Get Mystery Box with random crypto!

MEDITATION🎯

የቴሌግራም ቻናል አርማ rasn_mehon — MEDITATION🎯 M
የቴሌግራም ቻናል አርማ rasn_mehon — MEDITATION🎯
የሰርጥ አድራሻ: @rasn_mehon
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 557
የሰርጥ መግለጫ

“ዉድድርህ ከሰዎች ጋር አይደለም! ዉድድርህ:-
➻ከገደልከዉ ሰአት
➻ከፈጠርከዉ በሽታ
➻መማር እያለብህ ችላ ካልከዉ እዉቀት
➻መስዋእት ካረከዉ ጤናህ
➻አዲስ ሃሳብን አልቀበልም ካልከዉ ማንነት
➻ያንተን መጣር ከማይወዱ ሰዎች
➻እድለ ቢስ እንደሆንክ ከሚነግርህ ሰይጣን ጋር ነዉ”
@MENGE_DEGNAW

Ratings & Reviews

2.00

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

0

3 stars

1

2 stars

1

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች

2022-07-20 12:27:30 "አንድ ሰው በክፋ መንፈስ የሚናገር ወይንም የሚሰራ ከሆነ ስቃዩ አይለቀውም ። ፍጹም ንጹህ በሆነ ሃሳብ ተመርቶ ሲናገር ወይንም ሲሰራ ደስታ ነው የሚከተለው፤ ደስታ ልክ እንደ ጥላ ሆኖ ፈጽሞ ላይለቀው በሄደበት ይከተለዋል።"

ጋውታማ ቡዳህ ( 563-483 ከክርስቶስ ልደት በፊት )

@RASN_MEHON
213 viewsIt's Me , 09:27
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-20 12:11:58 የመሳሳብ ሕግ ተጣባቂ ነው !

የመሳሳብ ሕግ ተጣባቂ ነው ። የሌላን ሰው መልካም ዕድል በምትወድበት ጊዜ መልካም እድላቸው አንተ ላይ ይጣበቃል ። እንዲሁም የሌላን ሰው ማንኛውንም  ጥሩ ነገር ስታደንቅ ያ ነገር ወደአንተ ይጋባል ። በሌላም በኩል ስለ አንድ ሰው መጥፎ ወይም ያልተገባ ባህሪያት በምታወራበት ጊዜ እነዚያ ነገሮች ወደ አንተ ሕይወት ይገባሉ።

የመሳሳብ ሕግ ለስሜቶችህ ሳያቋርጥ አፀፋ በመመለስ ላይ ነው ። የሰጠኸውን ማንኛውንም ነገር ትቀበላለህ ። ማንኛውም ሰውም ሆነ ኩነት ላይ የለጠፍከው ስም በአንተ ላይ እንደተለጠፈ ቁጠረው ። ያንኑ መልሰህ ትቀበላለህና።

በእርግጥ ይህ አሁን ያልነው ነገር እጅግ መልካም ዜና ነው! ለምን ቢባል አንተ የምትፈልጋቸውን እና የምትወዳቸውን ነገሮች ሁሉ በሌላ ሰው ላይ ፈልገህ በማግኘት የአንተ እንዲሆኑ ማድረግ ትችላለህና። ዓለም በመሰረቱ ለአንተ ልክ እንደ መጻሕፍት ማስመረጫ ካታሎግ ነች ። የፍቅርን ሀይል ምትረዳ ከሆነ አንተ ምትወደውን ነገር ሁሉ በሌሎች ላይ ማየትና ማግኘት ትችላለህ ። ለነገሩ ህይወትህን መቀየሪያ በጣም ቀላል እሚባል መንገድ ነው ። ብዙ ትግልና ግብግብ የማይጠይቅ በመሆኑ ከአንተ ሚጠበቀው ብቸኛ ነገር ቢኖር እምትወደውን ነገር እንደምንም ብለህ በሌላ ሰው ላይ መፈለግ ነው ። በሌላ በኩል ደግሞ እማትፈልጋቸውንና እማትወዳቸውን ነገሮች በሰው ላይ ስታይ ሽሻቸው ። እንግዲ ይህ የቱን ያህል ቀላል እንደሆነ አስተውል ።

" በዚህ እረገድ የመጀመሪያውን እርምጃ ጥሩ በማሰብ ፤ ሁለተኛውን እርምጃ በመልካም ቃል ፤ ሶስተኛውን ደግሞ በመልካም ተግባር ጀምሬ ነው ይኸው አሁን ገነት የገባው ያህል ሚሰማኝ " (የዛሮዋስትሪያኖች የሀይማኖት ጥቅስ)

ምንጭ ፦ ታላቁ ሀይል

@MENGE_DEGNAW
211 viewsIt's Me , 09:11
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-13 14:12:11 ከስጋ እስር መውጣት...

፨፨፨

ስጋዊ አካል ከንቃተ አካል የተለየ ነው ። ንቃተ አካል ስጋዊ አካል ውስጥ ገብቶ የሚኖር ቢሆንም በራሱም ግን ከቁሳዊ ባህሪይ በላይ የሆነ የተለየ ሕልውና አለው ።

፧

ስጋዊ አካል ቁሳዊ የሆነና በስሜይ ህዋሳቶቹ አማካኝነት ከቁሳዊው ዓለም ጋር የሚግባባ ሲሆን ፣ ንቃተ አካል ግን ግን ስጋዊ አካልን እንደ ልብስ የሚጠቀምና ቁሳዊ ያልሆነ ህልውና ነው ።

፧

ንቃተ አካል ከስጋዊ አካል ወጥቶ ሲሄድ ስጋዊ አካል በድን ሆኖ ይቆያል ። በዚህ ወቅት በስጋዊ አካል ፈንታ ንቃተ አካላችን ብዙ ነገሮችን እየተከታተለ ይቆያል ።
...

ፕሌቶ እንዲህ ብሎ ነበር...

" የሰው ጥንተ ተፈጥሮ (ምነነት) ያለው ነፍሱ ላይ ነው ። ነፍስ በስጋ ከመታሰሯ በፊት የራሷ ሕልውና የነበራትና ከስጋ መሞት በኋላም ሕያው ሆና የምትኖር ናት ። "

፧

ይህ የፕሌቶ አስተምህሮ በኋላ ላይ የተለያዩ ሃይማኖቶች ውስጥ ገብቷል ይለናል ፍልስፍናው...

@RASN_MEHON
365 viewsIt's Me , 11:12
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-10 21:41:24 Essentialism (የመጠርቃት ጥበብ)!

አለመጠርቃት፣ ይሄንንም ያንንም ማግበስበስ፣ ሁሉንም መፈለግ፣ በቃኝን አለማወቅ፣ ስንዝር ሲገኝ ክንድን እያሰቡ እንቅልፍ ማጣት፣ ሁሉአማረሽነት፣ በአጠቃላይ አለመጠርቃት። የዘመናችን ትልቁ የሰውልጅ በሽታ ነው።

ህይወት አጭር ናት። ሁሉንም ለማግበስበስ አትበቃም። ሁሉንም ብታግበሰብስስ ምን ያደርግልሀል? "Essentialism" የዚህ የ "በቃኝ" ሳይንስ ነው። የመምረጥ ጥበብ ነው። አስፈላጊዬ የቱ ነው? የአህያ ፈሱስ የቱ ነው? ብሎ ትኩረትን የሚሰጡትንና፣ እንዳላየ የሚያልፉትን ነገር የመምረጥ፣ የማወቅ፣ የመቆጠብ ህይወት ነው።

ህይወትህን አብራህ ልትዘልቅ ፈቃደኛ የሆነች ሴት አግኝተሀል። በቃ በቃህ። እሷው ትበቃሀለች። አስር ሴት ላይ አትንጠላጠል። ምንም የተለየ ነገር አይገኝም። ያው ነው። ከያውም በላይ መበሳበስ ነው።

አመነዘርክ። ዶሮም ያደርገዋል። ውሻም ይልከሰከሳል። ከመልከስከስ ህይወት ውጣ። እና አንድ የምትሆንህን፣ የምታዛልቅህን፣ የወደድካትን፣ የምትወድህን ሔዋን ምረጥና፣ እዚህም እዚያም ዳሌ እያባረርክ የምትንዘላዘልበትን ሀይልና ቀልብ ሰብሰብ አድርገህ፣ በሌላ ለሰውልጅ ጠቃሚ ነገር ላይ አውለው።

ባለፀጋ መሆን ትፈልጋለህ? የብር ርሃብ ላይ ነህ? ሀብት ጠምቶሃል? ጥሩ። ግን ከመጠን በላይ በመስገብገብ ዕድሜህን በመንጠቆነት አትጨርሰው። የሰውልጅ የሚባሉ ድንቅ ፀጋዎችህን ሁሉ ለገንዘብ አትቸርችር።

ማንነትህን አጥና። ራስህን ፈልገህ አግኝ። ዋጋህን ተረዳ። ደካማና ጠንካራ ጎንህን እወቅ። ሰው እንደሆንክ፣ የገንዘብ ሰንዱቅ ሆነህ ሳትቀር፣ በህይወትህ ስኬታማ የምትሆንበትን መንገድ ፈልገህ፣ ኃይልህን በዚያ ላይ አውለው።

ያሰብከውን ስታገኝ የምትጠረቃ ሰው ሁን። ስኬታማነትና ደስተኝነትን ከሚቅጨለጨል ሳንቲም ጋር አታለካካ። ሀብታም ማለት ሌላ አይደለም። ባለው የሚደሰት ሰው ነው። የፈጣሪን ፀጋ ተላበስ። ለሌሎች መትረፍን እንጂ ሁልጊዜ በሌሎች ማትረፍን አትመኝ። ራስህን ቻል። ተብቃቃ። በቃኝን እወቅ።

በዚህ ዓለም ላይ ሚሊየን ዓይነት ሙያዎች አሉ። ሚሊየኑንም ልትላበስ አትችልም። የመምረጥን ግዴታ እወቅ። የማታውቀውን ተማር። አጥና። የማታውቀውን አትዘባርቅ። ባልዋልክበት ኩበት ለቀማ አትውጣ። በምታውቃት፣ አሪፍ በሆንክባት ነገር ላይ ለመጨመር ትጋ። በያዝከው ነገር ለመራቀቅ መንፈስህን አስገዛ።

Essentialism is freedom። ራስን መወሰን፣ በቃኝ ማለት መቻል፣ ታላቅ ነፃነትን መቀዳጀት መሆኑን ተረዳ።

ፈላስፋው ዲዮጋን ጎዳና ወጥቶ በእንጨት ግርግም ውስጥ ያረረበትን ምስር እየቀማመሰ ኑሮውን ሲገፋ የተመለከተ አንድ የንጉሡ አማካሪ የሆነ ፈላስፋ ለዲዮጋን አዝኖለት አንድ ምሽት ሰው ሳያየው ወደ ዲዮጋን ግርግም ቀረበና ዲዮጋንን መከረው፦

"ዲዮጋን ወዳጄ፣ በዕውቀት ካንተ ባልስተካከልም
አንዲትን ትንሽዬ ምክር ልለግሥህ ነው ዛሬ ወዳንተ
የመጣሁት፣ አንተኮ በዚህ ዕውቀትህ ላይ ትንሽ
ለንጉሡ የመሽቆጥቆጥ ጠባይ ብታክልበት ኖሮ፣
እውነት እልሀለሁ ዛሬ መገኛህ ከንጉሡ ጋር ቤተ-
መንግሥት ውስጥ ነበር፣ ያረረበት ምሥር ሳይሆን
የሚያስጎመጅ ጮማህን እየቆረጥክ፣ እና እባክህ
ስማኝ ዲዮጋን፣ ይህን የምመክርህ ላንተው ቅን
አስቤ መሆኑን ተረዳኝ፣ ምክሬ ይቺው ናት. . !"

ብሎት፣ ሰው አየኝ አላየኝ ብሎ ከግርግሟ ሊፈተለክ ሲነሳ፣ በፀጥታ ሲያዳምጠው የነበረው ዲዮጋን ለምክሩ የሙያ አጋሩን አመስግኖ፣ ግን አንዲትን አባባል ለመንገዱ ጣል አደረገለት፦

"ወዳጄ አሪስቲፐስ፣ አንተምኮ ግን፣ በዚህ ቅንነትህ
ላይ ያረረ ምሥርን እየበሉም ደስተኛ ሆኖ መኖር
እንደሚቻል ብታውቅበት ኖሮኮ፣ ይኼን ጊዜ
የንጉሡ አጫዋችና ምንጣፍ ጎታች ከመሆን
ትገላገል ነበርኮ!"

በቃኝ ማለት ነፃነት ነው። መብቃቃትን መምረጥ ትልቅ ነፃነት አለው። መጠርቃት ከባርነት እስራት ነፃ መውጣት ነው።

ጃፓኖች ይህንን "የመብቃቃት ጥበብ" "Minimalism" ይሉታል። በሁሉነገራቸው ነው የሚተገብሩት። በአኗኗራቸው፣ በአመጋገባቸው፣ በገንዘብ ጥማታቸው፣ በገንዘብ አመዠራረጣቸው፣ በጊዜ አጠቃቀማቸው፣ በህንፃ አገነባባቸው፣ በኪነጥበባቸው፣ በቤተሰብ አመሠራረታቸው፣ በቴክኖሎጂያቸው፣ በሪሶርስ አጠቃቀማቸው፣ በሁሉነገራቸው። የተመጠነ፣ የተቆጠበ፣ የረቀቀ፣ የተመረጠ፣ ቁጥብ፣ ምጥን፣ ህይወትን ነው የሚመሩት።

ይህን ጥበብ ከአያቶቻችን፣ ከወላጆቻችን የበለጠ ማንም ሊነግረን የሚችል አይመስለኝም። አያት ቅድመ አያቶቻችን ነፃነታቸውን የተጎናፀፉት የበቃኝን ጥበብ በማወቃቸው ይመስለኛል። ነፍሳቸውን ከቁስ ሰቀቀን ማላቀቅ በመቻላቸው ይመስለኛል የራሳቸው ጌታ ለመሆን የበቁት።

በብሉይ ዘመን የክርስቶስ የፍቅርና የይቅርታ ትምህርት የማረካቸው ነጋዴዎች ክርስቶስን ተከትለው፣ ያንተ ደቀመዝሙሮች ለመሆን ምን እናድርግ? አሉት። ሀብታችሁን ጥላችሁ ተከተሉኝ አላቸው።

ነጋዶቹ ግን ሀብታቸውን አልጣሉም። የፈለጉት ያንንም ይሄንንም ነው። ክርስቶስ ግን እንዲመርጡ የግድ አላቸው። እርሱ እንዳላቸው ሀብታቸውን ጥለው አልተከተሉትም። የእርሱን ፍቅርና ይቅርታ ጥለውለት ሄዱ።

ሁሉንም ማግበስበስ አይቻልም። መንፈሳዊ ነህ? የመንፈስን ነገር ተከተል። ፅድቅን ሥራ። በጥበብህ ተራቀቅ። በሥጋ ሥራ አትርመጥመጥ። መንፈሣዊ ልዕልናህን፣ ለጮማም ለምሥርም አትሽጥ። ፈጣሪ በነፃ የሸለመህን የከበረ ነፃነት፣ በማይረባ ርካሽ የወንበር ቁስ አትለውጠው! አለዚያ ግን ነጋዶቹ እንዳደረጉት ጥምጣምህን ጣልና፣ ገንዘብ የሚገኝበትን የነጋዶች ገበያ ተቀላቀል።

ምረጥ። ተብቃቃ። በቃኝን እወቅ። ሁሉ አይመርህ። ሁሉንም መሆን አትችልም። የምትሆነውን ዛሬውኑ ምረጥ። እና ነፃነትህን ተቀዳጅ።

Essentialism ይኸው ነው።

አመስግኜ አበቃሁ።

(Assaf Hailu)

#ለሰዎች #ሼር በማድረግ መገደኛውን ይደግፉ

ለመቀላቀል

@MENGE_DEGNAW
@MENGE_DEGNAW
395 viewsIt's Me , 18:41
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-01-21 17:46:51
#ህይወታችንና_የገደል_ማሚቶው...

አንድ ልጅ ከአባቱ ጋር ወደ አንድ ተራራ ላይ እየተንሸራሸሩ ነበር፡፡ ድንገት ልጁ አንሽራተተውና ሲወድቅ “እካካካካካ!” ብሎ ጮኸ፡፡ በሚያስገርም ሁኔታ ተራራውም “እካካካካካ!” ሲል ደገመለት፡፡ “ማነህ አንተ?” ሲል ጠየቀ ልጁ በጉጉት፡፡ “ማነህ አንተ?” አለው ተራራውም መልሶ፡፡ “አደንቅሃለሁ!” ሲል ጮኸ ልጁ፡፡ ተራራውም መልሶ “አደንቅሃለሁ” አለ፡፡ በመልሱ የተናደደው ልጅ “ፈሪ!” ብሎ አንባረቀ፡፡ ተራራውም “ፈሪ!” ብሎ ጮኸበት፡፡ .

ግራ የገባው ልጅ ወደ አባቱ ዘወር ብሎ “ምን እየተካሄደ ነው?” ሲል ጠየቀው፡፡ አባትየው ፈገግ ብሎ “ልጄ! አድምጥ” አለውና “አሸናፊ ነህ!” አለ ጮክ ብሎ፡፡ ከተራራው ውስጥ የሚሰማውም ድምጽ መልሶ “አሸናፊ ነህ!” አለ፡፡ ልጁ ምንም ነገር ባይገባውም በአድናቆት ተዋጠ፡፡ አባትየው እንዲህ ሲል ምሥጢሩን ገለፀለት፤ “ሰዎች የገደል ማሚቶ ይሉታል፤ እሱ ግን ሕይወት ነው። አንተ የምትናገረውን ወይም የምታደርገውን ነገር መልሶ ላንተው ይሰጥሃል። ሕይወታችን በቀጥታ የድርጊታችን ነፀብራቅ ነው፡፡ በዚህች ዓለም ላይ ሰዎች ብዙ ፍቅር እንዲሰጡህ ከፈለግህ የራስህን ልብ በሰዎቹ ፍቅር ሙላው። የሥራ ባልደረቦችህ በጥራት እንዲሰሩልህ ከፈለግህ አንተ በጥራት ስትሰራ ይዩህ፡ : ይህ እውነታ በሁሉም የሕይወት ገጽታዎች ውስጥ በማንኛውም ነገር ላይ ይሰራል። ሕይወት የሰጠሃትን ማንኛውንም ነገር መልሳ ትሰጥሃለች” አለው፡፡ ሕይወትህ አጋጣሚ ሳይሆን የራስህ ነፀብራቅ ነው!!

ዶ/ር አቡሽ አያሌው
1.6K viewsaman •‿•, 14:46
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-10-11 22:40:22 መፍራት ስትጀምሩ መኖር ታቆማላችሁ

የናዚ ተጽእኖ በከፋባቸው ዓመታት ጃኔዝ (Janez Rus) የተባለ አንድ ሰው በናዚ
ዘመን በነበረው አቋም ምክንያት በቀልን በመፍራት ለ32 ዓመታት ከአንድ
ስፍራ ሳይወጣ እንደተደበቀ ይነገራል፡፡ ይህ ወጣት በፍርሃት ከመደበቁ በፊት
የጫማ ስራ ባለሞያ ነበር፡፡ ፍርሃቱ ከነገሰበት በኋላ ግን የቀረውን የወጣትነቱን ዘመን በመደበቅ ነበር ያስበላው፡፡ በፈረንጆቹ አቆጣጠር በJune, 1945 ይህ ወጣት በእህቱ እርሻ ውስጥ በሚገኝ ቤት (Farmhouse) ውስጥ ለ32 ዓመታት ተደብቆ ሲኖር የእናቱን ቀብር እንኳን ለመካፈል አልወጣም፡፡ ከዚህ ስፍራ ከወጣ በኋላ እንዲህ ሲል ተደምጧል፣ “ከተደበኩበት ቦታ ሆኜ ውጪ የሚገኙ ሰዎች ሲደሰቱና ሲስቁ ስሰማ ምርር ብዬ አለቅስ ነበር”፡፡
ይህ ወጣት በእነዚያ አመታት ውስጥ ያገኘውን ነገር እየበላ ከላይ ሆኖ
ወደታች ያለውን መንደር ከማየት ውጪ ምንም ነገር አላደረገም፡፡

ፍርሃት እንዲህ ይልሃል …

◆ አትመልከት - አንድ ነገር እንዳታይ!
◆ አታድምጥ - አንድን ነገር እንዳትሰማ!
◆ አታስብ - አንድ ድምዳሜ ላይ እንዳትደረስ!
◆ አትወስን - ስህተት እንዳትሰራ!
◆ አትራመድ - እንዳትወድቅ!
◆ አትኑር - እንዳትሞት!
◆ አትማር - ፈተና እንዳትወድቅ!
◆ አትውደድ - እንዳትጎዳ!

በሕይወትህ ልታነግሱ የምትችሉት ስሜት አንዱን ብቻ ነው - የፍርሃትን ወይም የመኖር ድፍረትን፡፡ አንዱ እንዲነግስ ስትፈቅድለት ለሌላኛው የባርነት ትእዛዝን እያስተላለፍክ ነው፡፡ ፍርሃት ሲነግስ የመኖር ጣእም ይጠፋል፡፡

#ተነሱና_ፈጣሪን_ተማምናችሁ_ቀና_ብላች_ኑሩ!

ዶ/ር ኢዮብ ማሞ
@RASN_MEHON
2.0K viewsaмan•‿•, 19:40
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-10-09 20:10:21 ሶቅራጥስ እስር ቤት ሳለ


…………………………………………………
"ሰው በህይወቱ ሁሉ አኗኗሩን ለሞት በቀረበ ሁኔታ ውስጥ አድርጎ ራሱን ያሰለጠነ፣ ሞት ወደ እሱ ሲቀርብ መጨነቁ ታዲያ ቂላቂልነት ነው"

/\ሶቅራጥስ/\_____

እውነተኛ ፈላስፎች ስልጠናቸውን በሞት ላይ ያደርጋሉ። ከሌሎች ሰዎች በተለየ ሞት ለእነሱ ችግር የሚፈጥርባቸው አይደለም።
በዚህ መልኩ እስኪ ተመልከቱ………
እነሱ አጥብቀው በስጋቸው እርካታ የማይሰማቸው ከሆነ፣ እንዲሁም ነፍሳቸው ብቻዋን እንድትሆን የምትናፍቅ ከሆነ እንግዲያውስ የናፈቁት ሲሳካ መፍራቱና መጨነቁ ጭራሽኑ ምክንያታዊነት የለውም።



የህይወት ዘመናቸው ተሳክቶ ሲሹት ወደነበረው ቦታ በመድረሳቸው መደሰት ባህርያዊ አይሆንምን?_ ጥበብ ላይ፤ እንደዚሁም ደማይፈለገው ከስጋ ቁርኝት ማምለጥ?

በርግጥ ብዙዎች በነፃ ምርጫቸው ሟች ፍቅረኛዎቻቸውን ሚስቶቻቸውንና ልጆቻቸውን በመከተል እነዚህ የሚወዷቸው ሰዎችን በላይኛው ዓለም ማየትና የማግኘት ተስፋ የሚያደርጉ አሉ።
በአንፃሩ ጥበብን የሚሻት ወደሚቀጥለው ዓለም ሳይተላለፍ እዚህች ጥበብ ላይ መድረስ እንደማይችል የሚገነዘብ_ በሞቱ ሀዘን ይሰማዋልን?
እሱ የምር ፈላስፋ ከሆነ ይህን ጉሆ ማድረጉ ደስታ አይፈጥርበትምን?

ይህንን ነው ልናስብ የምንችለው፤ ምክንያቱም ጥበብን ከነንፅህናዋ የሚያገኛት በሌላ ቦታ ሳይሆን በሌላኛው ዓለም ላይ ብቻ መሆኑን እሱ የጠነከረ እምነት ስለሚይዝ። ይህ እንግዲህ እውነት ከሆነ፤ ይህ ሰው ሞትን መፍራቱ ትርጉም የለሽ አይሆንምን?



ሞት ሲመጣበት ሀዘን የሚሰማው ሰው ካየህ እሱ ጥበብ አፍቃሪ ሳይሆን ስጋውን ወዳጅ መሆኑን የሚያረጋግጥ ነው። እንደኔ እምነት ይህ ሰው አፍቃሬ-ነዋይ እና አፍቃሬ-ዝና ነው፤ ወይም ከሁለቱ አንዱን ወይም ደግሞ ሁለቱንም ወዳጅ ነው። እውነታው ይሄ ነው።

መልካም ስነምግባርና ቁርጠኝነት ብለን የምንጠራቸው በዋናነት የፍልስፍና ተግባር ነው መሆን ያለበት ብለን መውሰድ እንችላለን።

እራስን መግዛትንም እንደዚሁ። በሰፊው እንደሚታወቀው በፍላጎቶች ያለመነዳት የተቆጠበ ደንታቢስነት ማሳየት ይሄ ለነዚያ ለስጋቸው ለማይጨነቁትና ህይወታቸዉን በመፈላሰፍ ለሚያሳልፉ የተሰጠ አይደለምን?

/ቁርጠኝነትና ራስን መግዛትን በተመለከተ በሌሎች ሰዎች በሚተገበረው መልኩ ከወሰድነው አመክንዮ'ኣዊ ሆነው አናገኛቸውም/

እንዴት ብለን ብንጠይቅ…… መቼም ታውቃላችሁ፣ ከፈላስፋ በስተቀር ሌሎች ሰዎች ሞትን የላቀው ክፋት አድርገው እንደሚወስዱት። ወይስ አታውቁም?

ደፋር የሆነ ሰው ሞትን ሲጋፈጥ- የሚጋፈጠው ከዛ በላይ ይኖራል በሚል ፍራቻ ነው። ከፈላስፋ በስተቀር ለሌሎች ቁርጠኝነት ከፍራቻና ከሰቀቀን የሚመጣ ነው። ምንም እንኳን ፍራቻና ቦቅቧቃነት ሰውን ደፋር ማድረጋቸው ኢ-ምክንያታዊ ቢሆኑም።

ራስን መግዛትንስ? ይሄስ ከላይ እንደተጠቀሰው አይደለምን?
ልቅ የሆነ ፍላጎትን ገታ ማድረግ?
ይህን የማይቻል አድርገን እንቆጥረው ይሆናል፤ ይሁን እንጂ ሁሉም አንድ ናቸው። ራስን መቆጣጠርን በተወሰነ መልኩ የተለማመደ ከላይ እንደጠቀስኩት ይህንንም ማድረግ ይችላል። ሰዎች አንድን ፍላጎት ትተው ሌላውንም መቆጣጠር ስለማይችሉ ሌሎቹ እርካታዎች እንዳይቀሩባቸው ይሰጋሉ።
የፍላጎታቸውን ማድረጋቸዉ ለደስታቸው ቅድመ ሁኔታ አድርገው ፍቺ ቢሰጡም፣ እውነታዉ ግን ያ አይደለም- የተወሰኑ ፍላጎቶችን ለመቆጣጠር ስለማይችሉ ይፈፅሟቸዋል፣ ይህ ደግሞ ለሌሎች ተከታታይ የማይቋቋሟቸው ደስታዎች ያጋልጧቸዋል፤ ይህ እንዳይሆን ቀደም ብሎ ወደተጠቀሰው ይወስደናል- ፍላጎትን በመግታት ራሳቸውን መሰብሰብ ይችላሉ ወደሚለው።



አንድን ደስታ ወይም ስቃይን ወይም ፍርሀትን ከግብረ-ገብ አንፃር ስናየው በሌላ መለወጥ ትክክለኛ መንገድ አይደለም። ልክ ሳንቲሞች የተለያዬ ዋጋ እንዳላቸው ሁሉ እነዚህም እንደዛ ናቸው።

እነዚህ የምንነጋገርባቸው ሁሉ የሚገበያዩበት አንድ አይነት ተመን ነው ያላቸው--- ጥበብ። ቁርጠኝነት፣ እራስን-መግዛት፣ የመርህ ሰው መሆንን ወይም ግልፅ በሆነ ቋንቋ መልካምነት፤ የደስታ ወይም የፍርሀት እና የመሳሰሉት ስሜቶች መኖርን እንዲተገብሩ የሚያደርገው ለነገሩ ጥበብ ነው፤ ያለበለዚያ በራሳቸው ምንም ናቸው። እንደዚሁም የግብረ-ገብ ስርዓት በተነፃፃሪ ስሜታዊ እሴቶች ላይ የተመሰረተ ከሆነ-በዝርዝር የቀረበ ግልፅ እሳቤ በውስጡ ምንም ጥልቅና እውነት የሌለው እንዲያው የማይጨበጥ ሀሳብ ብቻ ነው ሚሆነው።

ትክክለኛ የግብረገብ እሳቤ እራስ መግዛትም ሆነ የመርህ ሰው ወይም ቁርጠኝነት፣ እራስህን ከእነዚያ ስሜቶች ማንፂያ ሲሆን፣ ጥበብ እራሱ ደግሞ ከእነዚህ ስሜቶች የፀዳ ማድረጊያ ነው።

ምናልባት እነዚህ ሀይማኖታዊ ተነሳሽነትን የሚወስዱ ሰዎች ከዚህ ጥበብ የራቁ አይደሉም። ሁልጊዜ አስተምህሮታቸው በተምሳሌት ትርጉም የሚሰጠው ነው- ያእውቀትን ያልተላበሰውና እውቀት ያልተገለፀለት ሰው ወደሚቀጥለው አለም ሲገባ ወደ አረንቋው ይጣላል። ነገር ግን ያ ነፅቶና ተገልፆለት ወደሚቀጥለው ዓለም የደረሰ ከመላዕክት ጋር ይቀላቀላል። ተግባርን የሚያከናውኑ ሃሳብ ጠንሳሾች ምን እንደሚሉ ታውቃላችሁ፦ <<ብዙዎች አርማውን ተሸክመዋል የሚተገብሩት ግን ጥቂቶች ናቸው>>


ሶቅራጥስ በእስር ቤት ሳለ ከወዳጆቹ ጋር ካደረገው ንግግር……

ምንጭ ፕሌቶ (የሶቅራጥስ የህይወቱ መጨረሻና ፍልስፍናው)

ትርጉም በስንታየሁ ዘርዓብሩክ
ከገፅ 73_76

Credit to Sileshi Million
@RASN_MHONE
1.6K viewsaмan•‿•, edited  17:10
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-10-01 10:35:36
''መንፈሳዊነት ከሃይማኖት አይመጣም። መንፈሳዊነት የሚመጣው ከነፍሳችን ውስጥ ነው። ሃይማኖትንና መንፈሳዊነትን አንቀላቅል። ሃይማኖት ማለት መንፈሳዊነትን ለማጠናከር ለሰዎች የተፈጠረ ህግና ስርአት ነው።...

...መንፈሳዊነት ማለትም የርዕዮተ አለም አመለካከት አልያም ስለአምላክ የሚያጠና የእውቀት ዘርፍ አይደለም፣ መንፈሳዊነት ማለት ንፁህና በተፈጥሮ የሚቸረን የህይወት መንገድ ነው። መንፈሳዊነት በሰማየ ሰማያት ካለው የበላይ ሃይል ፣ ጠፈር ጋር እንዲሁም እርስበርሳችን የሚያቆራኘን መረብ ነው።''

(ሞሐ አንበሳ ዘ እምነ ነገደ ይሁዳ ቀዳማዊ ኃይለ ስላሴ)

@rasnflega
1.4K viewsaмan•‿•, 07:35
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-09-28 19:32:03 የምታስበውን ነህ

“የጠላነው የሚደርስበት የፈራነው የሚወርስበት ምክንያት”

በነጋሽ አበበ

በቁሳዊ (ፊዚካል) ሳይንስ ዓለም ውስጥ ተቃራኒ አካላቶች እንደሚሳሳቡ የተረጋገጠ እውነት ነው፡፡ በአንፃሩ በስነ ልቡናው ዓለም ተመሳሳይ ነገሮች ይሳሳባሉ የሚል አመለካከት አለ፡፡ በአጭሩ “በሕይወታችን ወጥተን ወርደን የምናገኘው ነገር የሚመስለንን፣ የምንኖረው የምናስበውን፣ የምንሆነው የምንመኘውን ነው” የሚል ፍቺ ነው ያለው፡፡

በአንድ ተራ ቀን ውስጥ በብዙ ሺህ የሚቆጠሩ ሀሳቦች ወደ አእምሯችን ጓዳ ይጎርፋሉ፡፡ ከእነዚህ ሀሳቦች ውስጥ ሚዛን የሚደፉት ሀሳቦች ሕይወታችን የያዝነውን መልክ እንዲይዝ መንስኤ ናቸው፡፡ እያልኩ ያለሁት አብዝተን የምናስበውን እንሆናለን ነው፡፡ አልፎ አልፎ ብቻ የምናስበው ሀሳብ ከተራ ምኞት የዘለለ ወደ ተጨባጭ እውነታነት የሚቀየርበት እድል የሌለው የሕልም ቅቤ ነው፡፡

ወደድንም ጠላንም ሕይወታችን የአስተሳሰባችን ቅኝት ነው፤ ውጪ የምንመለከተው ኑሯችን የማንመለከተው የውስጥ ሀሳባችን ነፀብራቅ ነው፡፡ ፈረንጆቹ “what goes around comes around” ይላሉ፡፡ የሄደ ነገር ተመልሶ መምጣቱ አይቀሬ ነው የሚል ትርጉም አለው፡፡

ሀሳብ ኃይል አለው፤ ጉልበት አለው፡፡ ከውስጣችን ሲፈልቅ፣ ለሌሎች ሲገለፅም ሆነ ለራስ ብቻም ሲታሰብ የሚመስለውን ጠፍጥፎ ሰርቶ ይዞ መምጣቱ አይቀርም፡፡ አንድ አንድ ጊዜ በፍርሀት እና ጭንቀት ብቻ ሰዎች አካላቸው የሚመነምነው እንዲሁም ታማሚ የሚሆነው ለዚህ ነው፡፡ ደስታ ብቻውን ፊታችንን እንደ ጨረቃ የሚያበራውም ለዚህ ነው። የማይጨበጥ ሀሳብ የሚጨበት ቁስ አካል ይሆናል፡፡

በሀሳብ እና ቁስ መካከል ያለው ልዩነት የመጨበጥ እና ያለመጨበጥ ብቻ ነው፡፡ ከኮምፒውተር ጋር አመሳስለን ብንመለከተው ሀሳብ “ኦፕሬቲንግ ሶፍትዌር” ነው፤ ቁስ አካላት ደግሞ “ሀርድዌር”፡፡ ኮምፒውተሩ የሚሰራው በሶፍትዌሩ ምሪት ነው፡፡ ኮምፒውተሩ ላይ ሰርተን የምናገኘው የትኛውም ነገር ወደ ኮምፒውተሩ ያስገባነው ነገር ውጤት ነው፡፡ “Garbage in garbage out” እንዲሉ፡፡ በጎ ማሰብ በጎ ነገር ወደ ሕይወት ይዞ ሲመጣ ክፉ ሀሳብ ክፉ ክፉውን እንዲሁ ጎትቶ ይዞ ይመጣል፡፡

እህል ለሰጠ አፈር ወርቅ ለሰጠ ጠጠር መስጠት ሁልጊዜ የሚያጋጥም ክስተት አይደለም፡፡ እህል የሰጠ እህል ወርቅ የሰጠም ወርቅ ነው የሚያገኘው፡፡ መልካም ነገሮች በተደጋጋሚ ሲያጋጥሙት “የአያቴ ምርቃት እኮ ነው” የሚል ወዳጅ አለኝ፡፡ በልጅነቱ መልካም ልጅ ነበር፡፡ አሁን የሚያጋጥመው መልካም ነገር የዛ መልካም ልጅነት ውጤት ነው፡፡ እዚህ ሀሳብ ውስጥ ቁልፉ ነገር በእርግጥ አስተዳደጉ በጎ አመላከከት እንዲኖረው አድርጓል የሚለው ነው፡፡ ቢያንስ እኔ ይኼንን መመስከር እችላለሁ፡፡

ደግመን ደጋግመን የምናስባቸው ሀሳቦች፣ አእምሮአችን የሚያወጣቸው እና የሚያወርዳቸው ግምቶች እና መላ ምቶች እንዲሁም በዓይነ ህሊናችን መላልሰን የምንቃኛቸው ነገሮች በአንድም ሆነ በሌላ መልኩ ወደ ሕይወታችን ነፍስ ዘርተው አካል አውጥተው ይከሰታሉ፡፡

መጥፎ የሕይወት አጋጣሚ የምትሉትን አንድ ነገር እስኪ ለማስታወስ ሞክሩ፡፡ ስራ ማጣት፣ ከሚወዱት ሰው ጋር መለያየት ወዘተ ሊሆን ይችላል፡፡ የክስተቱን መነሻ ገመድ ጫፍ ይዛችሁ እስከ ሌላኛቸው ጫፍ ድረስ ያለውን ሁኔታ በጥልቀት ስትቃኙት በአእምሯችሁ ይፈጠራል ብላችሁ አስቀድማችሁ ያሰባችሁት፣ ውስጣችሁ በስጋት መልኩ የተመላለሰ፣ የጠረጠራችሁት ወዘተ ክስተት ሆኖ ታገኙታላችሁ፡፡ “የፈሩት ይደርሳል የጠሉት ይወርሳል” ማለት ይኼ ነው፡፡

ትልልቅ ፈተናዎች ጎዳናችን ላይ ጋሬጣ ሆነው ሲመጡ ፍርሀት እና ንዴት ውስጣችን ይፈጠራል፡፡ በእርግጥ ይኼ ተፈጥሮአዊ ነው፡፡ ፈተና ሲጋረጥብን ፈተናውን የምንመለከትበት መንገድ ግን ለፈተናው እጃችንን እንድንሰጥ ወይንም ደግሞ ከፈተናው ደመና በላይ ከፍ ብለን ፈተናውን እንድናልፈው ያደርገናል፡፡

“ነግሬህ ነበር እኮ፣ ባለፈው እንኳን እንደዚህ እንደዛ ሆኖ፣ ሰውን ማመን ድሮም… ወዘተ” የሚል የማያቋረጥ አስጨናቂ ሀሳብ ማሰብ ያንኑ መላልሰን የምናስበውን እና የምንናገረውን ይወልዳል፡፡ ደስ ሲለንም እንዲያው ነው፡፡ ሁሉንም ነገር በሮዝ  መነፅር እንመለከታለን፤ ለምናገኘው ሰው በሙሉ በጎዎች እንሆናለን፤ ፍቅራችን ይጨምራል፤ አመስጋኝ ነን፤ ሰዎች ለምን እንደሚከፋቸው ሁሉ ግራ ግብት ሊለን ይችላል፡፡

ቀደም ሲል ሀሳብ ጉልበት አለው ብያችኋለሁ፡፡ በእርግጥ ሕይወታችን ውስጥ ለሚፈጠሩ የረቡም ሆኑ ያልረቡ ነገሮች ብቸኛው ተጠያቂ ሁልጊዜም መሆን አለብን እያልኩ አይደለም፡፡ ሳንፈቅድ ሊጫኑብን፣ ሊያጋጥሙን፣ ልናልፍባቸው ወዘተ የሚችሉ ነገሮች አሉ፡፡
ችግር ተደራርቦባችሁ ሀዘን ውስጥ ወድቃችሁ፣ ድብርት ተጫጭኗችሁ ሳለ አጮልቃችሁ የምታዩበት ትንሽ የተስፋ ቀዳዳ ሲታያችሁ ውስጣችሁ መነቃቃት ይፈራል፣ ጥንካሬያቸሁ ያቆጠቁጣል፡፡ በሂደት ወደነበራችሁበት ጥሩ የስሜት ከፍታ ትመለሳላችሁ፡፡ አሁን ምን ማድረግ እንደምትችሉ አጥርታችሁ ትጀምራላችሁ፡፡ ያሏችሁ አማራጮች ጎላ ጎላ ብለው ይታያችኋል፡፡ “ለካ ይኼንንም ማድረግ እችላለሁ” ማለት ትጀምራላችሁ፡፡ “ምን ነክቶኝ ነው እስከዛሬ ድረስ ዓይኔ ስር ቁጭ ብሎ ያላየሁት” ትሉ ሁሉ ይሆናል፡፡ የነካባችሁ እና የጋረደባችሁ አሉታዊ አስተሳሰባችሁ ነው፡፡

አሉታዊ አስተሳሰብ አሉታዊ ነገሮችን ደርቦ ደራርቦ ይዞ እየመጣ መንገዳችሁን ዘግቶት ነበር፡፡ አዎንታዊ ነገር ማሰብ በሌላ መልኩ ስትጀምሩ ግን ማድረግ የምትችሉት ነገር ይገለጥላችኋል፡፡ የተለየ ነገር ስለመጣ ሳይሆን ዓይነ ህሊናችሁን የጋረደው መጥፎ የሀሳብ ሞራ ስለተገፈፈ ነው፡፡ የነካችሁ አዎንታዊ አስተሳሰብ ነው፡፡ አስተሳሰባችሁን መቀየራችሁ ብቻውን ወደ ሕይወታችሁ ተመልሶ የሚመጣውን ነገር መቀየር ሲጀምር ታስተውላላችሁ፡፡ ሁላችንም ከየት ተነስተን ወደየት እንደመጣን ብናስብ አመዛኙ ድላችንም ሆነ ውድቀታችን ከአመለካከታችን ጋር በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ የተያያዘ ሆኖ እናገኘዋለን፡፡

“Stickiness” የሚባል የኢንተርኔቱ ፅንሰ ሀሳብ አለ፡፡ አንድ ድረ ገፅ ምን ያህል በተደጋጋሚ በጎብኚዎች ይጎበኛል የሚለውን የሚገልፅ ሀሳብ ነው፡፡ በዚህ መልኩ በጎ ነገሮች ሕይወታቸው ውስጥ ያለማቋረጥ የሚመጣላቸው (ወረቀት ከፈለኳት እግር አውጥታ ቢሮዬ ድረስ ትመጣከለች ትላለች አንድ ወዳጄ)፣ ደስታ ከፊታቸው ገፅ ላይ የማይጠፋ፣ ያም ያም ያለ ልዩነት የሚወዳቸው ሰዎች አሉ፡፡ አንድ አንድ ጊዜ “ምን አስነክታው? ምን አስነክቷት? ይሆን” የሚል ጥያቄ እናነሳለን፡፡ ለምን ይኼንን ድረ ገፅ ሰዎች ከሌላው የበለጠ ይጎበኙታል ብሎ እንደመጠየቅ ነው፡፡

የእነዚህ ሰዎች ማራኪ ምስጢራቸው ከአስተሳሰባቸው ጋር የተጋመደ ነው፡፡ ሰው መልካም እንደሆነ ያስባሉ፤ በራሳቸው ይተማመናሉ፤ ቅን እና ተባባሪ ናቸው፤ ከአይቻልም ይልቅ ይቻላል ማለትን ያዘወትራሉ፤ በጥቅሉ አጠር አድርጌ ስገልፀው በአንድ መደበኛ ቀን ውስጥ የሚያስቡት አብዛኛው ሀሳብ በጎ ነው፡፡ በመሆኑም በጎ ነገር በብዛት ይገጥማቸዋል፤ የጥሩ ነገር ማግኔት ናቸው፤ ከውስጣቸው ወደውጪ የሚንፀባረቀው በጎ ሀሳብ በጎ ነገሮችን መልሶ መላልሶ ወደ ሕይወታቸው ይዞ ይመጣል፡፡ መጪው ጊዜ በጎ አሳቢዎች ከመቼውም ጊዜ በበለጠ መልኩ የሚበረክቱበት እንዲሆን ምኞቴ ነው፡፡

መልካም ምሽት

ሌላውን ለማስተማር ሼር አድርጉ!!
@RASN_MEHON
1.4K viewsaмan•‿•, 16:32
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-09-27 15:49:57 #አንተ_ግልፍተኛ_እስቲ_ተመከር!

“ቁጣህ ሲገነፍል ይህን አስታውስ - ቁጣህ አንተን መግዛት እንደሌለበት። ከዚያ ይልቅ እርጋታ እና መልካም ምላሾችን መስጠት ከስልጡን ሰው የሚጠበቁ ናቸው። እውነተኛ ሰው ለቁጣ መንገድ አይሰጥም፤ አይረበሽምም፡፡ ይህ ሰው ጥንካሬ፣ ድፍረት እና አቅሙም አለውና ቁጣ እና ማማረር እርሱን አይገዙትም። ሰው ወደ እርጋታው በቀረበ ቁጥር ወደ ጥንካሬው ይቀርባል”
#ማርከስ_አውሬሊየስ

ስለምን ቦክሰኞች ከፍልሚያ በፊት እርስ በእርስ መጥፎ ቃላትን ይሰጣጣሉ? ቃላቶቹ መጥፎ እንደሆኑም እያወቁ ወደ ተፎካካሪዎቻቸው በእጅጉ የቆሸሹ ቃላትን ይወረውራሉ። ይህን ማድረጋቸው የንዴት ምላሽን ለመፍጠር ነው። ሰዎችን መረበሽ እና ማበሳጨት እነሱን ከጨዋታው ለማስወጣት ቀላሉ መንገድ ነው።

የተናደድክባቸውን ጊዚያት አስታውስ። ቁጣ የሚያስደንቅ አልያም የጥንካሬ ምልክት አይደለም - መናደድ በራሱ ስህተት ነው።

ደካማነት ነው።

ምናልባትም ይህ አንተን ለመጣል የተዘረጋ ወጥመድ ይሆናል።

ተፎካካሪዎቹ እና ደጋፊዎቹ ቦክሰኛውን ጆዊ ሊዮስን “የሳጥን ውስጥ ሮቦት” ብለው ይጠሩታል። ለዚህም ምክንያታቸው ደግሞ ሊዮስ በቦክስ ፍልሚያ ሳጥን ውስጥ ሳለ ምንም አይነት ስሜትን አይገልጽም - ስሜተ በራድ ነው፤ ፍጹም እርጋታን የሚያሳየው ገጽታው ለተፋላሚዎቹ መፍራትን እና መሸበርን ይፈጥርባቸዋል።

ጥንካሬ ማለት ራስን መቆጣጠር ነው። የማይፈራ፣ የማይደነግጥ፣ የማይቆጣ ምክንያቱም ሁሉም ስሜቶቹ በእርሱ ስር ናቸው።

በስሜቶቹ_ሳይሆን_የሚመራው እርሱ የስሜቶቹ መሪ ነው።

የስሜትህ መሪ ሁን!!!
@RASN_MEHON
1.1K viewsaмan•‿•, 12:49
ክፈት / አስተያየት ይስጡ