ወደ ውስጥ ሊያልፉ ቢፈልጉም በትራቸውን አግድም ስለያዙት ያግዳቸው ነበር፡፡ አንዳቸውም ከሌላኛው ኋላ በመሆን በትሩን ፊትና ኋላ አድርገው ሊገቡ አልፈለጉም፡፡ስለዚህም በፉክክር ከውጭ ቀሩ፡፡

ያ ድምፅ ለዚያ አረጋዊ አባት
እንዲህ አለው፡፡ ‹እነዚህ ሰዎች የጽድቅን ቀንበር በትዕቢት ተሸክመውታል፣ ራሳቸውን ዝቅ ዝቅ አላደረጉም፤ ራሳቸውን ለማረምና በክርስቶስ የትኅትና ጉዞ ለመጓዝ አልፈለጉም፣ ስለዚህም ከመንግሥተ ሰማያት በአፍኣ (በውጭ) ይቀራሉ፡፡

እንጨት የሚቆርጠው ሰውም በኃጢአት ላይ ኃጢአት የሚጨምርን ሰው ይመስላል፡፡ ንስሐ ከመግባት ይልቅ ሌሎች ኃጢኣቶችን እንደገና ይጨምራል፡፡

ውኃ የሚቀዳውም ሰው መልካም ሥራን የሚሠራ ሰውን ይመስላል፣ ነገር ግን መልካም ሥራው ከክፉ ሥራው ጋር የተቀላቀለ በመሆኑ ጥቂቱ መልካሙ ሥራው ይበላሽበታል ።

ስለሆነም እያንዳንዱ ለሚሠራው ነገር ሊጠነቀቅና በከንቱ እንዳይደክም ሊያስብበት ይገባል› አለው፡፡ ”

ከቅዱሱ አባታችን አባ አርሳንዮስ ረድኤት በረከት ይክፈለን!

ዋቢ ፡- በበረሃው ጉያ ውስጥ መጽሐፍ - በዲያቆን ዳንኤል ክብረት


@hiwotemenekosat
480 views03:50
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-21 00:57:11 የሀይማኖት ትርጉም

የጋሽ ግርማ ከበደ ትምህርት

@Hiwotemenkosat
412 viewsedited  21:57
ክፈት / አስተያየት ይስጡ