Get Mystery Box with random crypto!

ከሙሉነት ጥቂቱን...7 (Team Huda) : #ጀግንነት_ራሱኑ!! ስለ እዝነትና ይቅር ባይነታቸው | TEAM HUDA

ከሙሉነት ጥቂቱን...7
(Team Huda)
:
#ጀግንነት_ራሱኑ!!

ስለ እዝነትና ይቅር ባይነታቸው ስናወጋ ሌላኛው ጎናቸውሳ ማለታችን አይቀርም... ፍርሀት ማነው አይነት ጥያቄን የሚያስነሱ ጀግና መሆናቸውን በተለያየ የታሪክ ሁነት አንብበናል። ወደ መዲና ለመሰደድ ሲወጡ በራቸውን የከበቧቸውን ጎረምሶች በእንዴት ያለ ድፍረት ተሻገሩ? ያሲንን ቀርተው!! እዚህ ጋር ነው የምንተዛዘበው...ጀግንነት በጡንቻህ አለይለካም...በምላስሽ ስለፎከርሽ አይወለድም...በአካኪ ዘራፍ አይነቃነቅም...በርግጥም ጀግንነት ሙሉ የሆነ መወከልን በአሏህ ላይ በመወከል እንጂ ከዬት ይገኛል? ቃሉን በመያዝ እንጂ እኛ ላይ የተቃጣ ሸር ሁላ በምን ይከሽፋል?

የበድር ጦርነት ወቅት ጀግናችን የነበሩበትን ሀል ጀግናው ፈረሰኛ ዐሊይ ቢን አቡጧሊብ(ረዲየሏሁ አንሁ) ሲተርኩ፡
<የአሏህ መልእክተኛ ከሁላችንም ይበልጥ ለጠላት ቅርብ ነበሩ።ከሁላችንም በላቀ ጀግንነት ተፋልመዋል።እኛም ከጠላት ጥቃት በርሳቸው እንከለል ነበር።>
በራእ(ረዲየሏሁ ዐንሁ) ሲለጥቁ
<በአላህ እምላለሁ አደጋ ሲበረታ በእርሳቸው እንከለል ነበር።ከመካከላችን በጣም ጀግናው ከእርሳቸው ጎን ተሰልፎ የሚዋጋው ነበር።>
ብለው ምስክርነታቸውን ሰደዋል...ጀግንነት በሳቸው በቃ!!


@Re_ya_zan
@Re_ya_zan
for any comment
@Teamhudabot