Get Mystery Box with random crypto!

የደ/ፀ/ሳ/ቅ/ጊዮርጊስ አጥቢያ የጥምቀት ተመላሽ ወጣቶችና ጎልማሶች መንፈሳዊ ማኅበር

የቴሌግራም ቻናል አርማ saloyouth — የደ/ፀ/ሳ/ቅ/ጊዮርጊስ አጥቢያ የጥምቀት ተመላሽ ወጣቶችና ጎልማሶች መንፈሳዊ ማኅበር
የቴሌግራም ቻናል አርማ saloyouth — የደ/ፀ/ሳ/ቅ/ጊዮርጊስ አጥቢያ የጥምቀት ተመላሽ ወጣቶችና ጎልማሶች መንፈሳዊ ማኅበር
የሰርጥ አድራሻ: @saloyouth
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 209
የሰርጥ መግለጫ

ዓላማችን ቤተከርስቲያን ማገልገልና በጎ አድራጎት ስራ መስራት እንዲሁም መንፈሳዊ ጉዞና መንፈሳዊ ሕይወታችንን የምናሳድግበት ነው ።

Ratings & Reviews

3.33

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

0

3 stars

1

2 stars

1

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች

2022-05-20 22:30:13
ቅዱስ ዮሐንስ አፈ ወርቅ እንዲህ አለ

"በምሰብክበት ጊዜ ስታጨበጭቡልኝ ሰው እንደመሆኔ በዚያ ቅጽበት ደስታና መደነቅ ይሰማኛል ወደ ቤቴ ሔጄ ያጨበጨቡልኝ ሰዎች ምንም ጥቅም እንዳላገኙ ሳስብ ግን ንግግሬ ሁሉ በከንቱ እንደቀረ ይሰማኛል፤ ስለዚህ ማጨብጨባችሁን የሚከለክልና ዝም ብላችሁ እንድትሰሙኝ ብቻ የሚያደርግ ሕግ ስለማስቀመጥ አስባለሁ" (On His Message 80)

“ቤት ውስጥ የእንግዳ ማረፊያ ቤት ይኑርህ አልጋ አዘጋጅ ጠረጴዛና መቅረዝም ይኑረው ክርስቶስ ሊመጣና ሊያርፍበት የሚችልበት ክፍል አዘጋጅና "ይህ የክርስቶስ ክፍል ነው" በል ምድር ቤት ያለ ትንሽ ክፍልም ቢሆን እሱ አይንቀውም፤ ዕርቃኑን የሆነው እንግዳ የሚፈልገው መጠለያ ብቻ ነው" (On Acts Homily 40.2)

“ለሞቱት ብቻ አናልቅስ፤ በቆሙት ብቻም አንደሰት ታዲያ ምን እናድርግ? ለኃጢአተኞች በሞቱ ጊዜ ብቻ ሳይሆን በቁማቸውም እናልቅስ፤ ስለ ጻድቃን ደግሞ በቁማቸው ብቻ ሳይሆን በሞቱም ጊዜ ደስ ይበለን ምክንያቱም ኃጢአተኞች ቆመውም ሞተዋል፤ ጻድቃን ግን ሞተውም ሕያዋን ናቸው" (On Phil. 3)

"ጴጥሮስ አለቀሰ ማልቀስ ብቻ ሳይሆን ምርር ብሎ አለቀሰ፤ ከዓይኑ በፈሰሰው ዕንባ ድጋሚ ተጠመቀ አምርሮ በማልቀሱም በዕንባው ኃጢአቱን አጠበ አንተም እንዲሁ አድርግ" (Paent 3.4)

“ንብ ከሌሎች እንስሳት ሁሉ ትከበራለች፤ የምትከበረው ታታሪ ሠራተኛ በመሆንዋ ሳይሆን የምትሠራው ለሌሎች በመትረፉ ነው"

ምንጭ
ዲያቆን ሄኖክ ኃይሌ
ግንቦት 12 2014 ዓ.ም
39 viewsAshe abdo, 19:30
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-03 07:30:19 "ዉሎህን/ሽን ቃኝ"

❖ አንድ ቀን ዝንብና ንብ እያወሩ በወሪያቸው መሀል ዝንብ ንብን እንዲህ ስትል ጠየቀቻት
"ንብ ሆይ ለምንድነው የሰው ልጆች እኔን የሚጠሉኝ? ለምንስ ነው የሚጸየፉኝ?
ቤታቸው ስገባ ያባርሩኛል ይገድሉኛል፤ የሚጠጡት ነገር ላይ ከተገኘሁ ይደፉታል የሚበሉት ነገር ላይ ካረፍኩ ያረፍኩበትን ቦታ ያለውን እህል ቆርሰው ይጥሉታል::

❖ አንቺን ግን እንደ እኔ አይገፉሽም እንደውም ቤታቸው ስትገቢ ይንከባከቡሻል ደግሞም መልካም ነገርን ተስፋ በማድረግ ደስታቸው እጥፍ ነው ለምንድነው?" ስትል ዝንብ ንብን ጥያቄዋን አቀረበች በዚህ ጊዜ ንብ እንዲህ አለቻት "ውሎሽ የት ነው?" እንግዲህ እዚህ ጋር ቆም እንበል፣
ሰው ጠላን፣ ገፋን፣ ናቀን እያልን እንደ ዝንቧ ጥያቄን አዝለን ከምንጓዝ ውሏችንን በደንብ እንይ መቼም ማንም በጤፍ ማሳ ላይ ስንዴን አይጠበቅም፤ ስለዚህ ምንጊዜም ውድቀታችንን ለማረምም ይሁን ብርታታችንን ለማብዛት ውሏችንን እንቃኝ።
181 viewsAshe abdo, 04:30
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-01 21:50:37 እስኪ ንገሩኝ! ክርስቲያንን ክርስቲያን ከሚያስብሉት ነገሮች እጅግ የራቃችሁ ኾናችሁ እያለ ክርስቲያን መሆናችሁን መለየት የምችለው በምንድነው? ክርስቲያን መባላችሁ ይቅርና ሰው ብዬ ልጠራችሁ የምችለውስ እንዴት ነው? እንደ አህያ ትራገጣላችሁ፣ እንደ ኮርማ ትሴስናላችሁ፣ እንደ ፈረስ ከሴቶች ኋላ ታሽካካላችሁ፣ እንደ ድብ ሆዳም ናችሁ፣ እንደ ግመል ቂም ትይዛላችሁ፣ እንደ ተኩላ ትነጥቃላችሁ፣ እንደ እባብ ትቆጣላችሁ፣ እንደ ጊንጥ ትናደፋላችሁ፣ እንደ ቀበሮ ተንኮለኛ ናችሁ፣ እንደ ክፉ ጋኔንም ከወንድማችሁ ጋር ትጣላላችሁና። ታድያ ክርስቲያን የሚለውስ ይቅርና በምናችሁ ሰው ብዬ ልጥራችሁ?? ሰው የሚያስብል ምልክት ሳይኖራችሁ እንዴት ብዬ ከሰው ዘንድ ልቁጠራችሁ??
ታድያ ምን ብዬ ልጥራችሁ የዱር አውሬ ልጥራችሁ? እንዲህስ አልላችሁም፣ ጭካኔያችሁ ከዱር አራዊት በላይ ነውና በሌላ መልኩ ደግሞ እነርሱ እንደዚያ የኹኑት ከተፈጥሮአቸው የተነሳ እንጂ እንደ አናንተ ወደውና ፈቅደው አይደለምና። ታድያ ምን ብዬ ልጥራቸሁ? ጋኔን ልበላችሁ? እንዲህስ አልላችሁም ምክንያቱም ጋኔን የሆድ ባርያ አይደለምና ፍቅረ ንዋይም የለበትምና። ታድያ ከዱር አራዊትም ከአጋንንትም የሚብስ ክፉ ግብር ከያዛችሁ ንገሩኝ ሰው ብዬ እጠራችሁ ዘንድ ይገባኛልን? ሰው እንኳን ለመባል የሚበቃ ምግባር ከሌላችሁስ ክርስቲያን ብለን ልንጠራችሁ የምንችለው እንዴት ነው???
ቅዱስ ዮሀንስ አፈወርቅ
171 viewsAshe abdo, 18:50
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-04-30 19:50:54 ነገ ሚያዚያ 23 ቀን 2014 ዓ.ም. በመላው ዓለም በሁሉም አጥቢያ ቤተ ክርስቲያን በመገኘት  #ከቅዳሴ_በኃላ_በሁሉም_አጥብያ_ከሥር_ያሉትን_መፈክሮች_እናሰማ።(በኮምፒተር ተጽፈው፤በባነር ይዘጋጁ።በቅድስት ቤተ-ክርስትያናችን ሁነን ድምጻችን እናሰማ።


☞ የኦርቶዶክሳውያንን ደም በማፍሰስ የሚጸና ወንበር የለም!
☞ በአፍጥር ስም እየተካሔደ ያለው መንግሥታዎ አሻጥር ይቁም
☞በሥልጤ ኦርቶዶክሳውያን ላይ የተፈጸነው ስቃይ ስቃያችን ነው!
☞ኢትዮጵያን የኦርቶዶክሳውያን የመከራ ቋት ማድረግ ይብቃ
☞ኦርቶዶክሳዊነትን እና ኦርቶዶክሳውያ አሻራን ማጥፋት ይቁም!
☞ አባቶቻችን አታስገድሉን!
☞ የቤተ ክርስቲያን አባቶች ዝምታ ይብቃ
☞ አማራን እና ተጋሩን በማጋደልቤተ ክርስቲያንን ለማዳከም የሚደረገው ሴራ ገብቶናል!
☞ የኦርቶዶክሳውያን ትዕግሥት ወሰን አለው!
☞ መንግሥት ሆይየአዛኝ ቅቤ አንጓች አስመሳይነትህን አቁም!
☞ ለኦርቶዶክሳውያን ከችግኝ ያነሰ ዋጋ መስጠት ይቁም
☞ በኦርቶዶክሳውያን ላይ የሚፈጸም ሥርዐታዊና መዋቅራዊ ጥቃት ይቁም!
☞ ፍትሕ በወራቤ በግፍ ለተጎዱ ኦርቶዶክሳውያን!
☞ አጥቅተውን ተጠቃን ብለው የጥላቻ ንግግር በሚያሰራጩ ጽንፈኞች ላይ መንግሥት እርምጃ ይውሰድ!
የሚሉ መፈክሮችን እናሰማ።share!!!ለምታውቋቸው ኦርቶዶክሳውያን inbox ላኩላቸው!!!
https://t.me/BetMetsahfte
255 viewsAshe abdo, 16:50
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-04-28 22:44:04
"…ቪድዮውን እስከመጨረሻው እዩት።

"…ጎንደር ላይ ነው። በሰሞኑ ግርግር መስቀል አድርጎ በሰፈራቸው የሚያልፍን ምስኪኑን ጎንደሬ በድንጋይ፣ በፌሮ በብረት ቀጥቅጠው፣ በገጀራ ፈልጠው ከገደሉት በኋላ አልረካ ብለው እንኳ አስከሬኑን ሲቀጠቅጡት ይታያል። በቪድዮው ላይ አንዳንድ ሙስሊሞች ተውተው አስከሬን አትምቱ ሲሉም ይታያል።

"…በዚህ ሁከት 5 ኦርቶዶክሳውያን ዐማሮች ተቀጥቅጠው በገጀራ ተከትፈው ተሰውተዋል። ግን ማን ይጩህላቸው? በዛሬው ዕለት የሙስሊሞቹን አስከሬን የጎንደር ከተማ አስተዳደር በክብር ይቀብሩ ዘንድ የሰጣቸው ሲሆን ኦርቶዶክሳውያኑን ግን ጥፉ ከዚህ ብሏቸዋል። ማን ይጩህላቸው።

"…እነሱ በጩኸት ሃገር ቀውጢ ሲያደርጉ የእኛዎቹ ግን በዝምታ ነገሩን በትዝብት ያዩታል። መጅሊሱ ባልተጣራ ነገር ሃገር ይያዝ ሲል ሲኖዶሱ ጭራሽ የት እንደገባ ፈጣሪ ይወቅ። ከዴይሊ ግብፅ እስከ አልጀዚራ አጀንዳውን ሲያጮሁላቸው፣ እስላሙ ደመቀ መኮንን ሥልጣኑን ተጠቅሞ አደባባይ ወጥቶ ሃዘኑን ሲገልፅ በዚህ በኩል አንዳቸውም ትንፍሽ የሚሉ አለመኖራቸው ገራሚ ነው።

"…ዛውያ ቲቪ፣ ሃሩን ሚድያ፣ የእስላም ኡስታዞች ጉዳዩን ከጣራ በላይ እያጮሁ እሪሪ ሲያስብሉት ከሳሽም፣ ወቃሽም የለባቸውም። በኦርቶዶክሳውያን ተቃውሞ ላይ ቃታ እየመዘዘ የሚደፋን ፖሊስ ዛሬ ሙጂብ አሚኖ ብቻውን ሲቀውጠው ባላየ ባልሰማ ነው የሚያልፈው።

"…የእኛዎቹ ጉደኛ ሰባክያን ተብዬዎች ብሔራዊ ቲአትር ስታንዳፕ ኮሜዲ ያቀርባሉ። የሲዲና የካሴት ምርቃት ሽቀላን ያጧጡፋሉ። ይሄ ነገር ልክ አይደለም የሚል አንድ እንኳ ታናቂ ሰባኪ ሲጠፋ ስታይ ደግሞ ምን ያህል አፈጣዲቆች እንደሆን ይገለጥልሃል። ኮተታም ምድረ ለማኝ የለማኝ ልጅ ደሀ ዘረ ደሀ ሳንቲም ቁስ ለቃቃሚ ሁላ። ደግሞ የፈለገ ብትሽለጠለጥ እንደው እሳቱ አይቀርልህም።

"…እየታዘባችሁ…!
143 viewsAshe abdo, 19:44
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-04-28 22:43:34
የወራቤ ቅዱስ ሩፋኤል ቤተ ክርስቲያን
117 viewsAshe abdo, 19:43
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-04-28 08:25:42
124 viewsAshe abdo, 05:25
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-04-28 08:25:40 ሐሙስ~አዳም

" አዳም ከእርሱ እንዳይበላ ያዘዝከውን በልቶ በበደለ ጊዜ ከገነት ደስታ ወጣ አንተ ግን አዳም ዕፅን በመብላት ያመጣውን ፍዳ ክቡርና ማኅያዊ በሚሆን መሰቀል ከፈልክለት "
አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ/ ውዳሴ መስቀል

በዚህ ዕለት ለአዳም የተሰጠው ተስፋ እና የተገባለት ቃል ኪዳን እንደተፈጸመ አዳምና ልጆቹ ነጻ እንደወጣን እናስባለን ሐሙስ አምስተኛ ቀን ነው እግዚአብሔር ለአዳም ከአምስት ቀን ተኩል በኃላ ከልጅ ልጅህ ተወልጄ አድንሃለው ብሎ የገባላት ቃልኪዳን እንደተፈጸመ ለማጠየቅ በዚህ ቀን የአዳም እና የልጆቹ መዳን ይዘከራል ቅዱስ ያሬድ በዝማሬው "የሕይወት ጎዳና የጥበብ ምንጭ ሕያው ሳለ የአዳምን ሥጋ ለብሶ ሞቶ በሞት ላይ በረታ ከሙትንም ተለይቶ ተነሣ በትንሣኤው አዳነን" እንዳለ መድኀኔዓለም ኢየሱስ ክርስቶስ በሞቱ እና በትንሣኤው ዘላለማዊ ድህነት እንደሰጠን አስበን በዚህ ቀን የበለጠ የአዳም እና የእኛ የልጆቹን መዳን እንዘክራለን

የሰው ልጅ እግዚአብሔር ከፈጠራቸው ፍጥረታት ሁሉ የተለየ ጸጋ እና ክብር የተሰጠው በአምሳለ እግዚአብሔር በከበሩ የእግዚአብሔር እጆች በገቢር የተፈጠረ ድንቅ ፍጥረት ነው የተሰጠውን ጸጋ ይዞ መጽናት ሲጠበቅበት ያልተሰጠውን ለማግኘት ሲሞክር የነበረውን ሁሉ ያጣ ነው በቅዱስ አትናቴዎስ ቅዳሴ ላይ
+ ሰው ንጉስ ሲሆን አላወቀም ራሱን በፍቃዱ አዋረደ ባሪያም ሆነ ጌቶች ያልሆኑም ገዙት
+ ሰው ባለጸጋ ሲሆን አላወቀም ራሱን በፍቃዱ አደኸየ ሆዱን አስራበ ነፍሱን አስጠማ
+ ሰው የብርሃንን ልብስ የለበሰ ሲሆን አላወቀም የቁርበትን ልብስ ለበሰ
+ ሰውስ ከጌታ በታች ገዢ ሲሆን አላወቀም ካልተፈቀደለት ዕፅ ቆርጦ በላ " ተብሎ እንደተጻፈ ያልተፈቀደለትን ዕፅ በልቶ ከጸጋ እግዚአብሔር ተራቆተ የሰውን መዳኑን እንጂ መጥፋቱን የማይወድ እግዚአብሔር አስቀድሞ ከፍቅሩ የተነሣ ሰውን በክብር እንደፈጠረው ከፍጹም ፍቅሩ የተነሣ ሲፈጥረን ከሰጠን የበለጠ ጸጋ እና ክብር ሰጥቶ አድኖናል በተአምረ ማርያም መቅድም የጠፋውን በግ አዳምን የፈለገው ባገኘውም ጊዜ የተሸከመው እውነተኛ ቸር ጠባቂያችን ክርስቶስ ከአንቺ የተወለደ እመቤቴ ማርያም ሆይ ደስ ይበልሽ ብለው አባቶች እመቤታችንን እንደሚያመስግኗት አዳም ኃጢአት ሰርቶ ከእግዚአብሔር በራቀና በጠፋ ጊዜ መልካም እረኛ ቸር ጠባቂ የተባለ ጌታችን ነፍሱን ስለ በጎቹ በመስጠት በመስቀል ሞቶ ሞታችንን አሸንፎልናል
ቅዱስ ያሬድ የዛሬው ዕለት ዝማሬም ይሄንን የሚዘክር ነው

" እነሆ ዛሬ የበረከት ፍሬዎች በቀሉ የጥምቀት ልጆችም በዙ የመድኃኒት ምልክት በአህዛብ መካከል ቆመ ክርስቶስ በዕፀ መሰቀሉ አድኖናል በደሙ ፈሳሽነት ዋጅቶናልና የሕይወት አገልጋይ በመካከላችን አለ እግዚአብሔር ወልድ ከሙታን ተለይቶ እንደ ተነሣ መላእክት ይናገራሉ ይመሰክራሉ ዛሬ ተነሥቷልና ሰማያት ይደሰታሉ ምድር ትደሰታለች ጌታ አዳምን ዛሬ ከእኔ ጋር ደስ ይበልህ በሞቴ አድኜሃለውና አለው"
119 viewsAshe abdo, 05:25
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-04-28 06:16:08
"ለሥልጣነ ክህነቱ የማይገባ' ካህን ብትመለከት፥ [በደፈናው] ክህነትን አትንቀፍ፡፡ ደገኛ የኾነውን የክህነት ሥልጣን ይዞ ያልተገባ ሥራን ሲሠራ በማየቱ ምክንያት፥ ከዚህ ተነሥቶ ሥልጣነ ክህነትን የሚነቅፍ አንድ ሰውስ እንኳን አይኑር፡፡

የአስቆሮቱ ይሁዳ ጌታችንን አሳልፎ ሰጥቷል፡፡ ይሁዳ እንዲህ በማድረጉ ግን ሐዋርያነት የሚነቀፍ ስለ ኾነ አይደለም፤ የይሁዳ የገዛ ነጻ ፈቃድ ችግር ነው እንጂ፡፡ የሚተቸውም ክህነቱ አይደለም፤ ጠማማው ነጻ ፈቃዱ ነው እንጂ፡፡

ስለዚህ አንተም ክህነትን አትንቀፍ፤ ክህነቱን ላልተገባ ሥራ የሚያውለውን ካህኑን እንጂ፡፡ ...

ሐኪም ሳይኾኑ ሐኪም ነን ያሉት ስንት ናቸው? በዚሁ ምክንያት በመድኃኒት ፈንታ መርዝ የሰጡትስ ስንት ናቸው? እየነቀፍኩ ያለሁት ሙያውን አይደለም፤ ሙያውን በአግባቡ የማይተገብሩትን ነው እንጂ፡፡

መርከቦች እንዲሰምጡ ያደረጉ መርከበኞችስ ስንት ናቸው? ነገር ግን ችግሩ የባሕር ላይ ጉዞ አይደለም፤ ሙያውን እንደሚገባ የማይተገብሩት ሰዎች ችግር ነው እንጂ፡፡

ስለዚህ አንተም አንድ ክፉ ክርስቲያን ብትመለከት በደፈናው የክርስትና ትምህርትን ወይም ሥልጣነ ክህነትን አትንቀፍ፤ ደገኛውን ሥልጣን ላልተገባ ሥራ የሚያውለውን ነው እንጂ፡፡"

ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ፥ የክርስቲያን መከራ፥ ገ. 115
101 viewsAshe abdo, 03:16
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-04-24 07:52:29
በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ

“ሕያውን ከሙታን መካከል ስለ ምን ትፈልጋላችሁ፤ ተነሥቶአል እንጂ በዚኽ የለም"
ሉቃ 24፥5

ክርስቶስ ተንስአ እሙታን፤
በዐቢይ ኃይል ወስልጣን፤
አሠሮ ለሰይጣን፤
አግዐዞ ለአዳም፤
ሰላም፤
እምይእዜሰ፤
ኮነ፤
ፍሥሐ ወሰላም።



❖ በእርግጥም አምላካችን በሞቱ ሞትን ገድሎ በትንሣኤው ሕይወትን አድሎናልና ደስታ ይገባናል::

❖ መድኃኔዓለም በኅቱም ድንግልና እንደ ተወለደ በኅቱም መቃብር ተነስቷል::

❖ ለደቀ መዛሙርቱም "ሰላም ለእናንተ ይሁን" ሲል በዝግ ደጅ ገብቷል::

❖ በዕለተ ትንሣኤው የመጀመሪያውን ደስታ እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ተካፍላለች፤ የእርሷን ያህል በሃዘን የተጐዳ የለምና፤ ቀጥለው ቅዱሳት አንስት እነ ማርያም መግደላዊት ትንሣኤውን አይተዋል፤ ሰብከዋልም::

❖ በዚሕች ቀን ማዘን አይገባም በትንሣኤው የደነገጡና የታወኩ የአጋንንትና የአይሁድ ወገኖች ብቻ ናቸውና::
 
❖ አምላካችን ወልደ እግዚአብሔር ኢየሱስ ክርስቶስ ከትንሣኤው በረከት ረድኤት አይለየን፤ በዓሉንም የሰላም የፍቅርና የበረከት ያድርግልን፤ የጌታችን በጐ ምሕረቱ በሁላችን ትደርብን::
 
"ሕያውን ከሙታን መካከል ስለ ምን ትፈልጋላችሁ ተነስቷል እንጂ በዚህ የለም፤ 'የሰው ልጅ በኃጢአተኞች እጅ አልፎ ሊሰጥና ሊሰቀል በሦስተኛውም ቀን ሊነሣ ግድ ነው' እያለ ገና በገሊላ ሳለ ለእናንተ እንደተናገረ አስቡ"
 
ሉቃ. 24፥5-8

"አሁን ግን ክርስቶስ ላንቀላፉት በኩራት ሆኖ ከሙታን ተነስቷል፤ ሞት በሰው በኩል ስለ መጣ ትንሣኤ ሙታን በሰው በኩል ሆኗልና፤ ሁሉ በአዳም እንደሚሞቱ እንዲሁ ሁሉ በክርስቶስ ደግሞ ሕያዋን ይሆናሉና"
 
1ኛ ቆሮ 15፥20
121 viewsAshe abdo, edited  04:52
ክፈት / አስተያየት ይስጡ