Get Mystery Box with random crypto!

አሃ ፡ አሃሃ ፡ ያኔ ፡ እንደወደደኝ አሃ ፡ አሃሃ ፡ ዛሬም ፡ ይወደኛል አሃ ፡ አሃሃ ፡ የእኔ | Pure_Christianity

አሃ ፡ አሃሃ ፡ ያኔ ፡ እንደወደደኝ
አሃ ፡ አሃሃ ፡ ዛሬም ፡ ይወደኛል
አሃ ፡ አሃሃ ፡ የእኔ ፡ ጌታ ፡ ፍቅሩ
አሃ ፡ አሃሃ ፡ መች ፡ ቀንሶ ፡ ያውቃል

አሃሃ ፡ እርሱ ፡ ያው ፡ ነው ፡ አልተለዋወጠም
አሃሃ ፡ ምህረቱ ፡ ዛሬም ፡ አልጐደለም
አሃሃ ፡ እርሱ ፡ ያው ፡ ነው ፡ አልተቀያየረም
አሃሃ ፡ ቸርነቱ ፡ ዛሬም ፡ አልጐደለም

ያኔ ፡ በመስቀል ፡ ላይ ፡ ሆኖ ፡ ኤሎሂ ፡ ያለላት
ከሲዖል ፡ እንድትድን ፡ ወዶ ፡ የተሟገተላት
ሞቶ ፡ እስከሚቀበር ፡ ድረስ ፡ የወደዳት ፡ ነፍሴ
ትገዛለታለች ፡ ዛሬም ፡ እያለች ፡ ንጉሤ

ወዶኛልና ፡ አዳነኝ
እያለች ፡ ቅኔ ፡ ስትቀኝ
ላልተለወጠው ፡ ማንነትህ
ምሥጋናም ፡ አላት ፡ ለምህረትህ (፪x)

አዝ፦ አሃ ፡ አሃሃ ፡ ያኔ ፡ እንደወደደኝ
አሃ ፡ አሃሃ ፡ ዛሬም ፡ ይወደኛል
አሃ ፡ አሃሃ ፡ የእኔ ፡ ጌታ ፡ ፍቅሩ
አሃ ፡ አሃሃ ፡ መች ፡ ቀንሶ ፡ ያውቃል

አሃሃ ፡ እርሱ ፡ ያው ፡ ነው ፡ አልተለዋወጠም
አሃሃ ፡ ምህረቱ ፡ ዛሬም ፡ አልጐደለም
አሃሃ ፡ እርሱ ፡ ያው ፡ ነው ፡ አልተቀያየረም
አሃሃ ፡ ቸርነቱ ፡ ዛሬም ፡ አልጐደለም

በሕይወቴ ፡ ውጣ ፡ ውረድ ፡ ባልፍም ፡ በመከራ
እርሱ ፡ ፈፅሞ ፡ አልተወኝም ፡ አለ ፡ ከእኔ ፡ ጋራ
ዓመት ፡ ዘመን ፡ ቢለዋወጥ ፡ ቀንም ፡ በቀን ፡ ላይ
እንከን ፡ አላየሁበትም ፡ ውዴም ፡ ፍቅሩ ፡ ላይ

በምህረቱ ፡ ባለጠጋ
ሆኖ ፡ አየሁ ፡ ወደ ፡ እርሱ ፡ ስጠጋ
አይጨምርም ፡ አይቀንስ ፡ ፍቅሩ
እርሱ ፡ ያው ፡ ነው ፡ በዘመኑ (፪x)

@pure_Christianity