Get Mystery Box with random crypto!

እግዚአብሔር_ጽድቅ ክፍል=ሁለት #በእምነት_የሚገኝ_ጽድቅ | የእግዚአብሔር ጸጋ ወንጌል\ The Gospel of the grace of God\


እግዚአብሔር_ጽድቅ


ክፍል=ሁለት

#በእምነት_የሚገኝ_ጽድቅ


ሮሜ 3 (አዲሱ መ.ት)
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
²¹ አሁን ግን ሕግና ነቢያት የመሰከሩለት፣ ከሕግ ውጭ የሆነ፣ የእግዚአብሔር ጽድቅ ተገልጦአል።
²² ይህ የእግዚአብሔር ጽድቅ ኢየሱስ ክርስቶስን በማመን የሚገኝ ጽድቅ ነው።

በብሉይ ኪዳን ዘመን ይገለጣል የተባለው የእግዚአብሔር ጽድቅ በአሁኑ ሰአት ከሕግ ውጭ በሆነ መልኩ ተገልጧል። ይህ የእግዚአብሔር ጽድቅ የተገለጠው በሙሴ ሕግ ሳይሆን በኢየሱስ ክርስቶስ በማመን የሚገኝ ጽድቅ ነው።

በክርስቶስ ኢየሱስ በማመን የሚገኘው የእግዚአብሔር ጽድቅ ለመቀበል እምነት ብቻ በቂ ነው።

በክርስቶስ ኢየሱስ በማመን የሚገኘው የእግዚአብሔር ጽድቅ በስራ እና በጥረት የሚገኝ ሳይሆን በእምነት የምትቀበለው ስጦታ ነው።

ጽድቅ የእግዚአብሔር ማንነት ስለሆነ፤ በእግዚአብሔር ዘንድ የነበረው ጽድቅ ወደ ሰዎች የመጣው በክርስቶስ ኢየሱስ በኩል ነው።

በክርስቶስ ኢየሱስ በማመን የሚገኘው ጽድቅ ሰዎች መቀበል የምችሉት በእምነት ብቻ ነው።

“ሰው በኢየሱስ ክርስቶስ በማመን እንጂ፣ ሕግን በመጠበቅ እንደማይጸድቅ እናውቃለን። ስለዚህ ሕግን በመጠበቅ ሳይሆን፣ በክርስቶስ በማመን እንጸድቅ ዘንድ እኛም ደግሞ በክርስቶስ ኢየሱስ አምነናል፤ ሕግን በመጠበቅ ማንም አይጸድቅምና።”
— ገላትያ 2፥16 (አዲሱ መ.ት)

“እንግዲህ ምን እንላለን? ጽድቅን ያልተከተሉት አሕዛብ ጽድቅን አገኙ፥ እርሱ ግን ከእምነት የሆነ ጽድቅ ነው፤”
— ሮሜ 9፥30

“ማንም ሰው ሕግን በመፈጸም ሳይሆን፣ በእምነት እንደሚጸድቅ እናረጋግጣለን።”
— ሮሜ 3፥28 (አዲሱ መ.ት)

የእግዚአብሔር ጽድቅ የተገለጠው በሙሴ ሕግ ላይ የተመሠረተ ሳይሆን በክርስቶስ ኢየሱስ በማመን የተገለጠ ጽድቅ ነው። ሙሴ እና ነቢያት የመሰከሩለት የእግዚአብሔር ጽድቅ ከሕግ ውጭ ሲሆን ይህ የእግዚአብሔር ጽድቅ የተገለጠው በክርስቶስ ኢየሱስ በማመን ያገኘነው ጽድቅ በእምነት ተቀብለናል።

ይቀጥላል
የእግዚአብሔር ሰው ኤፍሬም ገ/ኢየሱስ
Join and follow
https://t.me/+LUMYTeZz9lk2MzM8