Get Mystery Box with random crypto!

እግዚአብሔር_ጽድቅ ክፍል ሶስት #የእግዚአብሔር_ጽድቅ_በእምነት_ወይስ_በኦሪት_ሕግ | የእግዚአብሔር ጸጋ ወንጌል\ The Gospel of the grace of God\


እግዚአብሔር_ጽድቅ

ክፍል ሶስት

#የእግዚአብሔር_ጽድቅ_በእምነት_ወይስ_በኦሪት_ሕግ_ነው?

“ሰው በኢየሱስ ክርስቶስ በማመን እንጂ፣ ሕግን በመጠበቅ እንደማይጸድቅ እናውቃለን። ስለዚህ ሕግን በመጠበቅ ሳይሆን፣ በክርስቶስ በማመን እንጸድቅ ዘንድ እኛም ደግሞ በክርስቶስ ኢየሱስ አምነናል፤ ሕግን በመጠበቅ ማንም አይጸድቅምና።”
— ገላትያ 2፥16 (አዲሱ መ.ት)

ሐዋርያው ጳውሎስ በገላ.2፥16 ላይ ያለው ሀሳብ ስንመለከት በዚህ ጥቅስ ላይ ሦስት ጊዜ ሕግን በመጠበቅ መጽደቅ እንደማይቻል ሲያመለክት፣ ሦስት ጊዜ ደግሞ በክርስቶስ ማመን ፍጹም አስፈላጊ መሆኑን ይናገራል።

ሐዋርያው ጳውሎስ በሮሜ 3፥22 ላይ በግልጽ እንደተናገረው የእግዚአብሔር ጽድቅ በኢየሱስ ክርስቶስ በማመን የሚገኝ ጽድቅ ሲሆን ይህን የእግዚአብሔር ጽድቅ መቀበል የሚቻለው በእምነት ብቻ ነው።

ማንም ሰው በሕግ ስራ በመሥራት በእግዚአብሔር ፊት ጻድቅ መሆን እንደማይቻል በግልጽ ይናገራል።
ሕጉ ሰው የማጽደቅ አቅም ሆነ ብቃት የለውም።

ማንም ሰው በሕግ ስራ በመስራት መጽደቅ እንደማይችል ከታወቀ እንግዲያውስ ሰው የእግዚአብሔር ጽድቅ ተካፋይ መሆን የሚቻለው በእምነት እንጂ በሕግ ስራ አይደለም።

“እስቲ አብርሃምን አስቡ፤ “እርሱ እግዚአብሔርን አመነ፤ ጽድቅም ሆኖ ተቈጠረለት።””
— ገላትያ 3፥6 (አዲሱ መ.ት)

ሮሜ 4 (አዲሱ መ.ት)
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
⁴ አንድ ሰው ሥራ ከሠራ ደመወዙ እንደ ስጦታ ሳይሆን እንደ ተገቢ ዋጋው ይቈጠርለታል።
⁵ ነገር ግን ለማይሠራው፣ ኃጥኡን ሰው ጻድቅ በሚያደርግ በእግዚአብሔር ለሚያምን ሰው፣ እምነቱ ጽድቅ ሆኖ ይቈጠርለታል።

ሐዋርያው ጳውሎስ በሮሜ 4፥4-5 ላይ በግልጽ እንደተናገረው ለኃጥኡን ሰው ጻድቅ የሚያደርገው በእምነቱ እንጂ በስራ አይደለም። አንድ ሰው በእምነት የእግዚአብሔር ጽድቅ ተካፋይ ከሆነ በኋላ ዳግመኛ ሀጢአተኛ ሊሆን አይችልም፤ ምክንያቱም ደግሞ በክርስቶስ ኢየሱስ በማመኑ የእግዚአብሔር ጽድቅ ተብሏል።

ሐዋርያው ጳውሎስ እንዳለው የእግዚአብሔር ጽድቅ መቀበል የሚቻለው በእምነት እንጂ የኦሪት ሕግ በመጠበቅ አይደለም።

ሮሜ 9 (አዲሱ መ.ት)
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
³⁰ እንግዲህ ምን እንበል? በእምነት የሆነውን ጽድቅ፣ ለጽድቅ ያልደከሙት አሕዛብ አገኙት፤
³¹ ነገር ግን የጽድቅን ሕግ የተከታተሉት እስራኤል አላገኙትም።

በእግዚአብሔር ጽድቅ ያለ ስራ እና ያለ ጥረት የመቀበል የሚቻለው በእምነት ብቻ ነው።

“ሕግ በመጠበቅ የሚገኝ የራሴ ጽድቅ ኖሮኝ ሳይሆን፣ በክርስቶስ በማመን ይኸውም ከእግዚአብሔር የሚመጣ፣ ከእምነትም በሆነ ጽድቅ በእርሱ ዘንድ እንድገኝ ነው።”
— ፊልጵስዩስ 3፥9 (አዲሱ መ.ት)

ይቀጥላል
የእግዚአብሔር ሰው ኤፍሬም ገ/ኢየሱስ

Join and follow
https://t.me/+LUMYTeZz9lk2MzM8


ምዕራፍ አንድ
#የእግዚአብሔር_ጽድቅ

#ክፍል=አንድ
#ጽድቅ_ምንድነው? (መግቢያ)

https://t.me/PRAISE_TO_OUR_GOD/3035

ክፍል ሁለት
#በእምነት_የሚገኝ_ጽድቅ

https://t.me/PRAISE_TO_OUR_GOD/3036