Get Mystery Box with random crypto!

#ሳልወድህ_የወደድከኝ =================== ሳልወድህ የወደድከኝ ሳልመርጥህ የመረጥ | የእግዚአብሔር ጸጋ ወንጌል\ The Gospel of the grace of God\

#ሳልወድህ_የወደድከኝ
===================
ሳልወድህ የወደድከኝ ሳልመርጥህ የመረጥከኝ
በከበረው ደም ገዝተህ እንዲያው ልጅህ ያረከኝ
አበሳዬን አራከው ቀንበሬን ሰባበርከው
(ፍቅርህ ለእኔ ልዩ ነው ስምህን ላሞጋግሰው) (፪x)

ኃጢአተኛ ሳለሁ ጽድቅ የማይገባኝ
መርገሜን ወሰደው ኢየሱስ በደሙ አነጻኝ
የከሰሰኝ ጠላት እግሬ ስር ወደቀ
በረሃው ሕይወቴ ምንጭን አፈለቀ

ሳልወድህ የወደድከኝ ሳልመርጥህ የመረጥከኝ
በከበረው ደም ገዝተህ እንዲያው ልጅህ ያረከኝ
አበሳዬን አራከው ቀንበሬን ሰባበርከው
(ፍቅርህ ለእኔ ልዩ ነው ስምህን ላሞጋግሰው) (፪x)

የዕዳ ጽህፈቴን በደሙ ደምስሶ
ጠላቴን በእጄ እረግጦ ሰጠኝ አሳልፎ
ጽኑ ስልጣን አለኝ የአምላክ ልጅ ሆኛለሁ
የፈታኝን ጌታ ተፈትቸ አከብረዋለሁ

ሳልወድህ የወደድከኝ ሳልመርጥህ የመረጥከኝ
በከበረው ደም ገዝተህ እንዲያው ልጅህ ያረከኝ
አበሳዬን አራከው ቀንበሬን ሰባበርከው
(ፍቅርህ ለእኔ ልዩ ነው ስምህን ላሞጋግሰው) (፪x)

ለዚህ የሚያበቃ ጽድቅ እንኳን ሳይኖረኝ
በሰማዩ ስፍራ በቀኙ እንዲሁ አከበረኝ
ምህረቱ ብዙ ይሄ ታላቅ ጌታ
ከእኔ ጋር ሆናችሁ በዜማ አክብሩት በልልታ

ሳልወድህ የወደድከኝ ሳልመርጥህ የመረጥከኝ
በከበረው ደም ገዝተህ እንዲያው ልጅህ ያረከኝ
አበሳዬን አራከው ቀንበሬን ሰባበርከው
(ፍቅርህ ለእኔ ልዩ ነው ስምህን a ላሞጋግሰው) (፪x)

(ዘማሪ #ተስፋዬ ጫላ)

Join and follow
https://t.me/+LUMYTeZz9lk2MzM8