Get Mystery Box with random crypto!

የአማራ ኃይል ከመከላከያ ጋር እንዲዋጋ አንፈልግም፤ እንዲሁ መወጋትም አንፈልግም፤ ነገር ግን... | ሽፈራው የሶማው

የአማራ ኃይል ከመከላከያ ጋር እንዲዋጋ አንፈልግም፤ እንዲሁ መወጋትም አንፈልግም፤ ነገር ግን...


የምንቃወመው መንግስት፣ እኛን ለመውጋት የላከው ሌላ አካል ሳይሆን የመከላከያ ሰራዊት ወታደሮችን ነው። የተፈለገው ህግ የማስከበር ዘመቻ ቢሆን መከላከያ የሚሰማራበት አግባብ አልነበረም። ሆኖም የአብይ አስተዳደር የአቶ ግርማን ሞት ተከትሎ የወሰደው ከመጠን ያለፈ ውሳኔ [blown out of proportion] የሚባል ነው። ይህ ግን በስህተት የተፈጸመ ሳይሆን በዓላማ የተደረገ ነው።

ሁላችንም እንደምንረዳው በአማራ ክልል የተከፈተው ጦርነት አንዱ እና ዋነኛ አላማው አማራን በጉልበት በማንበርከክ ለብሔራዊ መብት እና ጥቅሙ መታገል የማይችል ደካማ እና ተለጣፊ ኃይል የማድረግ ነው። ሆኖም ጦርነቱ ካሉት ዘርፈ ብዙ መልኮች አንዱ በአማራ እና በመከላከያ ሰራዊት መካከል የተፈጠረውን የወዳጅነት ትምምን ማበላሸት ነው። ይህ ደግሞ መከላከያ በሀገራዊ ተቋምነቱ የሁሉ ጠባቂነቱ ቀርቶ ከሌላው ቀምቶ ለአገዛዙ ብቻ የሚቆም የማድረጉ ፕሮግራም አካል ነው።

መከላከያ በኦሮሚያ እና በትግራይ ክልል አሁን ደግሞ በአማራ እና ሶማሊያ ክልል በተለያዬ መልኩ ከሕዝብ ጋር ቀጥተኛ ግጭት ውስጥ እንዲገባ በማድረግ ሕዝባዊነቱን የመሸርሸሩ ተግባር ብዙ ርቀት ሄዷል።
ይህ ለእኔ ብቻ የሚለው ኬኛ ኃይል በአማራ ክልል ጦርነት ሲያውጅ በዚህ አግባብ የታሰበ እንደሆነ መረዳት ተችሏል። በዚህም ዕቅድ ምክንያት የአብይ አስተዳደርም ሆነ ጀሌዎቹ በህዝብ ሀይሎች እየቀረበ ያለውን የሰላም እና የውይይት ጥሪ ለማዳመጥ ፈቃደኞች አልሆኑም። አይሆኑም'ም።

በዚህ ጦርነት የአማራው ፍላጎት የአማራን ብሔራዊ መብት እና ፍትሃዊ ጥያቄ ማስከበር ነው። የዚህ ፍላጎት አንኳር ማጠንጠኛ ደግሞ የተጋረጠብን የህልውና አደጋ ነው። ይህ አደጋ ደግሞ ዛሬ በአማራ ክልል በተከፈተው ጦርነት የመጣ ሳይሆን ለአስርት ዓመታት የቆዬ ግን ደግሞ ባለፉት 5 ዓመታት በአስደንጋጭ ፍጥነት አድጎ እጅግ ከፍተኛ ጉዳት ያስከተለ ነው። ይህ ጦርነት የሁሉም ጥያቄዎች መልስ አይደለም፤ ሆኖም በከፋ ሁኔታ ተመትቶ ከመጥፋት ለመዳን የሚደረግ ተጋድሎ ነው። ስለዚህም ራስን ከጥቃት ከመከላከል ውጭ አማራጭ የለም።

ይህ ከመደበኛ የመንግስት ተቃውሞ የተለዬ ነው፣ ይህ ተራ ሕዝባዊ አመጽ አይደለም፣ ከዘወትራዊው የአማራ ጥቃት ከፍ ያለ አደጋን ያዘለ ነው። ስለዚህም ከማስቆም አለያም ከመመከት ውጭ አማራጭ የለም። ሆኖም ለማስቆምም ሆነ ለመመከት ሕዝቡ የመረጠው ለጥቃቱ አጸፋ ምላሽ ሰጥቶ ባለበት የማስቆም መንገድ ትክክለኛ እና የአብይ / ብልጽግና አስተዳደርን የማጥቃት ፍላጎት ሊከለክል የሚችል [ deterrence ] ስትራቴጂ ነው። ይህን ስትራቴጂ መደገፍ እና ለስኬቱ አጋዥ ሆነን መገኘት ይገባናል።

መከላከያ ጋር የተፈጠረውን የወዳጅነት ትምምን ሳይበላሽ እንዲቀጥል የቀውስ ኢንተርፕሩነሩን አስተዳደር መግታት ይገባል። አስተዳደሩ ሰላማዊም ሆነ ለአመጽ ፖለቲካ ትክክለኛ ምላሽ እንደማይሰጥ ታይቷል፤ ሆኖም ከሰላማዊ እንቅስቃሴ ይልቅ ለጉልበት የተሻለ መልስ እንደሚሰጥም ታይቷል። እናም መግባባት በሚቻልበት ቋንቋ መነጋገር ተገቢ ነውና በዚህ መንገድ መቀጠሉ አማራጭ የሌለው አካሄድ ነው።

ድል ለአማራ !

#AmharaStruggle
#Justice4Amhara
#AmharaGenocide