Get Mystery Box with random crypto!

ቅዱስ ዮሐንስ አፈ ወርቅ እንዲህ አለ 'በምሰብክበት ጊዜ ስታጨበጭቡልኝ ሰው እንደመሆኔ በዚያ | የደ/ፀ/ሳ/ቅ/ጊዮርጊስ አጥቢያ የጥምቀት ተመላሽ ወጣቶችና ጎልማሶች መንፈሳዊ ማኅበር

ቅዱስ ዮሐንስ አፈ ወርቅ እንዲህ አለ

"በምሰብክበት ጊዜ ስታጨበጭቡልኝ ሰው እንደመሆኔ በዚያ ቅጽበት ደስታና መደነቅ ይሰማኛል ወደ ቤቴ ሔጄ ያጨበጨቡልኝ ሰዎች ምንም ጥቅም እንዳላገኙ ሳስብ ግን ንግግሬ ሁሉ በከንቱ እንደቀረ ይሰማኛል፤ ስለዚህ ማጨብጨባችሁን የሚከለክልና ዝም ብላችሁ እንድትሰሙኝ ብቻ የሚያደርግ ሕግ ስለማስቀመጥ አስባለሁ" (On His Message 80)

“ቤት ውስጥ የእንግዳ ማረፊያ ቤት ይኑርህ አልጋ አዘጋጅ ጠረጴዛና መቅረዝም ይኑረው ክርስቶስ ሊመጣና ሊያርፍበት የሚችልበት ክፍል አዘጋጅና "ይህ የክርስቶስ ክፍል ነው" በል ምድር ቤት ያለ ትንሽ ክፍልም ቢሆን እሱ አይንቀውም፤ ዕርቃኑን የሆነው እንግዳ የሚፈልገው መጠለያ ብቻ ነው" (On Acts Homily 40.2)

“ለሞቱት ብቻ አናልቅስ፤ በቆሙት ብቻም አንደሰት ታዲያ ምን እናድርግ? ለኃጢአተኞች በሞቱ ጊዜ ብቻ ሳይሆን በቁማቸውም እናልቅስ፤ ስለ ጻድቃን ደግሞ በቁማቸው ብቻ ሳይሆን በሞቱም ጊዜ ደስ ይበለን ምክንያቱም ኃጢአተኞች ቆመውም ሞተዋል፤ ጻድቃን ግን ሞተውም ሕያዋን ናቸው" (On Phil. 3)

"ጴጥሮስ አለቀሰ ማልቀስ ብቻ ሳይሆን ምርር ብሎ አለቀሰ፤ ከዓይኑ በፈሰሰው ዕንባ ድጋሚ ተጠመቀ አምርሮ በማልቀሱም በዕንባው ኃጢአቱን አጠበ አንተም እንዲሁ አድርግ" (Paent 3.4)

“ንብ ከሌሎች እንስሳት ሁሉ ትከበራለች፤ የምትከበረው ታታሪ ሠራተኛ በመሆንዋ ሳይሆን የምትሠራው ለሌሎች በመትረፉ ነው"

ምንጭ
ዲያቆን ሄኖክ ኃይሌ
ግንቦት 12 2014 ዓ.ም