Get Mystery Box with random crypto!

ብርሃኑ ነገን ጨምሮ አብዛኛው ብልፅግና ውስጥ ያለ የደቡብ ልሒቅ ከኦሮሙማ ጎን ጎን የቆመው ተሸውዶ | ሽፈራው የሶማው

ብርሃኑ ነገን ጨምሮ አብዛኛው ብልፅግና ውስጥ ያለ የደቡብ ልሒቅ ከኦሮሙማ ጎን ጎን የቆመው ተሸውዶ ነው። የሚፀፀተው ፣ የሚባንነው ፣ የሚደነግጠው ወደፊት ነው።
የኦሮሙማ ሰዎች ለሁሉም የሚፈልገውን እና የሚመጥነውን ይነግራሉ። እንዳሉትም የሚያሳምነውን እና የሚያደናግረውን ያደርጋሉ።
"ኩሽ ናችሁ" በማለት የትብብርና አጋርነት ስሜት የፈጠሩባቸው ወይንም ሊፈጥሩባቸው የሞከሯቸው ነበሩ፣ አሉ። ብዙዎቹ ደቡቦች የዚህ ሰለባ ሲሆኑ ተጨማሪ ማስመጫም ቀርቦላቸዋል።
"ኢትዮጵያን ለ3ሺህ አመታት የበዘበዟት የሰሜን ፖለቲከኞች ይበቃቸዋል፤ የደቡብ ኢትዮጵያ ጭቁን ሕዝቦች የሚወስኑባት አገር እንድትመጣ አብረን እንቁም" ብለዋቸዋል። "ለደቡቦች ባለን አጋርነት ሁሉንም የደኢሕዴግ አመራር በስልጣን አስቀጥለናል" ይሏቸዋል።
በተለይ የሰሜኖቹ ትግሬና አማራ ፈላጭ ቆራጭነት ማብቃት አለበት የሚለውን ተቀብለው ዝም ጭጭ ያሉት ብዙ ናቸው።

▲ ብርሃኑ ነጋ የፌደራል ስርዓቱን እና ሕገመንግስቱን ለመቀየር የሚታገል የሚመስላቸው ብዙ ነበሩ ፤ በለየለት የዘረኝነት ወቅት አጡት።
▲ ብርሃኑ ነጋና መሠል ሰዎች ለሰብዓዊ መብቶች የሚታገሉ የሚመስላቸው ነበሩ፤ በሰብዓዊ ውድመት ዘመን አጡት።
▲ ብርሃኑ ነጋ እና መሰሎቹን የዲሞክራሲ ታጋዮች አድርገው የሚስሉ ነበሩ፣ በለየለት የአፈና ወቅት የሉም።

ሆኖም፣
ያልተሸወዱት፣ ነገ እነሱን ሊውጣቸው የመጣ ዘንዶ መኖሩን የተረዱት፣ ሐቀኞቹ የደቡብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ትግል ላይ ናቸው። አደጋውን እንደአማራው ሕዝብ እያዪትና እየቀመሱት በመሆኑ ትግል ላይ ናቸው።
ያለው ትግል የሴሜቲክ-ኩሽቲክ፣ የሙስሊም-የክርስቲያን፣ የሰሜን-የደቡብ ሳይሆን የኢትዮጵያውያን የፀረ-ጭቆናና ሕልውና መረጋገጥ ትግል ነው !!


ድል ለአማራ !

#AmharaStruggle
#Justice4Amhara
#AmharaGenocide