Get Mystery Box with random crypto!

መንፈስ ቅዱስ በእኔ ውስጥ አለ ብለህ የምታምን ሆይ ታዲያ ምነው ሀጢያት እንደሌለብህና ፍፁም ንፁህ | Pure_Christianity

መንፈስ ቅዱስ በእኔ ውስጥ አለ ብለህ የምታምን ሆይ ታዲያ ምነው ሀጢያት እንደሌለብህና ፍፁም ንፁህ መሆንህን ማመን ከበደህ? መይንስ መንፈስ ቅዱስ ከሀጢያት ጋር የሚስማማ ነው? አንተ በክርስቶስ ስራ ምክንያት በደሙ ፈፅሞ ንፁህና ቅዱስ ባትሆን አስቀድሞም መንፈስ ቅዱስ በአንተ ውስጥ ባላደረ ነበር። መንፈስ ቅዱስ ወደ አንተ የመጣው የክርስቶስ የመስቀል ላይ ስራ ስለተጠናቀቀ ነው። ስለዚህ አንተ ንፁህና ቅዱስ መሆንህን መንፈስ ቅዱስ አንተ ውስጥ በማደር አረጋግጦልሀልና አንተም ፍፁም የሆነ ንፅህናና ቅድስና እንዳለህ አምነህ ተቀበል። አደራህን ከየት አምጥቼው ነው እንዳትለኝ የክርስቶስ ፍፁም ንፅህናን መቀበልህንና የአንተን ሀጢያት እርሱ መውሰዱን ዘንግተህ። አንተ ንፁህና ፃዲቅ ነህ። ይህ የሆነው ኢየሱስ ክርስቶስን በማመንህ ብቻ ነው።
@Pure_Christianity
@Pure_Christianity