Get Mystery Box with random crypto!

እራስን አታሎ ማሸነፍ በውሸት ልክፍት መለከፍ አታላይ ነኝ ባልዋልኩበት ቦታ እራሴን የማ | pökä arts ™

እራስን አታሎ ማሸነፍ
በውሸት ልክፍት መለከፍ


አታላይ ነኝ
ባልዋልኩበት ቦታ እራሴን የማገኝ
ቂላቂል ነገርን ሃሳብን ማመነጭ
በባዶ ሜዳ ላይ በባዶ ምፈነጭ
አታላይ ነኝ

ድብን ያልኩ ቂላቂል
በጭላንጭል አለም ምፈካ በወኪል
ድብን ያልኩ ውሸታም
የነገሮች ደሃ የሃሳቦች ሀብታም
አታላይ ነኝ

አታለልሁት ደጋግሜ
ተታለልኩኝ ደጋግሜ
ህልሜ ምርኩዝ ሆኖ
የውሸት ሃሳብን ቀምሜ

ህህህህህህ
አኔነቴን አታለልኩት
ፈጣጥሬ አሸነፍኩት
ትወድሃለች እያልኩት

#ትወደኛለች

ዮኒ
ኣታን @yonatoz

ንባብ ፡ ፀባዖት ሶልአኪያ