Get Mystery Box with random crypto!

....መናፈቅ (ሚካኤል.አ) በማደግ ተራቀቅን... ልባችን ተዋጠ በፍራንካ ተመን ማወቅ ክፉ ሆኖ | pökä arts ™

....መናፈቅ
(ሚካኤል.አ)
በማደግ ተራቀቅን...
ልባችን ተዋጠ በፍራንካ ተመን
ማወቅ ክፉ ሆኖ ለሀሳብ ሞሸረን
ይኸው ባክነን ቀረን !
ግብ ግብ ከህይወት
ዘወትር ሩጫ...
በዚህ መሀል ሳትን የትናንቱን ብልጫ።
ጎዳናው ተሞልቷል በወጣት ባ'ዛውንት
እድሜ ባደረሰው ...
ከልቡ የሚስቅ ብቻ ነው 'ማላየው !
ፈገግታው የውሸት ከአፍ የሚቀዳ
ሀዘኑ የእውነት ነፍስን የሚጎዳ።
ይሄ ነው የሞላው በዚህ እድሜ ዘመን
ታድያ ትናንትና እንደምን ይተመን?
ያ ሳቅ በመጣልኝ
የክረምቱ ሞገስ ደጄ በዋለልኝ.. .
ወጥቼ ባቦካሁ የመንደሬን ጭቃ
ፍሬ በደረደርኩ ለአዝናኝ እቃቃ
ዘልዬ ደስ ባለኝ በገመድ ቡረቃ።
ያ ሳቅ በመጣልኝ.. .
በውድ አልባሳቶች በሚያምር ቁመና
በሀብትና ዝና...
መሀል ተጋርጄ ካልደላኝ መኖሬ
ምናለ ልጅ በሆንኩ ከትናንት በርሬ
አልጣመኝም ዛሬ !

።።።።።።።።።።

ንባብ ፡ ፀባዖት ሶልአኪያ