Get Mystery Box with random crypto!

@whoweareinchrist #እንደሚያስፈልግህ_ያውቃል ማቴዎስ 6 (አዲሱ መ.ት) ³¹ ስለዚህ | የእግዚአብሔር ጸጋ ወንጌል\ The Gospel of the grace of God\

@whoweareinchrist
#እንደሚያስፈልግህ_ያውቃል
ማቴዎስ 6 (አዲሱ መ.ት)
³¹ ስለዚህ፣ ‘ምን እንበላለን? ምን እንጠጣለን? ምንስ እንለብሳለን?’ ብላችሁ አትጨነቁ፤
³² አሕዛብ እነዚህን ነገሮች ሁሉ ለማግኘት ይጨነቃሉና፤ #የሰማዩ #አባታችሁም #እነዚህ #ሁሉ #ለእናንተ #እንደሚያስፈልጓችሁ #ያውቃል።
መብል መጠጥ እና ልብስ የብዙ ሰው ጥያቄ ነው እንደውም ከዛም አልፎ ብዙ ሰው ምን እበላለው ምን እጠጣለሁ ምንስ እለብሳለው ብሎ ይጨነቃል።
ለዚህ ደግሞ ቅዱሱ መፅሐፍ የሰጠን መፍትሄ አይዞህ ጌታ ከከበረ ባትበላም ችግር የለውም ፣ ራቁትህን ብትሆንም አንድ ቀን ሰማይ ቤት ታርፋለህ የሚል የሀይማኖት ተረት እና ተስፋ ሳይሆን እግዚአብሔር እነዚህ ሁሉ እንደሚያስፈልጋችሁ ያውቃል ይላል። #የሚገርም #ነው #እግዚአብሔር #አይ #ምግብ #ምን #ያደርግላቸዋል #አይልም #እንደሚያስፈልግህ #ያውቃል። ስለዚህ እግዚአብሔር ምን እንደሚያስፈልገኝ ያውቃል አልጨነቅም ብለህ በጌታ ላይ የምትደገፈው። ““ስለዚህ እላችኋለሁ፣ #ስለ #ኑሮአችሁ ምን እንበላለን? ምን እንጠጣለን? ምንስ እንለብሳለን? በማለት #አትጨነቁ። ማቴዎስ 6፥25 (አዲሱ መ.ት)
ስለዚህ እግዚአብሔር ስላንተ ያስባል የሚያስጨንቅህን በእርሱ ላይ ጣል እንዴት እኖራለው አትበል። ጻድቅ በእምነት በህይወት ይኖራል።
ስለዚህ መንፈሳዊነት ማለት አጥተህ መራብ፣ መራቆት እና መጠማት አይደለም ይህ ምንኩስና/ጉስቁልና እንጂ መንፈሳዊነት አይደለም።
#እግዚአብሔር #ስላንተ #ኑሮ #ይህ #ሁሉ #እንደሚያስፈልግህ #ያውቃል። እዚ እውቀቱ ላይ አርፈህ ተደገፍ።
ጌታ አሳምሮ ያኖራል
መዝሙር 55:22፤ #ትካዜህን #በእግዚአብሔር #ላይ #ጣል፥ #እርሱም #ይደግፍሃል፤ #ለጻድቁም #ለዘላለም #ሁከትን #አይሰጠውም።
@whoweareinchrist