Get Mystery Box with random crypto!

ጦቢያ ግጥምን በጃዝ: ምን አይነት ዘመን ላይ ደረስን ወገን ! ኢትዮጵያ ምድራዊ ገሀነም (hell | pökä arts ™

ጦቢያ ግጥምን በጃዝ:
ምን አይነት ዘመን ላይ ደረስን ወገን !

ኢትዮጵያ ምድራዊ ገሀነም (hell pro version) የሆነችበት ዘመን የሠው ልጅ እንደ እባብ ያውም ተጨፍጭፎ ተቀጥቅጦ ተወግሮ ተቃጥሎ ተቆራርጦ ተቦጫጭቆ በጎሳ (ብሔር) ብቻ እየተለየ የሚታረድበት የሠይጣን አመት

ህገመንግስት እንጂ ህግ የሌለበት
መሪ ከነጀሌዎቹ እቃቃ በነፍስ ላይ የሚጫወትበት

ሀገር ስሟ እንጂ ክብሯ እና ልዕልናዋ ሀያልነቷ የከሰመበት

ችግኝ ዛፍ እና ቅጠላ ቅጠል ተከብረው የሠው ልጅ ነፍስ ከጥፍር ቆሻሻ የማይቆጠርበት

እናቱ ስትሰደብ የሚያንገበግበው የሌላው እናት ግን በጦርነት በርሀብ በበሽታ በዘረኝነት ጭፍጨፋ ነፍሷ ሲቀጠፍ ደንታ የማይሰጠው

እንዲህ አይነት የሰይጣን ባለሟሎች ያሉበት ጊዜ ላይ ነን ።

የምናገረው ስለ አንድ ማህበረሰብ ወይም ክልልና ከተማ ወይም ብሔር እና ነገድ አይደለም

የምጮኸው ሠው ተብሎ ስለተፈጠረው
የአዳም የልጅ ልጆች ነው ።

ጎሳ ነገድ ብሔር ክልል ሀገር (ኢትዮጵያ)
ይሔንን ሁሉ ለማለት ሰው መሆን ይቀድማል

ስለእግዚአብሔር ብላችሁ ስለ ሰው ልጅ ክብር ይኑረን

ድምፃችን እኩል ይሰማ

ዛሬ የሚጨፈጨፈው ወገንህ ሲያልቅ ነገ ወዳንተ እንደሚመጣ አትርሳ እያንዳንድህ ።

ኡኡታህን አቅልጠው እንደ ራሔል እንባህን ወደሰማይ እርጨው

ከዚያ የረጨኸው እንባ የሰማዩን ዙፋን አነቃንቆ የወረረንን ደም የተጠማና የማይጠግብ የሰይጣን መንፈስ ይዞት ይጠፋል ።

#በቃ
#የዜግነት_ክብር
#ቀይ_አሻራ

በአራቱም አቅጣጫ የሰዉ ነፍስ መጥፋት ይቁም
የተጎጂ ወገኖችን ድምፅን መስማት ያማል!!

#Ni_Gahaa!
#Kabaja_lammummaa
#በቃ
#የዜግነትክብር
#ይኣኽለና
#ናይ_ዜግነት_ኽብሪ
#Stopkillingcivilians