Get Mystery Box with random crypto!

pökä arts ™

የቴሌግራም ቻናል አርማ pokartstseba — pökä arts ™ P
የቴሌግራም ቻናል አርማ pokartstseba — pökä arts ™
የሰርጥ አድራሻ: @pokartstseba
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 714
የሰርጥ መግለጫ

pökä art of drawings and graphic designs -
And Poetry vocal reading
for any comments contact @tsebaot_melodical_habesha
@pokArtsTseba @pokArtsTseba

Ratings & Reviews

2.33

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

0

3 stars

0

2 stars

0

1 stars

2


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች

2022-07-25 19:07:37 ሀዘን አዥጎድጉዶ
መቃብር ጎድጉዶ
ስሜ እስከሚከዳኝ
ሞት እስኪከነዳኝ

ሰው እንደናፈቀኝ
ስለፍቅሯ ስቀኝ
ናፍቆት እንደያዘኝ
ቃሏ እንደመረዘኝ

መሄድ እንደፈለኩ
መቅረት እንዳማረኝ
መዳን እንደተመኘው
ሞት እንደቀጠረኝ

አይታኝ ልትሰስት
በሳጥኔ ቅስት
በፍትሃቴ ማግስት

ጥቁር ለብሳ ትቁም
እሷ ብቻ ትመጣ
ወድሃለው ትበል
አንዴ ካፉ ይውጣ

መቃባር ፈንቅዬ
ታአምር ሰራለሁ
በለቅሶዬ ድንኳን
ሰርግ እደግሳለሁ

አዲብ
( @Tufaw_muhe )

ንባብ ፡ ፀባዖት ሶልአኪያ
98 views🅢🅞🅛 🅺🅸 Tsebaot, edited  16:07
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-25 19:06:38 እራስን አታሎ ማሸነፍ
በውሸት ልክፍት መለከፍ


አታላይ ነኝ
ባልዋልኩበት ቦታ እራሴን የማገኝ
ቂላቂል ነገርን ሃሳብን ማመነጭ
በባዶ ሜዳ ላይ በባዶ ምፈነጭ
አታላይ ነኝ

ድብን ያልኩ ቂላቂል
በጭላንጭል አለም ምፈካ በወኪል
ድብን ያልኩ ውሸታም
የነገሮች ደሃ የሃሳቦች ሀብታም
አታላይ ነኝ

አታለልሁት ደጋግሜ
ተታለልኩኝ ደጋግሜ
ህልሜ ምርኩዝ ሆኖ
የውሸት ሃሳብን ቀምሜ

ህህህህህህ
አኔነቴን አታለልኩት
ፈጣጥሬ አሸነፍኩት
ትወድሃለች እያልኩት

#ትወደኛለች

ዮኒ
ኣታን @yonatoz

ንባብ ፡ ፀባዖት ሶልአኪያ
66 views🅢🅞🅛 🅺🅸 Tsebaot, edited  16:06
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-25 19:00:17 ....መናፈቅ
(ሚካኤል.አ)
በማደግ ተራቀቅን...
ልባችን ተዋጠ በፍራንካ ተመን
ማወቅ ክፉ ሆኖ ለሀሳብ ሞሸረን
ይኸው ባክነን ቀረን !
ግብ ግብ ከህይወት
ዘወትር ሩጫ...
በዚህ መሀል ሳትን የትናንቱን ብልጫ።
ጎዳናው ተሞልቷል በወጣት ባ'ዛውንት
እድሜ ባደረሰው ...
ከልቡ የሚስቅ ብቻ ነው 'ማላየው !
ፈገግታው የውሸት ከአፍ የሚቀዳ
ሀዘኑ የእውነት ነፍስን የሚጎዳ።
ይሄ ነው የሞላው በዚህ እድሜ ዘመን
ታድያ ትናንትና እንደምን ይተመን?
ያ ሳቅ በመጣልኝ
የክረምቱ ሞገስ ደጄ በዋለልኝ.. .
ወጥቼ ባቦካሁ የመንደሬን ጭቃ
ፍሬ በደረደርኩ ለአዝናኝ እቃቃ
ዘልዬ ደስ ባለኝ በገመድ ቡረቃ።
ያ ሳቅ በመጣልኝ.. .
በውድ አልባሳቶች በሚያምር ቁመና
በሀብትና ዝና...
መሀል ተጋርጄ ካልደላኝ መኖሬ
ምናለ ልጅ በሆንኩ ከትናንት በርሬ
አልጣመኝም ዛሬ !

።።።።።።።።።።

ንባብ ፡ ፀባዖት ሶልአኪያ
67 views🅢🅞🅛 🅺🅸 Tsebaot, edited  16:00
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-24 15:55:50 ጦቢያ ግጥምን በጃዝ:
ምን አይነት ዘመን ላይ ደረስን ወገን !

ኢትዮጵያ ምድራዊ ገሀነም (hell pro version) የሆነችበት ዘመን የሠው ልጅ እንደ እባብ ያውም ተጨፍጭፎ ተቀጥቅጦ ተወግሮ ተቃጥሎ ተቆራርጦ ተቦጫጭቆ በጎሳ (ብሔር) ብቻ እየተለየ የሚታረድበት የሠይጣን አመት

ህገመንግስት እንጂ ህግ የሌለበት
መሪ ከነጀሌዎቹ እቃቃ በነፍስ ላይ የሚጫወትበት

ሀገር ስሟ እንጂ ክብሯ እና ልዕልናዋ ሀያልነቷ የከሰመበት

ችግኝ ዛፍ እና ቅጠላ ቅጠል ተከብረው የሠው ልጅ ነፍስ ከጥፍር ቆሻሻ የማይቆጠርበት

እናቱ ስትሰደብ የሚያንገበግበው የሌላው እናት ግን በጦርነት በርሀብ በበሽታ በዘረኝነት ጭፍጨፋ ነፍሷ ሲቀጠፍ ደንታ የማይሰጠው

እንዲህ አይነት የሰይጣን ባለሟሎች ያሉበት ጊዜ ላይ ነን ።

የምናገረው ስለ አንድ ማህበረሰብ ወይም ክልልና ከተማ ወይም ብሔር እና ነገድ አይደለም

የምጮኸው ሠው ተብሎ ስለተፈጠረው
የአዳም የልጅ ልጆች ነው ።

ጎሳ ነገድ ብሔር ክልል ሀገር (ኢትዮጵያ)
ይሔንን ሁሉ ለማለት ሰው መሆን ይቀድማል

ስለእግዚአብሔር ብላችሁ ስለ ሰው ልጅ ክብር ይኑረን

ድምፃችን እኩል ይሰማ

ዛሬ የሚጨፈጨፈው ወገንህ ሲያልቅ ነገ ወዳንተ እንደሚመጣ አትርሳ እያንዳንድህ ።

ኡኡታህን አቅልጠው እንደ ራሔል እንባህን ወደሰማይ እርጨው

ከዚያ የረጨኸው እንባ የሰማዩን ዙፋን አነቃንቆ የወረረንን ደም የተጠማና የማይጠግብ የሰይጣን መንፈስ ይዞት ይጠፋል ።

#በቃ
#የዜግነት_ክብር
#ቀይ_አሻራ

በአራቱም አቅጣጫ የሰዉ ነፍስ መጥፋት ይቁም
የተጎጂ ወገኖችን ድምፅን መስማት ያማል!!

#Ni_Gahaa!
#Kabaja_lammummaa
#በቃ
#የዜግነትክብር
#ይኣኽለና
#ናይ_ዜግነት_ኽብሪ
#Stopkillingcivilians
203 views🅢🅞🅛 🅺🅸 Tsebaot, 12:55
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-04-22 14:56:41 #አባቴ ያ’ውና

#ይታይሀል_ጀርባው

እንደ አክርማ ስንጥቅ - የተከፋፈለ
እንደ ባድማ መሬት - ላዩ የቆሰለ

ጠኔ እንደመታው - አጥንቱ ገጠጠ
የገላው ቆዳ ተራግፎ - ዕዡ ፈጠጠ

የተተለተለ የስጋ - ርጋፊ
ይታይሀል ፊቱ - ያረፈበት ጥፊ
፡’
የቆመበት ስፍራ - በደሙ ጨቅይቶ
በልብሱ ዕጣ ላይ - ቁማራቸው ደርቶ

የስድቡ ብዛት - ወርደትና ንቀት
እኔን ለመፈለግ - ያደረገው ትጋት
ፍቅሩን ነው ’ሚተርክ - የጀርባው ግርፋት
ሁሉን የሚችለው - ያ’ውል የ'ኔ አባታ

በቃሉ ያጽናት - ምድርም ስትርቀው
በመውደቅ መነሳት - ውርደት ስትንቀው

#አባቴ ያ’ውና
ፍቅሩ እየበረታ - ምህረቱን ያጸና

መከራዬን ታግሎ - በመስቀል ላይ ሊሞት
ሆሳህና ብዬ - ትናንት የሸኘሁት
ቀራኒዮ ሳልደርስ - ከረቅት ያየሁት

መከራውን ስገጥም
ውርደቱንም ሳዜም

ጭንቀቱን ስተርክ
ጩኽቱንም ስሰብክ
ልቤ ሳይንበረከክ

ስለፍቅሩ ምለሽ
ከዓለም ጋራ ስሸሽ

በውርደቱ ካባ - እኔ ከበርኩበት
ስራውን ስናገር - ዝና አተረፍኩበት
በመስቀሉ መንገድ - ለዓለም ገነንኩበት

ፍቅር ባዘለ ልብ - በዛለ ትከሻው
የሞቱ ፍጻሜ - እኔ ፡ ነኝ መድረሻው


ፀባዖት
5.1K views🅢🅞🅛 🅺🅸 Tsebaot, edited  11:56
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-04-21 16:29:37 ምን እየሆንኩ ልጠብቅሽ?
ኤልያስ ሽታኹን
~ ~ ~ ~ ~
ቅድ ሰማይ እየሰፋሁ
ራስ ዳሽን እየገፋሁ
ወይስ
እየሰራሁ የኖኅ መርከብ
ሳፈላልግ የሰው ኮከብ..
ምን እየሆንኩ ልጠብቅሽ?

እየዘመርኩ?
እየዘፈንኩ?
እያረመምኩ?
ግራ ገባኝ እኮ
ያልለየት ድል ነው ያልለየት ምርኮ።

ምን ስሆን ልጠብቅሽ?
አባይን ስጠልቀው
ኤርታሌን ስሞቀው
ቆዳዬን እንደጨርቅ ችሎ ቢተኩሰው
ተዋነይ ጋር ልሂድ ዕፁን እንዲምሰው።

ማን ጋር ልጠብቅሽ?
ከጌታዬ ግራ ከጌታዬ ቀኙ
በየት ትመጫለሽ ወይ አፍቃሪ ሞኙ።
ካብርሃም ቤት አጋር
ወይስ
ባቢሎን ግንብ ጋር።

የት ጋር ትመጫለሽ?

በዘመን የት ዘመን?
በቦታ የት ቦታ?

ከንጉሥ የት ንጉሥ?
ከባህር ምን ባህር?

ከጫካ የት ጫካ?
ከደብር የት ደብር?
:
ከሶላት ምን ሰዓት?

ምን እያረግኩኝ ልጠብቅሽ?
ከመላእክት ጋር ስገለፍጥ
የዛፍ ቆዳ ስልጥ...

ግዙፍ ሆኜ ወይ ረቂቅ
ንፋስ ሆኜ ወይስ ደቂቅ....

ወንዝ ሆኜ ወይስ አምባ
ደስታ ሆኜ ወይስ ዕምባ...

ፀሀይ ግርጌ ወይ ጨረቃ
ግጥም ሆኜ ወይ ሙዚቃ...

ምን እየሆንኩ ልጠብቅሽ?


ገጣሚ ኤልያስ ሽታሁን
ንባብ ፀባዖት ሶልአኪያ
232 views🅢🅞🅛 🅺🅸 Tsebaot, 13:29
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-04-21 16:29:37 .....ህማማት
.....
አባ አይኮንኑኝ
የጦም በመብላቴ
እንቁላል በልቼ
ብትቆይ ህይወቴ
ሌሎቹን ሳያዩ
እኔን አይገዝቱ
ሰው እየቦጨቁ
በለተ ህማማቱ
ምን ነው ግን አባቴ
በኔ ላይ በረቱ???
ቀለል አርገው አይተው
አባቴ ይፍቱኛ
የጣለችው ዶሮ
ነበረች ጦመኛ
በህይወት ዘመኗ
ስትጭር ስትለቃቅም
ከጥሬ በስተቀር
አንዳች በልታ አታውቅም

ፀባዖት ሶልአኪያ
184 views🅢🅞🅛 🅺🅸 Tsebaot, 13:29
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-04-06 10:06:47
የሞት ጥቁር ወተት

ተስፋሁን ከበደ (ፍራሽ አዳሽ)
ፀባዖት
374 views🅢🅞🅛 🅺🅸 Tsebaot, edited  07:06
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-04-06 10:05:00 የሞት ጥቁር ወተት ~ [ የግጥም መድበል ]

ተስፋኹን ከበደ ( ፍራሽ አዳሽ )

"ሰው አምላክ ቢኾንስ? በሐሳብ መቅደሱ
ፈጣሪስ ሠው ቢኾን? ሥጋን በመልበሱ
ድንቅ ነው! ረቂቅ ፤ ካ'ምላክ መወዳደር
ከምድር ላይ ቆሞ ፣ ሰማይ ላይ መንደርደር::
ከጥቁር ሰማይ ሥር . . .
በቃል ኀይለ-ብእር ፣ ብርሃንን መልበስ
በሕያው ነፍስ ላይ . . .
የሞት ጥቁር ወተት ፣ ለዘላለም መቅምስ::"

ተስፋኹን ከበደ
( ፍራሽ አዳሽ )
2013 ዓ.ም



ይፋዊ ገፆቻችን
@tobiyagitmnbejaz_yetibebmead
@tobiyamisrakterefe
@misrakterefetobiya
367 views🅢🅞🅛 🅺🅸 Tsebaot, 07:05
ክፈት / አስተያየት ይስጡ