Get Mystery Box with random crypto!

Ghion Automotive - ግዮን አዉቶሞቲቭ

የቴሌግራም ቻናል አርማ ghionautomotive — Ghion Automotive - ግዮን አዉቶሞቲቭ G
የቴሌግራም ቻናል አርማ ghionautomotive — Ghion Automotive - ግዮን አዉቶሞቲቭ
የሰርጥ አድራሻ: @ghionautomotive
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 1.58K
የሰርጥ መግለጫ

ስለ ተሽከርካሪ ,ተሽከርካሪ ክፍሎች እና ጥገና ሙያዊ ማብራሪያዎች እንዲሁም የመንጃ ፍቃድ ትምህርቶች ይቀርቡበታል።
የዩቲዩብ ቻናል👇
https://youtube.com/channel/UCL39ckebS0PpWTou8EBdkoA

Ratings & Reviews

2.00

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

0

3 stars

1

2 stars

0

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች

2022-07-27 13:44:34


የባጃጅ(ታክሲ 1) የመንጃ ፍቃድ ስልጠና ተግባር ክፍል 1
የመጀመሪያ ቀን አነዳድ ምን ይመስላል?
ሊንኩን ተጭነዉ ቪዲዮዉን ይከታተሉ...
609 viewsSam Bob, 10:44
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-24 14:40:48
786 viewsSam Bob, 11:40
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-24 14:37:53 Over 21k followers on tiktok!
5K Subscribers on YouTube
10Q

follow me here
https://youtube.com/channel/UCL39ckebS0PpWTou8EBdkoA


https://vm.tiktok.com/ZMNjx6ePS/
720 viewsSam Bob, 11:37
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-01 21:05:45 https://vm.tiktok.com/ZMNkwQTM9/?k=1
learn driving on tiktok! 3ቁጥር መሰናክል part 1
1.4K viewsSam Bob, 18:05
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-26 20:40:26 https://vm.tiktok.com/ZMNMxWfX7/?k=1
በየቀኑ አዳዲስ አስተማሪ ቪዲዮዎችን በግዮን አዉቶሞቲቭ የቲክቶክ ቻናል ይከታተሉ!

ሊንኩን ተጭነዉ ቪዲዮዉን ይመልከቱ
1.5K viewsSam Bob, 17:40
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-23 09:23:05 https://vm.tiktok.com/ZMNjx6ePS/
የግዮን አዉቶሞቲቭ አጫጭር አስተማሪ ቪዲዮዎችን በቲክቶክ ይከታተሉ!
ከላይ ሊንኩን ይጫኑ

ግዮን አዉቶሞቲቭ!
@Ghionautomotive
1.5K viewsSam Bob, 06:23
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-19 07:12:16 የመንጃ ፍቃድ ትምህርት
ንድፈ ሀሳብ - ክፍል 3

የማቀዝቀዣ ክፍሎች

ኢንጅን(ሞተር) ሀይል የማምረት ተግባር በሚያከናዉንበት ጊዜ በሚቀጣጠለዉ ነዳጅ ምክንያት ከፍተኛ ሙቀት ይፈጠራል።

ይህ ሙቀት ካልተወገድ በሞተር ክፍሎች ላይ ጉዳት ያስከትላል። ስለሆነም ይህን ሙቀት በተለያዩ ዘዴዎች መቀነስ ወይም ማስወገድ ያስፈልጋል።@GhionAutomotive

ለዚህም cooling system ወይም የማቀዝቀዝ ስርዓት ለሞተር ደህንነት እጅግ አስፈላጊ ሲሆን ሞተርን የማቀዝቀዝ ዘዴ በሁለት ይከፈላል እነርሱም:-
1,በአየር የማቀዝቀዝ ዘዴ እና
2, በዉሀ የማቀዝቀዝ ዘዴ ናቸዉ@GhionAutomotive

በአየር የማቀዝቀዝ ዘዴ

ይህ ስርዓት አየር በሞተር ፊንሶች(ሽንሽን ብረቶች) በማለፍ ሲሊንደርን ጨምሮ ከፍተኛ ሙቀት ያላቸዉን የሞተር ክፍሎች የሚያቀዘቅዝበት ዘዴ ነዉ።@GhionAutomotive

በአየር የማቀዝቀዝ ዘዴን ቀለል ያሉና ሞተራቸዉ ለአየር ተጋላጭ የሆኑ እንደሞተር ሳይክል አይነት ሞተሮች ይጠቀሙታል።

በዉሀ የማቀዝቀዝ ዘዴ

ዉሀ በሞተርና በራዲያተር መካከል በዉሀ ቦይ አማካኝነት በመመላለስ ሞተር ሲሞቅ ሙቀቱን ተሸክሞ ወደ ራዲያተር በመዉሰድ ከቀዘቀዘ በኋላ ደግሞ ተመልሶ ወደ ሞተር በመሄድ የሞተር ክፍሎችን የሚያቀዘቅዝበት ሂደት ነዉ።@GhionAutomotive

በዉሀ የማቀዝቀዝ ዘዴ የማቀዝቀዣ ክፍሎች

ራዲያተር:- ለሞተር ማቀዝቀዣ የሚያስፈልገዉን ዉሀ የሚይዝና ከሞተር ሙቀት ተሸክሞ የተመለሰዉን ዉሀ በፋን(ቬንቲሌተር) አማካኝነት የሚያቀዘቅዝ ቱቦና ፊንስ(ሽንሽን ብረቶች) ያሉት ክፍል ነዉ።@GhionAutomotive

የራዲያተር ክዳን:- በራዲያተር ዉስጥ ያለዉ ዉሀ ወደ ዉጭ እንዳይፈስ ከማድረግ ሌላ ሁለት ተግባራትን የሚያከናዉኑ ሁለት ቫልቮች አሉት። እነርሱም:-
1,ፕሬዠር ቫልቭ እና
2, ቫኪዩም ቫልቭ ናቸዉ።@GhionAutomotive

ፕሬዠር ቫልቭ:- ከፍተኛ ፕሬዠር(ግፊት) ያለዉ ዉሀ ወደ ራዲያተር በሚመለስበት ጊዜ ይህ ቫልቭ በመከፈት የተወሰነ ዉሀ ወደ ኤክስፓንሽን ታንክ እንዲገባ ያደርጋል።

ቫኪዩም ቫልቭ:- ከዉሀ ጋር ተቀላቅሎ የሚገባዉ አየር ወደ ዉጭ በሚወጣበትና ራዲያተር ዉስጥ ያለዉ የዉሀ መጠን በሚቀንስበት ጊዜ ቫኪዩም(ክፍት ቦታ) ይፈጠራል። ይህ ቫኪዩም ራዲያተር ሽሪንክ እንዲያደርግ ወይም እንዲጨማተር ያደርጋል። ይህ እንዳይፈጠር ቫኪዩም ቫልቭ በመከፈት ተመጣጣኝ የሆነ ዉሀ ከኤክስፓንሽን ታንክ ወደ ራዲያተር እንዲመለስ ያደርጋል። @GhionAutomotive

ዋተር ፓምፕ(የዉሀ ፓምፕ)(ፖምፓዲላኮ):- ሞተር ከተነሳ በኋላ ከክራንክ ሻፍት የዙር ሀይል የሚያገኝ ሲሆን በራዲያተር ዉስጥ የሚገኘዉን ዉሀ በከፍተኛ ፕሬዠር በመግፋት ዉሀዉ በሞተር ክፍሎች በመዘዋወር እንዲያቀዘቅዝ ያደርጋል።@GhionAutomotive

ዋተር ጃኬት(የዉሀ መተላለፊያ ቱቦ):- በሞተር ዉስጥ ዉሀ የሚዘዋወርበትና የሞተር ክፍሎችን የሚያቀዘቅዝበት ክፍል ነዉ።

ቴርሞስታት:- የሞተር የመስሪያ ሙቀት መጠን እስከሚደርስ ድረስ ዉሀ ከሞተር ወደ ራዲያተር እንዳያልፍ ዘግቶ የሚያቆይ ሲሆን የሞተር የመስሪያ ሙቀት መጠን በሚደርስበት ጊዜ ቫልቯን በመክፈት ዉሀ ከሞተር ወደ ራዲያተር እንዲያልፍ የሚያደርግ ክፍል ነዉ።@GhionAutomotive

ኤክስፓንሽን ታንክ:- በከፍተኛ ፕሬዠር(ግፊት) ምክንያት ከራዲያተር በፕሬዠር ቫልቭ በኩል የሚወጣዉ ዉሀ የሚጠራቀምበት ክፍል ነዉ።

ፋን(ቬንትሌተር):- በመካኒካል ወይም በኤሌክትሪክ ሀይል የሚሰራ ሲሆን አየርን በመቅዘፍ በራዲያተር የሚገኝን ዉሀ ያቀዘቅዛል።@GhionAutomotive

በአንድ ራዲያተር ላይ ሁለት አይነት ሆዝ ወይም የዉሀ መስመር ያለ ሲሆን እነርሱም:-
1, ወሳጅ ሆዝ(ወሳጅ መስመር) እና
2, መላሽ ሆዝ(መላሽ መስመር) ናቸዉ።

ወሳጅ ሆዝ(ወሳጅ መስመር):- ዉሀ ከራዲያተር ወደ ሞተር የሚያልፍበት ቱቦ ወይም መስመር ነዉ።@GhionAutomotive

መላሽ ሆዝ(መላሽ መስመር):- የሞቀ ዉሀ ከሞተር ወደ ራዲያተር የሚያልፍበት ቱቦ ወይም መስመር ነዉ።

Engine overheating( ሞተር ከመጠን በላይ የሚሞቅባቸዉ ምክንያቶች)@GhionAutomotive

በቂ ዉሀ በራዲያተር ዉስጥ አለመኖር
የራዲያተር መቀደድ
የራዲያተር ክዳን ቫልቮች ብልሽት
የራሱ ያልሆነ የራዲያተር ክዳን መጠቀም
የራዲያተር ፊንሶች(ሽንሽን ብረቶች) በቆሻሻ መደፈን
የቴርሞስታት ዘግቶ መቅረት
የዉሀ ፓምፕ ብልሽት@GhionAutomotive
የቬንትሌተር መሰበር ወይም ተገልብጦ መገጠም
የዘይት ከመጠን በላይ መወፈር መቅጠና መቆሸሽ
የሚኒሞ መብዛት
የጎማ ሊሾ መሆንና የመሳሰሉት ናቸዉ።@GhionAutomotive

ለማቀዝቀዣ ክፍሎች መደረግ ያለበት ጥንቃቄ

የማቀዝቀዣ ክፍሎችን በንፅህና መያዝ
የሚያፈሱ ክፍሎች እንዲጠገኑ ማድረግ
በራዲያተር ዉስጥ ዝገት እንዳይፈጠር አንቲረስት (ፀረ ዝገት) ኬሚካል መጠቀም@GhionAutomotive
በማቀዝቀዣ ክፍል ዉስጥ ዉሀ ወደ በረዶነት እንዳይለወጥ አንቲ አይስ(ፀረ በረዶ መጠቀም)
ዉሀ በራዲያተር ስንጨምር ሞተር በሚኒሞ ማሰራት@GhionAutomotive
ቺንጊያ መላላት መጥበቁን ማረጋገጥ
የራዲያተር ክዳንን በአግባቡ መግጠም

ማብራሪያዉ ይበልጥ ግልፅ እንዲሆንልዎት ቪዲዮዉን በዚህ

ሊንክ ዩቲዩብ ላይ በመግባት ይከታተሉ!

ግዮን አዉቶሞቲቭ!
@GhionAutomotive
2.1K viewsSam Bob, 04:12
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-17 13:42:52 የመንጃ ፍቃድ ትምህርት
ንድፈ ሀሳብ - ክፍል 3

የማቀዝቀዣ ክፍሎች
ሞተር የማቀዝቀዝ ሂደትና አይነቶች
በዉሀ የማቀዝቀዝ ዘዴ/ በአየር የማቀዝቀዝ ዘዴ
ራዲያተር
የራዲያተር ክዳን
ፕሬዠር ቫልቭ/ ቫኪዩም ቫልቭ
ዋተር ፓምፕ
ሞተር ከመጠን በላይ የሚሞቅባቸዉ ምክንያቶች(Engine Overheating)
ለማቀዝቀዣ ክፍሎች መደረግ ያለበት ጥንቃቄ
.
.

ሊንኩን

ተጭነዉ ትምህርቱን በዝርዝር ይከታተሉ! ቻናላችንን ሰብስክራይብ ያድርጉ!

ግዮን አዉቶሞቲቭ!
@Ghionautomotive
1.7K viewsSam Bob, 10:42
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-05 07:35:02 የመንጃ ፍቃድ ትምህርት
ንድፈ ሀሳብ - ክፍል 2

የነዳጅ አስተላላፊ ክፍሎች

ሞተር በትክክል ሀይል የማመንጨት ተግባር እንዲያከናዉን ከሚያስችሉት ሀይል አጋዥ ክፍሎች መካከል የነዳጅ አስተላላፊ ክፍሎች ይጠቀሳሉ።

የነዳጅ አስተላላፊ ክፍሎች የምንላቸዉ ከነዳጅ ማጠራቀሚያ ጋን እስከ ኮምበስሽን ቻምበር ወይም ሲሊንደር ድረስ ያሉትን ክፍሎች ሲሆን በሚገኙበት የሞተር አይነት በሁለት ይከፈላሉ።@Ghionautomotive

እነርሱም:-
የቤንዚን ሞተር የነዳጅ አስተላላፊ ክፍሎችና የናፍጣ ሞተር የነዳጅ አስተላላፊ ክፍሎች ናቸዉ።

በቅድሚያ የቤንዚን ሞተር የነዳጅ አስተላላፊ ክፍሎችን በዝርዝር እንመልከት።

ሳልቫትዮ(የነዳጅ መያዣ ጋን):- ተሽከርካሪዉ ሀይል ማምረት እንዲችል የሚያደርገዉን ነዳጅ ማለትም ቤንዚን የሚይዝ የነዳጅ አስተላላፊ ክፍል ነዉ።@Ghionautomotive

fuel line(የነዳጅ መስመር):- ከነዳጅ ማጠራቀሚያ ጋን ወደ ፓምፕና ካርቡሬተር ነዳጅን የሚያስተላለፍ ነዳጅ አስተላላፊ ቱቦ ነዉ።

ፊልትሮ(የነዳጅ ማጣሪያ):- ወደ ካርቡሬተርና ሲሊንደር የሚገባዉን ነዳጅ የሚያጣራ ክፍል ነዉ።@Ghionautomotive

ፖምፔታ(የነዳጅ ፓምፕ):- ነዳጅን ከሳልቫትዮ በመሳብ በግፊት ሀይል ወደ ካርቡሬተር የሚያስተላልፍ ክፍል ነዉ።

ካርቡሬተር:- Carburetor በGasoline engine ወይም የቤንዚን ሞተር ላይ ብቻ የሚገኝ ሲሆን ዋና አገልግሎቱም አየር እና ነዳጅን መጥኖ በማዋሀድ ወደ ሲሊንደር እንዲገባ ማድረግ ነዉ።@Ghionautomotive

የካርቡሬተር ክፍሎች
ቾክ ቫልቭ:- በካርቡሬተር የላይኛዉ ክፍል በመገጠም የአየር ማስገቢያን ለመዝጋት ወይም ለመክፈት የሚያገለግል ሲሆን ጠዋት በቅዝቃዜ ጊዜ ሞተር ስናስነሳ የአየሩ መጠን አንሶ የነዳጁ መጠን መብዛት ስላለበት የአየር መተላለፊያዉን በመዝጋት ሞተር ቶሎ እንዲነሳ የሚያደርግ ክፍል ነዉ።@Ghionautomotive

ፍሎት ቦል(ተንሳፋፊ ኳስ):- በካርቡሬተር ዉስጥ መጠኑን የጠበቀ ነዳጅ እንዲኖር የሚቆጣጠር ክፍል ነዉ።

ቬንቹሪ:- በካርቡሬተር ዉስጥ አየርና ነዳጅ ተመጥነዉ የሚደባለቁበት ጠባብ የካርቡሬተር ክፍል ነዉ።

የventuri ወይም ጠባቧ የcarburetor ክፍል የአየሩ ፍጥነት እንዲጨምር እና ግፊቱ እንዲቀንስ በማድረግ ነዳጅና አየር እንዲቀላቀል ያደርጋል።@Ghionautomotive

ይህም carburetor በበርኖሊ ህግ ወይም Bernoulli's principle አማካኝነት እንደሚሰራ የሚያሳይ ሲሆን

Bernoulli's principle አየር ፍጥነቱ በሚጨምርበት ጊዜ ግፊቱ እንደሚቀንስ ያስቀምጣል።@Ghionautomotive

ትሮትል ቫልቭ:- ከነዳጅ መስጫዉ ፔዳል ጋር የተያያዘ ሲሆን በቬንቹሪ ዉስጥ የተቀላቀለዉ የነዳጅና የአየር ድብልቅ ወደ ሲሊንደር ዉስጥ ሲገባ መጠኑን ለመጨመርና ለመቀነስ የምንጠቀምበት ቫልቭ ነዉ።

የካርቡሬተር ፒስተን:- የventuri የጎን ስፋት እንዲጨምርና እንዲቀንስ ያደርጋል።@Ghionautomotive

main jet:- ነዳጅ ወደ venturi እንዲተላለፍ ያደርጋል።

idler channel:- ተሽከርካሪ በሚኒሞ እየሰራ አየር የሚያልፍበት ክፍል ነዉ።

Neddle jet:- እንደ carburetor ፒስተን እንቅስቃሴ main jet እንዲከፈት እና እንዲዘጋ የሚያደርግ ሲሆን ተሽከርካሪ በሚኒሞ ሲሰራ main jetን በመዝጋት ነዳጅ ወደ venturi እንዳያልፍ የሚያደርግ ሲሆን አየር ደግሞ በidler channel እንዲያልፍ ያደርጋል።@Ghionautomotive

ዲፕራተር(የአየር ማጣሪያ):- በካርቡሬተር የላይኛዉ ክፍል ላይ በመሆን ሶስት ተግባራትን ያከናዉናል:-
1, ወደ ካርቡሬተር(ሲሊንደር የሚገባዉን አየር ያጣራል።
2, በካርቡሬተር አናት በኩል የሚነሳዉን እሳት ያስቀራል።
3, ከሞተር አካባቢ ሊነሳ የሚችልን ድምፅ አፍኖ ያስቀራል።@Ghionautomotive

የናፍጣ ሞተር ሀይል አስተላላፊ ክፍሎች

ሳልቫትዮ(የነዳጅ ማጠራቀሚያ ጋን):- ሞተር ሀይል ለማምረት የሚያስችለዉን በቂ ነዳጅ የሚይዝ ክፍል ነዉ።@Ghionautomotive

ፊድ ፓምፕ(መጋቢ ፓምፕ):- ነዳጅን ከነዳጅ ማጠራቀሚያ ጋን ስቦ በፊልትሮ በኩል በአነስተኛ ግፊት ለኢንጀክሽን ፓምፕ የሚያደርስ የነዳጅ አስተላላፊ ክፍል ነዉ።@Ghionautomotive

ፊልትሮ(የነዳጅ ማጣሪያ):- ነዳጅን በማጣራት ወደ ኢንጀክሽን ፓምፕ እንዲደርስ የሚያደርግ ክፍል ነዉ።

በናፍጣ ሞተር ላይ ሁለት አይነት ማጣሪያዎች ያሉ ሲሆን እነርሱም:-
የመጀመሪያ ማጣሪያ እና የሁለተኛ ማጣሪያ ናቸዉ።@Ghionautomotive

በናፍጣ ሞተር ላይ ሁለት የነዳጅ ማጣሪያ ያስፈለገበት ምክንያት ናፍጣ ቆሻሻ የመሸከም ባህሪ ስላለዉ ነዉ።

ኢንጀክሽን ፓምፕ:- ከፊድ ፓምፕ(መጋቢ ፓምፕ) በአነስተኛ ግፊት የሚመጣዉን ነዳጅ ተቀብሎ በከፍተኛ ግፊት ወደ ኢንጀክተር ኖዝል(እኛቶሪ) የሚያስተላልፍ ክፍል ነዉ።@Ghionautomotive

ኢንጀክተር ኖዝል(እኛቶሪ):- ከኢንጀክሽን ፓምፕ በከፍተኛ ግፊት ተገፍቶ የመጣዉን ነዳጅ ተቀብሎ በጉም መልክ ወደ ሲሊንደር በመርጨት ሀይል እንዲፈጠር የሚያግዝ ክፍል ነዉ።

መላሽ መስመር:- በእያንዳንዱ ኢንጀክተር ኖዝል(እኛቶሪ) ላይ በመሆን በትርፍነት የሚገኘዉን ናፍጣ በማሰባሰብ ወደ ሳልቫትዮ የሚመልስ ክፍል ነዉ።@Ghionautomotive

ካንዴሊቲ(ግሉ ፕለግ):- በናፍጣ ሞተር ሲሊንደር ዉስጥ ተጨማሪ ሙቀት እንዲፈጠር በማድረግ ሞተር ቶሎ እንዲነሳ የሚያግዝ ክፍል ነዉ።

ለነዳጅ አስተላላፊ ክፍሎች መደረግ ያለበት ጥንቃቄ

የነዳጅ ክፍሎችን ንፅህና መጠበቅ
መስመሮቹ በጥብቅ የታሰሩና የማያፈሱ መሆናቸዉን ማረጋገጥ
ሳልቫትዮን ሁልጊዜም በትክክለኛዉ ክዳን መክደን
በሳልቫትዮ ምንጊዜም በቂ ነዳጅ እንዲኖር ማድረግ@Ghionautomotive

ማብራሪያዉ ግልፅ እንዲሆንልዎት ቨዲዮዉን በዚህ ሊንክ

ይመልከቱ!

ግዮን አዉቶሞቲቭ!
@GhionAutomotive
1.8K viewsSam Bob, 04:35
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-02 07:59:32 እንኳን ለ1443 ዓመት ሂጅራ የኢድ አልፈጥር በዓል በሰላም አደረሳችሁ! ለመላዉ የእስልምና እምነት ተከታዮች መልካም በዓል እንዲሆንላችሁ እንመኛለን!!
ዒድ ሙባረክ!

ግዮን አዉቶሞቲቭ!
@Ghionautomotive
1.4K viewsSam Bob, 04:59
ክፈት / አስተያየት ይስጡ