Get Mystery Box with random crypto!

ራዚኤል ዘኢትዮጵያ

የቴሌግራም ቻናል አርማ razielethiopia — ራዚኤል ዘኢትዮጵያ
የቴሌግራም ቻናል አርማ razielethiopia — ራዚኤል ዘኢትዮጵያ
የሰርጥ አድራሻ: @razielethiopia
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 1.79K
የሰርጥ መግለጫ

#የህይወት_መፀሀፍ (መፀሀፈ ራዚኤል)
አባታችን አዳም ከገነት ከወጣ ቡሀላ ቅዱሳን መላእክት ያስተማሩት የሰማያተ ሰማይ ብሎም የምድራዊ ሰማያት ሚስጥራትን ጥበባትን ለልጆቹ #ለኢትዮጵያን ማስተማርያ ይሆን ዘንድ በ እግዜብሔር ፍቃድ በድንጋይ ላይ በግእዝ ቋንቋ ፅፎ አስቀመጠላቸው ይህ መፀሀፍ መፃፈ ራዚኤል ብለን የምንጠራው ነው።

Ratings & Reviews

3.67

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

1

3 stars

0

2 stars

1

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 3

2021-11-30 10:36:29
1.5K viewsMikiyas, 07:36
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-11-30 10:36:28
1.5K viewsMikiyas, 07:36
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-11-30 10:33:17 #ህዳር_ጽዮን 21_3_2014 ዓ.ም

በዚህች ቀን የእስራኤላውያን መመኪያ በእመቤታችን ስም የተሰየመችው ታቦተ
ጽዮን ዳጐን በተባለው ጣኦት ላይ ኃይሏን ክብሯን የገለጸችበት ቀን ነው፤
ቤተክርስቲያን ጽዮን ማርያም ስትል ዕለቱን ታከብረዋለች።

#ታሪክ : - አክሱም ጽዮን እንደዛሬው ድርቅ ያለ መሬት አልነበረም ባህር ነበር እንጂ፤ አብርሃና አጽብሃ ለታቦተ ጽዮን ምን ዓይነት ቤተክርስቲያን ነው የምንሰራላት ቦታውስ የት ጋር ነው የሚሆነው እያሉ ሲጨነቁ ጌታችን ተገለጸላቸው ድንጋይ ላይ ቆሞም አዩት፤ ቤተክርስቲያኗን እዚህ ባህር ላይ ስሩት ስሟንም በእናቴ ስም ሰይሟት፤ ይላቸዋል ጌታ ሆይ ይህ እኮ ባህር ነው ይሉታል ቅዱስ ሚካኤልን ከገነት አፈር ይዞ እንዲመጣ ያደርገዋል ባህሩ ላይ ነሰነሰው ደረቀ የዛሬውንም ቅርጽ ያዘ ይላል ጌታችን የቆመበት የእግሩ ምልክት ዛሬም ድረስ ይታያል ፤
ምንጭ፡ #ድርሳነ_ጽዮን፤

ዳግመኛ በዛሬዋ ዕለት ጎርጎርዮስ ገባሬ መንክራት ይለዋል የእረፍት ቀኑ ነው፤ አገሩ ቢሉ ሮም ነው የተማረ ግብረ ገብ
ነው፤ዓለም ያልፋል ይጠፋል ብሎ መንኖ ገዳም ገባ በተጋድሎም ኖረ፤ በወቅቱ
የነበረው ኤጲስ ቆጶስ በሞተ ጊዜ በምትኩ ጎርጎርዮስን ሊሾሙ አባቶች
ተሰበሰቡ እርሱ ግን ሹመት አልፈልግም ብሎ ከመካከላቸው ተሰወረ፤ እርሱ
በሌለበት ወንበር ዘርግተው ወንበሩን ካባ ላንቃ አልብሰው የጎርጎርዮስን ስም
እየጠሩ ጸሎት አድርገው ይሾሙታል ህዝቡም 3 ጊዜ ይደልዎ ይደልዎ ይላል፤ ይገባዋል ማለት ነው፤ ከዚህ በኃላ የእግዚያብሔር መልአክ ተገልጾ ከዚህ ገዳም ውጣ ሹመትህን ተቀብለህ ህዝቡን አገልግል ይለዋል፤ እንደተባለውም አደረገ ለ 45 ዓመት በሹመት ህዝቡን አገልግሏል፤ ብዙ ተግሳጻትን ድርሳናትን ደርሷል፤ ከነዚህ አንዱ ቅዳሴ ጎርጎርዮስ ነው፤ በሰሞነ ሆሳህና የሚቀደስ ቅዳሴ ነው፤ ለምን ጎርጎርዮስ ገባሬ መንክራት ተባለ ቢሉ፤ ብዙ ተአምራትን ይሰራ ስለነበረ ነው፤
•ከነዚህም አንዱ- ሁለት ወንድማማቾች ነበሩ አባታቸው
ትልቅ የውሃ ኩሬ ትቶላቸው ሞተ፤ እየተጣሉበት ተቸገሩ ጎርጎርዮስ አንድ ቀን አንተ አንድ ቀን እርሱ ዓሳውን እያጠመዳችሁ ተጠቀሙ ይላቸዋል፤ በአንተ ጊዜ ብዙ እየወጣ በኔ ጊዜ ምንም አይወጣም ብለው ድጋሚ ተጣሉ፤ ጎርጎርዮስ ጸሎት አድርጎ ያንን ውሃ አድርቆ እያረሳችሁ ተጠቀሙበት
ብሏቸዋል። የዚህ አባት እረፍቱ በዛሬዋ ቀን ነው፤ ከበዓሉ በረከት ያሳትፈን፤

የእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ምልጃ ረድኤት በረከት አይለየን፡ የአስራት ሀገሯ ቅድስት ሀገር ኢትዮጵያን ጽኑ ሰላም ታድርግልን።
@razielethiopia
1.5K viewsMikiyas, edited  07:33
ክፈት / አስተያየት ይስጡ