Get Mystery Box with random crypto!

ዕብራውያን 9 (13-14) የውጭ አካላቸው ይነጻ ዘንድ በረከሱ ሰዎች ላይ የሚረጨው የፍየሎችና የኮ | Pure_Christianity

ዕብራውያን 9 (13-14)
የውጭ አካላቸው ይነጻ ዘንድ በረከሱ ሰዎች ላይ የሚረጨው የፍየሎችና የኮርማዎች ደም እንዲሁም የፍየሎችና የጊደር ዐመድ የሚቀድሳቸው ከሆነ፣በዘላለም መንፈስ አማካይነት ራሱን ነውር አልባ መሥዋዕት አድርጎ ለእግዚአብሔር ያቀረበው የክርስቶስ ደም ሕያው እግዚአብሔርን እንድናመልክ ኅሊናችንን ከምውት ሥራ እንዴት ይበልጥ ያነጻ ይሆን! ሀሌሉያ!

ክርስቶስ ኢየሱስ በመስቀል ላይ ያፈሰሰው ደም ህሊናህን ፈፅሞ ሀጢያተኛ ነኝ ከሚል አስተሳሰብ ማንፃት ካልቻለ ቀራኒዮ መስቀል ላይ የቀረበው መስዋዕት በብሉይ ኪዳን ይቀርቡ ከነበሩ ከእንስሳት መስዋዕቶች የተለየ ዋጋ አልሠጠኸውም።

ዕብራውያን 9 (24-28)
ክርስቶስ የእውነተኛዪቱ ድንኳን ምሳሌ ወደ ሆነችውና በሰው እጅ ወደ ተሠራችው መቅደስ አልገባም፤ ነገር ግን አሁን ስለ እኛ በእግዚአብሔር ፊት ለመታየት፣ ወደ እርሷ ወደ ሰማይ ገባ።ሊቀ ካህናት የራሱ ያልሆነውን ደም ይዞ በየዓመቱ ወደ ቅድስተ ቅዱሳን እንደሚገባ፣ #ክርስቶስ #ራሱን #ብዙ_ጊዜ_መሥዋዕት_ለማድረግ_ወደ_ሰማይ_አልገባም። እንዲህ ቢሆን ኖሮ፣ ዓለም ከተፈጠረ ጀምሮ ክርስቶስ ብዙ ጊዜ መከራን መቀበል ባስፈለገው ነበር። አሁን ግን በዘመናት መጨረሻ ራሱን መሥዋዕት በማድረግ #ኀጢአትን #ለማስወገድ #ለአንዴና #ለመጨረሻ #ጊዜ #ተገልጦአል።ሰው አንድ ጊዜ ሊሞት ከዚያም በኋላ በፍርድ ፊት ሊቆም ተወስኖበታል። #ክርስቶስ_የብዙ_ሰዎችን_ኀጢአት_ለመሸከም፣ እንዲሁ አንድ ጊዜ መሥዋዕት ሆኖአል፤ ሁለተኛ ጊዜም ይገለጣል፤ ይህም ለሚጠባበቁት ድነትን ለማምጣት #እንጂ #ኀጢአትን #ለመሸከም #አይደለም።
አሜን
ኢየሱስ መስቀል ላይ በመሞቱ የትናንት የዛሬና የነገ ሀጢያትህን አስወግዶታል። ክርስቶስን እያመንክ አሁንም ሀጢያተኛ እንደሆንክ የምታስብ ከሆነ ክርስቶስ ከእንግዲህ ወዲህ ስለሀጢያ መስዋት ሆኖ ስለማይቀርብ ታዲያ እንዴት ይሆን ከሀጢያትህ የምትድነው? ይሄንን እውነት አጥብቀህ ያዘው። ክርስቶስ ኢየሱስ ሀጢያትህን ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ አስወግዶታል።
@Pure_Christianity
@Pure_Christianity