Get Mystery Box with random crypto!

ሀዘን አዥጎድጉዶ መቃብር ጎድጉዶ ስሜ እስከሚከዳኝ ሞት እስኪከነዳኝ ሰው እንደናፈቀኝ ስለፍ | pökä arts ™

ሀዘን አዥጎድጉዶ
መቃብር ጎድጉዶ
ስሜ እስከሚከዳኝ
ሞት እስኪከነዳኝ

ሰው እንደናፈቀኝ
ስለፍቅሯ ስቀኝ
ናፍቆት እንደያዘኝ
ቃሏ እንደመረዘኝ

መሄድ እንደፈለኩ
መቅረት እንዳማረኝ
መዳን እንደተመኘው
ሞት እንደቀጠረኝ

አይታኝ ልትሰስት
በሳጥኔ ቅስት
በፍትሃቴ ማግስት

ጥቁር ለብሳ ትቁም
እሷ ብቻ ትመጣ
ወድሃለው ትበል
አንዴ ካፉ ይውጣ

መቃባር ፈንቅዬ
ታአምር ሰራለሁ
በለቅሶዬ ድንኳን
ሰርግ እደግሳለሁ

አዲብ
( @Tufaw_muhe )

ንባብ ፡ ፀባዖት ሶልአኪያ