Get Mystery Box with random crypto!

ስትደክም የሚያዝንልህና የሚሳሳልህ ፀጋና ምህረትን እየሠጠ የሚደግፍህ አሸናፊ ሆነህ እንድትኖር የሚ | Pure_Christianity

ስትደክም የሚያዝንልህና የሚሳሳልህ ፀጋና ምህረትን እየሠጠ የሚደግፍህ አሸናፊ ሆነህ እንድትኖር የሚችለውን ሁሉ የሚያደርግ አባትህ እንጂ። ስትሳሳት ሊቀጣህ የተዘጋጀ ምህረት የማያውቅ በስህተትህ ሊራራልህ የማይችል ሁልጊዜ አንተን በመውቀስ ብቻ የሚኖር አባት የለህም!! ሁልጊዜም ልጄ አንተ ብርቱ ነህ ይልሀል። እኔ የሞትኩልህ አንተ በህይወት እንድትኖር ነው። የኔ አላማ አንተን ማዳን ነው እንጂ መግደል አይደለም። ሀጢያት አንተን ስለሚጎዳህ ልትሸሸው ይገባሀል በዚህ ጊዜ ደግሞ እኔ ያንተ ረዳት ነኝ። ከሀጢያት ጋር ተስማምተህ እንዳትኖር ምክንያቱም ያንተ ማንነት ፅድቅ እንጂ ሀጢያት አይደለም። አንተ የተፈጠርከው ለፅድቅ ነው። ስለዚህ እኔ ለ አንተ ጋሻህ ነኝ በዚህም ምክንያት አንተ አሸናፊ ነህ። በፍፁም ወደኔ ከመምጣት ተስፋ አትቁረጥ አንተን ማዳን የምችለው እኔ ብቻ ነኝ። የአምላክህ የልብ ንግግር ይሄን ይመስላል...አንተ የተወደድክ ነህ!
@Pure_Christianity
@Pure_Christianity