Get Mystery Box with random crypto!

Sᴀᴍɪ Tech™

የቴሌግራም ቻናል አርማ samitechew — Sᴀᴍɪ Tech™ S
የቴሌግራም ቻናል አርማ samitechew — Sᴀᴍɪ Tech™
የሰርጥ አድራሻ: @samitechew
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 9.48K
የሰርጥ መግለጫ

⬇️IN THIS CHANNEL
➡️ Games
➡️ ÅPPS
➡️ Tech news
➡️ Social media Hacking
➡️ Termux tool
For apps ➡️t.me/habeshaapps
🈯️የYoutube channel :https://youtube.com/channel/UCQv4geRfZgH6944QjdWU6Og

Ratings & Reviews

3.67

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

0

3 stars

2

2 stars

0

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች

2022-12-09 20:14:13
ቴሌብር ያለምንም ዋስትና ብድር እሰጣለሁ ብሎ ቴሌብር መላ እና ቴሌብር እንደኪሴ ሚባል System ለደንበኞቹ እንደጀመር አይርሳም። እና ብር የጠረረበት የኛ ወጣትም አይኑን ሳያሽ የቻለውን ያክል እየተበደረ ነው። አብዛኛው ተበዳሪ መልሶ ለመክፈል ሳይሆን "ምን ያመጣሉ? መቼስ ይሄ ሁሉ ሺ ሰው አያስሩም" ብሎ አስቦ ነው የተበደረው።

ብድሩን ያመቻቸው ዳሽን ባንክ ደግሞ ብድሩ በጊዜው ካልተመለሰልኝ በሕጋዊ መንገድ እጠይቃለሁ ብሏል።
እና ምን ልላችሁ ነው በቀጣይ ሦስት ወራት ወይ በአስር ሺዎች ሚቆጠሩ ወጣቶች ሸቤ ሲወርዱ እናያለን ወይ ደግሞ ዳሸን ባንክ ያ ሁሉ ብር ሲከስር እናያለን

ጎበዝ ከዚህ በላይ አጓጊ ርዕስ የት ይገኛል
Join & Share
::@samitech0
፡@Samitech0
975 viewsedited  17:14
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-11-22 20:14:45 የባትሪ እድሜ (Battery life)

በዚህ ዘመን በርካቶች የዘመናዊ ተንቀሳቃሽ ስልክ ተጠቃሚዎች መሆናቸው ይታመናል። ዘመናዊ ስልኮች ከስሪታቸው አንጻር ባትሪያቸው ቶሎ የሚያልቅና አጭር ጊዜን የሚያስጠቅሙ ናቸው። ከዚህ አንጻርም ተጠቃሚዎች ባትሪውን ቶሎ ቶሎ ሃይል ለመሙላት (ቻርጅ ለማድረግ) ሲሞክሩ ይስተዋላል። ይህ ሁኔታ ደግሞ ምናልባትም የባትሪን እድሜ ሊያሳጥር እና ሙሉ በሙሉ ሊያበላሸውም ይችላል።

ስልክን ከመጠቀም ባለፈ ግን የባትሪ እድሜን ማራዘምና በአግባቡ ቻርጅ በማድረግ መጠቀም ቅድሚያ የሚሰጠው ጉዳይ ነው። እርስዎ ከእነዚህ ተጠቃሚዎች አንዱ ከሆኑ ስልክዎን ቻርጅ በሚያደርጉበት ጊዜ ምናልባት ያላስተዋሏቸው ነገሮች ይኖራሉና እነዚህን የባለሙያ ሃሳቦች እናካፍልዎ፡

ቻርጅ እያደረጉ ስልክን በጭራሽ አለመጠቀም፦

አንዳንድ ጊዜ አስቸኳይ ጉዳይ ቢያጋጥም እንኳን ስልክን ቻርጅ እያደረጉ ባይጠቀሙ ይመረጣል። ምናልባት የግድ ከሆነ ደግሞ ስልኩ ከተሰራበት ኩባንያ አብሮ የተዘጋጀን ቻርጀር እየተጠቀሙ ቢሆን ይመረጣል ይላሉ ባለሙያዎች።

ጥራት ያላቸውን ባለማራዘሚያ ቻርጀሮች መጠቀም፦

ባለማራዘሚያና በአብዛኛው በነጭ መደብ የተሰሩ እውነተኛ ቻርጀሮችን መጠቀም የባትሪን እድሜ ለማራዘም ይረዳልና ይጠቀሙበት።

ሌሊቱን ሙሉ ቻርጅ ከማድረግ መቆጠብ፦

ወደ መኝታ ሲያመሩ ስልክዎን ቻርጀር ላይ ሰክቶ መተው አደጋ አለው። ይህም ባትሪው ከመጠን በላይ ቻርጅ በማድረግ ማዳከም ይጀምራል፥ በአብዛኛው ስልክን በ40 እና በ80 ፐርሰንት መካከል ቻርጅ ማድረግ መልካም መሆኑንም ይመክራሉ። ምክንያታቸው ደግሞ 40 ፐርሰንት ከደረሰ ቻርጅ ማድረጉ ግዴታ ሲሆን 80 ከሆነ በኋላ ነቅለው ቢገለገሉበት ችግር የለውም የሚል ነው።

ስልክን ለተወሰነ ጊዜ ማጥፋት፦

ሰው ሰርቶ ማረፍ እንደሚፈልገው ሁሉ ስልክን ማጥፋትም ለባትሪው መልካም እንደሆነ ነው ባለሙያዎች የሚገልጹት። ለዚህ ደግሞ ቢያንስ በሳምንት አንድ ቀን በተለይም ወደ መኝታ ሲያመሩ በማጥፋት እረፍት መስጠት። ይህ ሲሆን ደግሞ የስልኩ ባትሪ እድሜ እንዳያጥርና ረዘም ላለ ጊዜ እንዲያገለግልዎ ይረዳል።

ባትሪው እስከሚያልቅ ጠብቆ ቻርጅ አለማድረግ፦

ሌላውና በብዙ ሰዎች የተለመደው ጉዳይ ደግሞ የስልክ ባትሪ እስከሚያልቅ ጠብቆ ቻርጅ ማድረግ ነው። ይህ ደግሞ ለባትሪ እድሜ የመጀመሪያውና ዋናው ጠር ነውና ባትሪው 40 ፐርሰንት ላይ ሲደርስ ቻርጅ ማድረጉን ይመክራሉ። ይህ ባይሆን እና በጣም ከወረደ በኋላ ቻርጅ ለማድረግ መሞከሩ ግን ባትሪን በመግደል ከፍተኛ ጉዳት ያስከትላልና ይህን ልማድ ያስወግዱም ይላሉ።

ከዚህ ባለፈም ቻርጀሩን ከቀጥተኛው ሶኬት ላይ አለመሰካት እና ከፍተኛ ሙቀት ባላቸው ቻርጀሮች አለመጠቀም መልካም ነው። እርስዎም ከላይ የተጠቀሱትን የባለሙያ ምክረ ሃሳቦች በመተግበር የስልክዎን ባትሪ እድሜ ያራዝሙ።

Join & Share
::
@samitech0
@Samitech0
6.3K views17:14
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-11-12 22:24:47 ስልክ እየደወሉ እና የተለያዩ የማጭበርበር ዘዴዎችን በመጠቀም ወንጀል ከሚፈፅሙ ግለሰቦች ተጠንቀቁ  ሲል የአዲስ አበባ ፖሊስ አሳሰበ፡፡

ስልክ እየደወሉ እና የተለያዩ የማጭበርበር ዘዴዎችን በመጠቀም ወንጀሎችን የሚፈፅሙ ግለሰቦች መኖራቸውን ህብረተሰቡ ተገንዝቦ ተገቢውን ጥንቃቄ እንዲያደርግ የአዲስ አበባ ፖሊስ አስታዉቋል።

“በአዲስ አበባ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በተለያዩ ስልኮች እየተደወለ እንኳን ደስ አላችሁ ሎተሪ ደርሷችኋል ፣ሲስተም እያስተካከልን ነው፣ የሞባይሎትን አቅም ከ4G ወደ 5G እየቀየርን ነው ፣ከሌሎች ባንኮች ጋር ኦንላይን ሲስተም እየጀመርን ነው” በሚሉ እና በሌሎች ማደናገሪያዎች በመጠቀም የተለያዩ ግለሰቦች የማጭበርበር ወንጀል እየተፈፀመባቸው እንደሚገኝ የአዲስ አበባ ፖሊስ አስታውቋል።

ፖሊስ የምርመራ መዛግብቶችን ዋቢ አድርጎ እንደገለጸው አንዳንዶቹ የማጭበርበሪያ ስልቶች ግለሰቦች እንዲያምኑ በኤቲኤምም ገንዘብ ያወጡበት ትክክለኛ ቀን ተነግሯቸው የወንጀሉ ሰለባ እየሆኑ የሚገኙ ሲሆን የግለሰቦች የባንክ ሚስጥር የሚወጣበትን ሁኔታ ለማረጋገጥ ምርመራው ተጠናክሮ ቀጥሏል።

ወንጀሉ በልዩ ልዩ የአፈፃፀም ስልቶች እየተፈፀመ ከመሆኑም ባሻገር ስልክ በመንጠቅና ቴክኒካል የሆኑ ዘዴዎችን በመጠቀም የግለሰቦችን የባንክ አካውንት ወደ ቴሌ ብር በማስተላለፍ ወንጀሉ እየተፈፀመ ይገኛል።

ፖሊስ አያይዞ እንደጠቀሰው ወንጀሉን ለመከላከል ህብረተሰቡ ተገቢውን ጥንቃቄ እንዲያደርግ በኢትዮ ቴሌኮም በኩል የተለያዩ የማስጠንቀቂያ መልዕክቶች ቢተላለፉም አሁንም ወንጀሉ እየተፈፀመ ሲሆን ግለሰቦች የማያውቋቸው የስልክ ጥሪዎች እና የጹሁፍ መልዕክቶች ሲደርሷቸው ተገቢውን ማጣራት ማድረግ እንደሚገባቸው እና ጥሪው እንደደረሳቸው ወደ ተግባር ከመግባታው በፊት አቅራቢያቸው ወደሚገኝ ባንክ በመሔድ እውነታውን ማረጋገጥ እንደሚገባ ፖሊስ መልዕክት አስተላልፏል።

ፖሊስ መሰል ወንጀሎችን ለመቆጣጠር ከሚሰራው ሥራ ባሻገር አጠራጣሪ ነገሮች ሲያጋጥሙ መረጃውን ለፀጥታ አካላት በመስጠት ህብረተሰቡ ተባባሪ እንዲሆንም የአዲስ አበባ ፖሊስ ጥሪውን አስተላልፏል።

Join & Share
::
@samitech0
@Samitech0
6.9K views19:24
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-11-02 21:39:47 ቪፒኤን ለምን እንጠቀማለን? ጥቅሙስ ምንድን ነው?

ቪፒኤን (VPN) የኢንተርኔት ግንኙነታችንን ደህንነቱ የተጠበቀ እንዲሆን እና የምንለዋወጣቸዉ መረጃዎች ከመረጃ በርባሪዎች ጥቃት የተጠበቁ እንዲሆኑ የሚረዳ ሶፍትዌር ነው፡፡

ተጠቃሚዎች የቪፒኤን ግንኙነት ሲፈጥሩ ደህንነቱ የተረጋገጠ የመረጃ መተላለፊያ መንገድ ይፈጥራሉ፡፡
ቪፒኤን በተለየ ማስተላለፊያ መንገድ የሚተላለፉ ዳታዎችን ሚስጥራዊ የሚያደርግ በመሆኑ ማንኛዉም የመረጃ በርባሪ የመረጃዉን ይዘት ማዎቅ እንዳይችል ከማድረጉ ባሻገር የመረጃ ግንኙነቱ የሚሆነዉ በሁለቱ ባለመብት(ባለፍቃድ) አካላት ብቻ ነዉ፡፡

ሶፍትዌ የቀጥታ የበይነ-መረብ ግንኙነት 'የኦንላይን' እንቅስቃሴ በመደበቅ እንዲሁም እንዳይታይ በማድረግ(የትኛዉን ድረ-ገጽ እንደጎበኘን እና ምን አይነት ዳታዎችን እያስተላለፍን መሆኑን) ባለማሳዎቅ ያግዘናል፡፡

ይህን አገልግሎት በተገቢው መንገድ ማግኘት የምንችለው ደግሞ የቪፒኤን ሶፍትዌር ደንበኛ በመሆን አገልግሎቱን መጠቀም ስንጀምር ነዉ፡፡

ደንበኛ በመሆናችን የምናስተላልፋቸዉ ዳታዎች ከመዳረሻዉ ኔትወርክ ከመድረሳቸዉ በፊት ይመሰጠራሉ፡፡

ቪፒኤንን ለምን መጠቀም አስፈለገ?

ማንኛዉንም የዌብ ተግባራት ኢንክሪፕትድ(የተመሰጠሩ) እንዲሆኑ ያደርጋል።

የቀጥታ የበይነመረብ ግንኙነት (online) ተግባራችንን በመደበቅ ከሚከታተሉን የመረጃ መንታፊዎች ያድነናል፡፡

መዳረሻችንን በግልፅ እንዳይታይ እንዲሁም በቦታ የተገደቡ ዌቦችና ይዘቶችን አገልግሎት ማግኘት እንድንችል ይረዳናል።

በዌብ(በይነ-መረብ) ተግባር ላይ የማንነት መታዎቅ አጋጣሚን በእጅጉ ያጠባል።

የህዝብ ዋይፋይ ሆትስፖቶችን በምንጠቀምበት ጊዜ ግንኙነቱ ደህንነቱ የተጠበቀ እንዲሆን ያደርግልናል፡፡

Join & Share
::
@samitech0
@Samitech0
5.8K viewsedited  18:39
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-10-19 16:37:06 ይሄ አጠቃላይ የ Dark web Link የያዘ TXT ነው!

ሁሉም በየራሳቸው ረድፍ ነው ያሉት ስለ Hack ከፈለጋቹ Hack & Technology ከሚለው ስር ባሉ Link ተጠቀሙ!!

እነዚን ነገሮች ማድረግ እንዳትረሱ

1ኛ :- በምንም ተዓምር VPN ሳታገናኙ ወደ dark web እንዳትገቡ

2ኛ :- በምንም ተዓምር የስልካቹን ሆነ ወደ Dark web የምትገቡበትን Device Camera ሳትሸፍኑ እንዳገቡ

3ኛ :- ጥሩ ነገር ለማግኘት ከገባቹ ታገኛላቹ ካለበለዚያ ዘግናኝ ዘግናኝ Video ነው ምታገኙት!!

Join & Share
::@samitech0
፡@Samitech0
9.3K viewsedited  13:37
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-10-18 21:23:22 ቴሌግራም አለሰራ ያለቹ ካታች ያለውን ሊንክ ነክተው connect proxy ይጫኑ

Server: Unknown
Port: 443
Secret: 7gAAAAAAAAAAAAAAAAAAAAF3d3cuZ29vZ2xlLmNvbQ


Join & Share
::@samitech0
፡@Samitech0
7.2K viewsedited  18:23
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-10-08 10:31:12 Hi guys am back with new tiktok video and if there anything that u want to ask am open
8.1K viewsedited  07:31
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-20 13:23:13
PRIME VIDEO,NETFLIX,DISNEY ACCOUNT ለምትፈልጉ

በመጀመሪያ ይህንን LINK በመንካት https://t.me/Nathan_generator_bot?start=1737569926 ቦቱን START ትላላችሁ።

በቀጣይ የሚመጡላችሁን 3የTELEGRAM  ቻናሎች JOIN ብላችሁ CHECK የሚለዉን ትነካላችሁ ።

ከዛም REFERRAL የሚለዉን ትነካላችሁ ያን ጊዜ የናንተን INVITE LINK ይሰጣችኋል።ከዛ በኋላም የራሳችሁን ሊኒክ SHARE እያረጋችሁ ነጥብ በመሠብሠብ WITHDRAW ማድረግ ነዉ።

ቻናሎቹን LEAVE ካላቹ ነጥባችሁ በሙሉ ይቀነሳል!!

Join & Share
::@samitech0
፡@Samitech0
8.0K views10:23
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-16 14:25:06 ኮምፒተራችንን ከጥቃት ለመ ከላከል አንቲቫይረስ እንደምንጠቀመው ሁሉ ለኢንተርኔት ደህንነታችንስ ምን እንጠቀማለን

ዛሬ ስለ
#VPN በጥቂቱ እናወራለን፡፡

#VPN (Virtual private netowrk) የተለያዩ የግልና የጋራ ኔትወርኮችን (እንደ wifi hotspot ና ኢንተርኔት) ያሉ ኔትወርኮችን ደህንነታቸውን የተጠበቀ ለማድረግ ይረዳል፡፡ ይህም የኢንተርኔት ማንነታችንን ከጠላፊዎች (hackers) የተጠበቀ ያደርገዋል፡፡

#VPN አገልግሎት ለመስጠት በዋነኝነት የሚከተሉት ክፍሎች ሊኖሩት ይገባል፡፡

VPN server ፡- በ
#vpn ባለቤቱ የሚዘጋጁ በተለያዩ ሀገራት ና ከተሞች የሚገኝ ሰርቨር

vpn protocol፡- መተላለፊያውን (tunnel) ለመፍጠር

Encryption፡- አየር ላይ ያለን መረጃ ሚስጥራዊ  ለማድረግ
ይህም ጥሩ protocol በመጠቀም አስተማማኝ የሆነ መተላለፊያ በመፍጠር የተጠቃሚውን ግንኙነት አመስጥሮ (encrypt) ደህንነቱን ያስጠብቃል፡፡

እንዴት ይሰራል

vpn የራሱ የሆነ የሰርቨር ቦታዎች (locations like uk,sweden france and usa...) ስለዚህ የተጠቃሚውን IP በመቀየር (በመደበቅ) ሰርቨሩ ሌላ
#IP ያዘጋጅለታል፡፡

እናም እናንተ
#ኢትዮጵያ ሁናችሁ vpn ሰርቨሩ በሰጣችሁ IP አማካኝነት UK ወይም  france ሁናችሁ እየተጠቀማችሁ እንደሆነ የሚያስችል ቴክኖሎጂ ነው፡፡

እንዲሁም የሆነ ዌብሳይት እየጎበኛችሁ ቢሆን በእናንተ አዲስ IP ና በሳይቱ  መካከል መተላለፊያ (tunnel) በመፍጠር መረጃዎች በመተላለፊው አንዲጓጓዙ ና ሚስጢራዊ እንዲሆኑ ያደርጋል፡፡

Generally
#VPN can

avoid your orginal IP and replace with anonymous IP

encrypts your data
avoid censorship and georestriction

access websites and apps from anywhere at any time.

Join & Share
:@samitech0
፡@Samitech0
6.7K views11:25
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-15 14:22:01 የኮምፒውተር ኪቦርዳችን ላይ ከላይ የሚገኙትን (F1-F12) በተኖች ጥቅማቸውን ያውቁ ኖሯል?

➢ካላወቃችሁ አትጨነቁ!! ዛሬ የተወሰነ ጥቅማቸውን እናሳያችኋለን፡፡ እነዚህን የኪይቦርድ በተኖች ከዚህ በፊት ድምፅ ለመጨመር እንዲሁም የብርሃን መጠን ለማስተካከል ተጥቀምውባቸው ይሆናል፡፡

➢ነገር ግን ጥቅማቸው ከዚህ ከፍ ያለ ነው  ሁሉም ኮምፒውተር በሚያስብል ሁኔታ እነዚህን በተኖች ይዞ ነው የሚመጣው፡፡ እና ምንም ማስተካከል ሳያስፈልግ መጠቀም እንችላለን። ይሁን እንጂ አንዳንድ ኮምፒውተሮች ላይ እነዚህን በተኖች ለመጠቀም FN የሚለውን በተን በቅድሚያ መንካት አለብን::

❖ከF1 እስከ F12 ያሉትን በተኖች ጥቅም አንድ በአንድ ከስር ዘርዝረናል ....



       የ F1 ጥቅሞች
► ከ”Windows ቁልፍ (button) ጋር በጋራ ስንነካው help menuን ያመጣልናል፡፡
► Excel እና Word በምንጠቀምበት ወቅት ከ Control ጋር በጋራ ስንነካው Hides or displays ribbon menu ያደርግልናል፡፡

       የ F2 ጥቅሞች
◕ Alt + Ctrl + F2 - opens Document Library in Microsoft Office
◕ Allows you to edit the selected folder or file name in Windows Explorer

       የ F3 ጥቅሞች
► Opens search feature in Windows Explorer
► Shift + F3 - lets you change from lowercase to uppercase to all caps in Word
► Opens find feature in Firefox and Chrome

       የ F4 ጥቅሞች
◕ Alt + F4 closes window
◕ Places the cursor in the address bar in Explorer

       የ F5 ጥቅሞች
► Starts slideshow in Power Point
► Refreshes Internet browser pages
► Opens Find and Replace in Microsoft Office

       የ F6 ጥቅሞች
◕ Goes to the next page in a split screen in Microsoft Word
◕ Ctrl + F6 lets you easily switch between Word documents

       የ F7 ጥቅሞች
► Alt + F7 does a spelling and grammar check in Microsoft Word
► Shift + F7 open Thesaurus in Microsoft Word

       የ F8 ጥቅሞች
◕ In Excel, enables extend mode for arrow keys
◕ Enables safe mode in Windows

       የ F9 ጥቅሞች
► Ctrl + F9 inserts empty fields into Word
► Updates fields in Word

       የ F10 ጥቅሞች
◕ Opens menu bar
◕ Ctrl + F10 maximizes window in Word
◕ Shift + F10 does the same thing as a right click

       የ F11 ጥቅሞች
► Exits and enter full screen mode in browsers
► Shift + F11 adds a new spreadsheet in Excel

       የ F12 ጥቅሞች
◕ Opens Save As in Word
◕ Shift + F12 saves Word document
◕ Ctrl + F12 opens Word document


Join & Share
:
@samitech0
@Samitech0
5.5K views11:22
ክፈት / አስተያየት ይስጡ