Get Mystery Box with random crypto!

'ዉሎህን/ሽን ቃኝ' ❖ አንድ ቀን ዝንብና ንብ እያወሩ በወሪያቸው መሀል ዝንብ ንብን እንዲህ ስት | የደ/ፀ/ሳ/ቅ/ጊዮርጊስ አጥቢያ የጥምቀት ተመላሽ ወጣቶችና ጎልማሶች መንፈሳዊ ማኅበር

"ዉሎህን/ሽን ቃኝ"

❖ አንድ ቀን ዝንብና ንብ እያወሩ በወሪያቸው መሀል ዝንብ ንብን እንዲህ ስትል ጠየቀቻት
"ንብ ሆይ ለምንድነው የሰው ልጆች እኔን የሚጠሉኝ? ለምንስ ነው የሚጸየፉኝ?
ቤታቸው ስገባ ያባርሩኛል ይገድሉኛል፤ የሚጠጡት ነገር ላይ ከተገኘሁ ይደፉታል የሚበሉት ነገር ላይ ካረፍኩ ያረፍኩበትን ቦታ ያለውን እህል ቆርሰው ይጥሉታል::

❖ አንቺን ግን እንደ እኔ አይገፉሽም እንደውም ቤታቸው ስትገቢ ይንከባከቡሻል ደግሞም መልካም ነገርን ተስፋ በማድረግ ደስታቸው እጥፍ ነው ለምንድነው?" ስትል ዝንብ ንብን ጥያቄዋን አቀረበች በዚህ ጊዜ ንብ እንዲህ አለቻት "ውሎሽ የት ነው?" እንግዲህ እዚህ ጋር ቆም እንበል፣
ሰው ጠላን፣ ገፋን፣ ናቀን እያልን እንደ ዝንቧ ጥያቄን አዝለን ከምንጓዝ ውሏችንን በደንብ እንይ መቼም ማንም በጤፍ ማሳ ላይ ስንዴን አይጠበቅም፤ ስለዚህ ምንጊዜም ውድቀታችንን ለማረምም ይሁን ብርታታችንን ለማብዛት ውሏችንን እንቃኝ።