Get Mystery Box with random crypto!

ትምህርታቸውን አቋርጠው የቆዩ የወልዲያ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ግቢውን ለቀው እየወጡ መሆኑ ታወቀ! | QesemAcademy

ትምህርታቸውን አቋርጠው የቆዩ የወልዲያ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ግቢውን ለቀው እየወጡ መሆኑ ታወቀ!

በወልዲያ ዩኒቨርሲቲ በሰሜኑ የሃገሪቱ ክፍል በነበረው ጦርነት ሳቢያ የባከነው የትምህርት ዘመን በሚካካስበት ሁኔታ ላይ የሁለተኛ አመት ተማሪዎች እና የዩኒቨርሲቲው አስተዳደር መስማማት አልቻሉም።በጦርነቱ ሳቢያ ተቋርጦ የነበረውን የሁለት ዓመት ትምህርት በተጣበበ ፕሮግራም በአንድ ዓመት ውስጥ ተምረን መጨረስ አለብን የሚሉት ተማሪዎች ከዩኒቨርሲቲው ውሳኔ ጋር ባለመስማማታቸው ግቢውን ለቀው እየወጡ መሆናቸውን የወልዲያ ዩኒቨርሲቲ አስታወቋል።

ከሁለተኛ አመት ተማሪዎች መካከል ትምህርታቸውን እየተከታተሉ ከሚገኙ ከህግ፣ ከጤና፣ ከአርክቴክቸር እና ከልዩ ፍላጎት አካቶ ተማሪዎች ውጭ ያሉት ተማሪዎች በዩኒቨርሲቲው ፕሮግራም መሰረት ለመማር ፍላጎት ባለማሳየታቸው ለሁለት ሳምንታት ያክል ትምህርታቸውን አቋርጠው ቆይተዋል።ወልዲያ ዩኒቨርሲቲ በጦርነቱ በደረሰበት ከፍተኛ ውድመት ቤተ ሙከራዎች አገልግሎት መስጠት የማይችሉ በመሆናቸው፣ የትምህርት ሚኒስቴር የተጣበበ የትምህርት የጊዜ ሰሌዳ እንዳይኖር ለሁሉም የከፍተኛ የትምህርት ተቋማት በደብዳቤ በማሳወቁ የተማሪዎች ጥያቄ ተቀባይነትን ሳያገኝ ቀርቷል ተብሏል።

በቀጣይ የሚሰጠው የመውጫ ፈተናና የትምህርት ጥራት ጉዳይ በተማሪዎቹ ላይ የሚያሳድረው ተፅዕኖ እና የየትምህርቶቹ የኮርስ ባህሪ መለያየት እንዲሁም የጊዜ እጥረት ጋር ተያይዞ ጥያቄያቸው ባለመስተናገዱ መማር የሚፈልጉ እንዲቀጥሉ፣ መማር የማይፈልጉ ደግሞ ግቢውን ለቀው እንዲወጡ ዩኒቨርሲቲው ውሳኔ አስተላልፏል።የዩኒቨርሲቲውን ውሳኔ ተከትሎ ከሁለተኛ አመት ተማሪዎች መካከል ከፊሎቹ ትላንት ማለትም ጥር 19 ቀን 2015 ዓ.ም ጀምሮ ግቢውን ለቀው እየወጡ ናቸው ተብሏል።

ከHigh school  እስከ Campus አብረናችሁ ነን !
SHARE SHARE
╔════════════╗
JOIN: @QesemAcademy
JOIN: @QesemAcademy
╚════════════╝