2022-07-28 11:54:01
ኢየሱስ የመጣው ለመሞት ሳይሆን እኛን ለመግደል ነው!!!!=======================================
#የሞተስ_ከኃጢአቱ_ጸድቋልና።” ሮሜ 6፥6
የፀደቅነው ኢየሱስ ስለሞተ ሳይሆን እኛ ስለሞትን ነው፤ የኢየሱስ መሞት ብቻውን አላፀደቀንም። *ይሄ ምን ማለት ነው??
ኢየሱስ ለመሞት አልመጣም እኛን ለማዳን እንጂ
ኢየሱስ ለመዋረድ አልመጣም እኛን ለማክበር እንጂ
ኢየሱስ ዝቅ ለማለት አልመጣም እኛን ከፍ ለማድረግ እንጂ። የኢየሱስ አላማ አሁን እኛ የሆንነው ነው እንጂ ያኔ እርሱ የሆነው አይደለም፤ እና ለመዋረድ አልመጣም ስል ምን እያልኩ ነው?
ሲጀመር እርሱን ማንም አጨብጭቦና ተስማምቶ አላከበረውም ልክ እንደዚሁ የሮም ወታደሮችም ይሁን ሌሎች ተስማምተው አያዋርዱትም!! ያከበረው አባቱ ነው እንጂ አህዛብም ይሁኑ አይሁድ አይደሉም።አለም ሳይፈጠር በፊትም የከበረ ነበር፤ ክብር የሚለው #ቃል ሳይኖር እርሱ ከብሮ ይኖር ነበር!!
ነገር ግን እኛን ከፍ ለማድረግ ከነበረው ከፍታ፥ የነበርንበት ዝቅታ ድረስ መውረድ ነበረበት። ልክ አንድ እቃ ወድቆብን ልናነሳው ዝቅ እንላለን የዛኔ አላማው የእኛ ዝቅ ማለት ሳይሆን የእቃው መነሳት ነው ስለዚህ ያ እቃ በወደቀበት ዝቅታ ልክ ዝቅ ማለታችን የግድ ይሆናል።
ልክ እንደዚሁ ኢየሱስ የመምጣቱ አላማ፣ ዝቅ ለማለት ሳይሆን እኛን ከፍ ለማድረግ ነው።
ወደ መጀመርያው ሀሳብ ስመጣ ደግሞ፣ ኢየሱስ የመጣው ለመሞት ሳይሆን እኛን ለመግደል ነው። ይህንን ስል እርሱ ከመምጣቱ በፊት ለህግ ለሀጥያት,ለርኩሰት ባጠቃላይ ለጨለማው ዓለም ህያው የነበርን፥ለእግዚአብሔር ዓለም ግን ሙት የነበርን ሰዎች በኤፌ 2:1-2 እንደሚለው "በበደላችንና በኃጥያታችን ሙታን (ለእግዚአብሔር ዓለም)፤ በማይታዘዙ ልጆች ላይ ለሚሰራው መንፈስ ግን ህያው ሆነን የምንመላለስ የነበርንን ሰዎች ለህግና ለሀጥያት ገድሎን ለራሱ ህያው ሊያደርገን ወደደ።
ስለዚህም የራሱን ስጋ ተጠቅሞ እኛን ገደለ። “እንዲሁ፥ ወንድሞቼ ሆይ፥ እናንተ ደግሞ በክርስቶስ ሥጋ ለሕግ ተገድላችኋል፤ ለእግዚአብሔር ፍሬ እንድናፈራ፥ እናንተ ለሌላው፥ ከሙታን ለተነሣው፥ ለእርሱ ትሆኑ ዘንድ።” ሮሜ 7፥4
ለዛ ነው የሞተስ ከሀጥያቱ ፀድቋል የሚለን፤ በክርስቶስ ስጋ ሆነን ሞተናል፤ መሞታችንንም ስናምን መፅደቃችንን እናውቃለን። ገላ 2:20 "ከክርስቶስ ጋር ተሰቅያለሁ፤ እኔም አሁን ህያው ሆኜ አልኖርም ክርስቶስ ግን በእኔ ይኖራል"።
በአዳም ወገብ ሆነን ለፅድቅ ሞተን እንደነበረ ሁሉ፤ በክርስቶስ ወገብ ሆነን ለኃጥያት ሞተናል። ሮሜ 7:6
ስለዚህ ኢየሱስ የመጣው ለመሞት ሳይሆን በስጋው በኩል እኛን ለጨለማው አለም ገድሎ ለራሱ ዓለም ህያው ሊያደርገን ነው። #አላማው_የእርሱ_መሞት_ሳይሆን_የእኛ_መገደል_ነው።
የመረጃ ምንጭ Hani Kurabachew Facebook page የተወሰደ መልዕክት ነው።http://t.me/PRAISE_TO_OUR_GOD
793 viewsInternational Evangelist Ephraim G. Jesus, edited 08:54