2022-03-04 16:19:21
የቤቲንግ ሱስ ያለባቸው ሰዎች ካልተጫወቱ ይጨንቃቸዋል፡፡ ሲጫወቱ ደግሞ የበለጠ ይጨንቃቸውና ከፍ ባለ ገንዘብ ይጫወታሉ፡፡ አንዳንዴ በቁማሩ ምክኒያት ገንዘብ እያባከኑ ወይም ከቤተሰብ ጋር እየተጣሉም መጫወታቸውን ይቀጥላሉ፡፡ እንዴት እንደሚያስቡ ካልተረዳን ድርጊታቸው ትርጉም አይሰጥም፡፡ የቤቲንግ ሱስ ያለባቸው ሰዎች የሚስቡበት መንገድ በጥቂቱ፦
ሲያሸንፉ በችሎታ ነው፤ ሲሸነፉ በእድል ነው፡፡
ችሎታ የሚያስፈልጋቸው የቁማር ጨዋታዎች አሉ፡፡ እንደ ፑል ወይም አንዳንድ የካርታ ጨዋታዎች፡፡ ወይም እውቀት የሚፈልጉ ውርረዶች እንደ የስፓርት ውድድሮች፡፡ ነገር ግን የፈለገ ችሎታ ቢጠይቁ ሁሉም የቁማር ጨዋታዎች እድል ይፈልጋሉ፡፡ ማሸነፍም መሸነፍም ውስጥ ከችሎታ በተጨማሪ( አንዳንድ ጨዋታዎች ላይ ሙሉ በሙሉ) እድል አለ፡፡ የቤቲንግ ሱስ ያለባቸው ሰዎች ግን ሲያሸንፉ በችሎታ፣ ሲሸነፉ ግን በእድል እንደሆነ ነው የሚያስቡት፡፡
መርጦ ማስታወስ፦
የቤቲንግ ሱስ ያለባቸው ሰዎች ያሸነፉባቸውን ጥቂት ጨዋታዎች ጥርት አድርገው ሲያስታውሱ የተሸነፉባቸውን ብዙ ጨዋታዎች ይረሳሉ፡፡ በተጨማሪም 'ለጥ..ቂት!' የተሸነፉትን እንዳሸነፋ አድርገው ነው የሚያስታውሱት፡፡ ይህ የወደፊቱን ጨዋታ የማሸነፍ እድላቸውን ሲያሰሉ በተዛባ መንገድ እንዲሆን ያደርገዋል፡፡ "ሁሉንም ልክ ነበርኩ። ማንቺስተር ባይሸነፍ 20ሺ በላ ነበር" ይላሉ።
የተወሰነ ጨዋታ ቢበሉም ቁማሩን ከፍ ባለ ገንዘብ እስከቀጠሉ ድረስ የተበሉትን እንደሚያስመልሱ ያስባሉ፡፡ በዚህ ምክኒያት ለሌላ ሰው የሚያስደነግጥ ብር እየተበሉም ምንም አይመስላቸውም፡፡ ከዚሁ ጋር ተያይዞ በተደጋጋሚ ከተሸነፉ እድል ወደ እነሱ እንደምታዘነብል ያምናሉ፡፡ (they commit Monte Carlo fallacy) ልክ አንድ ልጅ ሲወለድ ሴት ወይም ወንድ የመሆን እድሉ ግማሽ ለ ግማሽ ቢሆንም ከዚህ በፊት ሁለት ሴቶች መውለድ የሚቀጥለውን ወንድ የመሆኑን አድል የሚጨምረው እንደሚመስላቸው ሰዎች፡፡
ስለ ቤቲንግ ሱስ ፌስቡክ ላይ መረጃ ስፈልግ አንድ ግሩፕ አጋጠመኝ። ቤጉማ ይባላል። 26 ሺ አባላት አሉት። የቤቲንግ ጉዳተኞች ማህበር ማለት ነው። የቤቲንግ ሱስ የሚታከም የአእምሮ ህመም ነው።
ያለ አእምሮ ጤና፤ ጤና የለም!
2.0K views13:19