Get Mystery Box with random crypto!

ምስል#11 (Team Huda) ለልጆቼ የማወርሰው ሃብት በዘመኔ አላከማቸሁም፤ ወጣትነቴን ለቤቴ | TEAM HUDA

ምስል#11
(Team Huda)

ለልጆቼ የማወርሰው ሃብት በዘመኔ አላከማቸሁም፤ ወጣትነቴን ለቤቴ ለኑሮዬ ማቃኛ የሚሆንልኝን ጥሪት አላከማቸሁም፤ ጀሊሌ መቼም ለባሮቹ ቅርብ ነውና እንደሰው የሚያስፈልገኝን አልነፈገኘም፤ የዕለት ሪዝቄን አያላሳጣኝም... "አልሃምዱሊላህ"
ለከርሞ መጠበቤ ያ አነበረም። ከልጆቼ አልፎ ለትውልዱ የማወርሰውን እውቀት በማሰባሰብ ላይ ቁዋውን ይችረኝ ዘንድ ነበር ሃሳብ ጭንቀቴ፤ ዱንያ መቼም ለዚህ ገር ባትሆንም ጀሊሉ ሰብሩን ሰጥቶኝ ከመንገዴ እንዳልፈናቀል በእዝነቱ ጠብቆኛል።
አሁን ስጋቴ በጭራሽ ያ አይደለም በእድሜ ማምሻ የሚደክሙ አይኖቼ ከዛሬ ነገ ኡማው ጋ ሳላደርስ እንዳላልፍ ነው... በኔ ላይ ያኖረውን ኢልም እንዴት ሳላወጣው ከኔው ጋ ይጠፋል..! ለዚህም ቀንከሌት አለይም...ምሽት አላውቅም..ንጋትን አልጠብቅም። እስካለሁ ከጠረቤዛዬ ተሰይሜ አደራዬን ለማውረስ እተጋለሁ ጀሊሌ ይቀበለኝ።

ባላደራ ሁኜ ሳለ እንዴት አደራዬን ሳላደርስ አይኖቼ ማንቀላፋት ይቻላቸዋል!

@Re_ya_zan
For any comment
@Teamhudabot