Get Mystery Box with random crypto!

#አባቴ ያ’ውና ፡ #ይታይሀል_ጀርባው ፡ እንደ አክርማ ስንጥቅ - የተከፋፈለ እንደ ባድ | pökä arts ™

#አባቴ ያ’ውና

#ይታይሀል_ጀርባው

እንደ አክርማ ስንጥቅ - የተከፋፈለ
እንደ ባድማ መሬት - ላዩ የቆሰለ

ጠኔ እንደመታው - አጥንቱ ገጠጠ
የገላው ቆዳ ተራግፎ - ዕዡ ፈጠጠ

የተተለተለ የስጋ - ርጋፊ
ይታይሀል ፊቱ - ያረፈበት ጥፊ
፡’
የቆመበት ስፍራ - በደሙ ጨቅይቶ
በልብሱ ዕጣ ላይ - ቁማራቸው ደርቶ

የስድቡ ብዛት - ወርደትና ንቀት
እኔን ለመፈለግ - ያደረገው ትጋት
ፍቅሩን ነው ’ሚተርክ - የጀርባው ግርፋት
ሁሉን የሚችለው - ያ’ውል የ'ኔ አባታ

በቃሉ ያጽናት - ምድርም ስትርቀው
በመውደቅ መነሳት - ውርደት ስትንቀው

#አባቴ ያ’ውና
ፍቅሩ እየበረታ - ምህረቱን ያጸና

መከራዬን ታግሎ - በመስቀል ላይ ሊሞት
ሆሳህና ብዬ - ትናንት የሸኘሁት
ቀራኒዮ ሳልደርስ - ከረቅት ያየሁት

መከራውን ስገጥም
ውርደቱንም ሳዜም

ጭንቀቱን ስተርክ
ጩኽቱንም ስሰብክ
ልቤ ሳይንበረከክ

ስለፍቅሩ ምለሽ
ከዓለም ጋራ ስሸሽ

በውርደቱ ካባ - እኔ ከበርኩበት
ስራውን ስናገር - ዝና አተረፍኩበት
በመስቀሉ መንገድ - ለዓለም ገነንኩበት

ፍቅር ባዘለ ልብ - በዛለ ትከሻው
የሞቱ ፍጻሜ - እኔ ፡ ነኝ መድረሻው


ፀባዖት