Get Mystery Box with random crypto!

የሩሕ ጉዞ... (Team Huda) ፍትሕ እንደ አድማስ ከእጃችን ሲርቅ ይናፍቁኛል። ሕግ ይሉት | TEAM HUDA

የሩሕ ጉዞ...
(Team Huda)

ፍትሕ እንደ አድማስ ከእጃችን ሲርቅ ይናፍቁኛል። ሕግ ይሉት የማይታይ መንና ሲሆንብኝ ይናፍቁኛል። ቁራሽ መሬት፡ ክቡዱን የሰው ልጅ መቆራረሻ ሰበብ ሲሆን ቢኖሩ እንዴት ይሆኑ እያልኩ በማሰብ ወስጥ ይናፍቁኛል። ምክንያት...እሳቸው ...የፍትሕ አምባ... የሐቅ ሚዛኑ ናቸውና። የእውነተኝነት አይነታው!!

ነብይ መሆናቸው ከመታወጁ በፊት ስለሆነው እናውጋ... ሀጀረል አስወድን ማን ነው ወደ ቦታው የሚመልሰው? የትኛው ጎሳ ነው የሚከበረው? በጎሳ በተቧደነ ...ደም ለመፋሰስና ሰይፉን ለመሳል ኢምንት ሰበብ የሚጠብቅ ማህበረሰብ ውስጥ ናቸውና ጉዳዩ እንደተፈታው ባይፈታ ኑሮ እንዴት እልቂት ሊመዝ እንደሚችል ሳይታለም የተፈታ ነው። እዚህ ጋር ነው የፍትሕ አይነታነት!
በጋቢ(ኩታቸው)ያስቀመጡትን ሀጀረል አስወድ የሁሉም ጎሳ ተወካዮች ጫፉን እንዲይዙ ተደረገ...የሑሉም ልብ በተካሽነት ረካች... ከጎሳዎቹ የተመረጠ አልነበረም... አሚኑ ሙሐመድ(ሰለሏሁ ዐለይሂ ወሰለም) ያስቆሙት ለዘመናት ሊቋረጥ የማይችልን የሰው ልጅ ሞትን ነው። ከዛማ በበረካ እጆቻቸው አንስተው ወደ ቦታው መለሱት...ምን ያማረ ሕግ ፈፃሚነት!!
እንዲህ እንዲህ አይነት ሁነቶችን እየመዘዝን ብናወጋ የአሚኑን አሚንነት ሳናወላዳ እንረዳለን። ወቅታችን ይህን ወደ ሀያታችን ልናወርድበት የሚገባ ነውና ኢምንት በምንላት ነገር እንኳ ፍትሐዊነት እንለማመድ...እኩል መቁረስን...በእኩል አይን ማየትን...!!

በፍጡር ትንፋሹ
በአየር ነፋሹ
በአፍቃሪ ልቦች
በተንኮሻኮሹ
በገፈሉ ቀልቦች
በተረባበሹ
ከነሱም በላቁ
አውርድ ራህመትህን
በወደር የለሹ
በአሐመድ ሙሐመዱ
በናፍቆት ጨራሹ
በቤተሰቡም
ከኑር ተቀንጣሹ
በሰሃባው ሁላ
ሙሓባ ቀላሹ

ሰለዋቱ ረቢ ዓለይክ ያ ሀቢበ ሏህ!

@Re_ya_zan