2022-01-24 22:49:27
ስለ እውነት ብቻ እኖራለሁና እንዲህ ብዬ እመሰክራለው።
"የኢየሱስ ደም ብቻ አስታራቂ ነው"!
በብሉይ ኪዳን አንድ ሰው ሐጥያት ከሰራና ከእግዚአብሔር ጋር ለመታረቅ ከወደደ የበግ ጠቦት ይዞ ወደ ካህን ዘንድ ይሄዳል።ካህኑም በጉን ስለ ሐጥያተኛው መስዋዕት አድርጎ ያቀርባል።የሐጥያት ቅጣት የሆነውን ሞት በጉ
ተቀብሏልና ሐጥያተኛው ይቅርታ ያገኛል።ዘሌ 16፡6
ይህ ምሳሌነቱ ለአዲስ ኪዳን ነው።ኢየሱስ ክርስቶስ መስቀል ላይ ሲሞት የእያንዳንዳችንን ሐጥያት ተሸክሞ
ነበር።”እግዚአብሔርም የሁላችንን በደል በእርሱ ላይ አኖረ”።ኢሳ 53፡6 አሁን ከእግዚአብሔር ጋር የምንታረቅበት ብዙ መንገድ ሳይሆን አንድ መንገድ አለ።እርሱም ከ 2000 አመት በፊት ስለእኛ የፈሰሰው የመሲሁ ደም።ከዚህ ደም ውጪ ሰውን ከእግዚአብሔር ጋር ማስታረቅ የሚችል አካል የለም።ቢኖርማ ኢየሱስ ክርስቶስ ያን ሁሉ መከራ መቀበል ባላስፈለገው ነበር።በብሉይ ኪዳን ከበጉ ደም ውጪ ዕርቅ እንደሌለ በአዲስ ኪዳንም ከጌታ ደም ውጪ ከእግዚአብሔር ጋር መታረቅ አይቻልም።ደምም ሳይፈስ ስርየት የለም።ዕብ 9:22
ኢየሱስ ክርስቶስ በደሙ ከራሱ፣ከአባቱና ከመንፈስ ቅዱስ ጋር አስታርቆናል ብለን ካመንን አሁንም በደሙ
ያስታርቀናል ብለን ለማመን ልንቸገር አይገባም።ደሙ ለዘላለም ህያው ስለሆነ ሰዎችን ከእግዚአብሔር ጋር
የማስታረቅ አቅም አለው። ዛሬም ደክመን ሐጥያትን ብናደርግ ወደ እግዚአብሔር መግቢያችንና አስታራቂያችን ደሙ ነው። "እግዚአብሔር በእምነት የሚገኝ በደሙም የሆነ ማስተስሪያ አድርጎ አቆመው" ሮሜ 3፡25 ቅዱስ ጳውሎስ የሚለን ደሙ ማስተስሪያ ነው።ደሙ የሚገኘው ደግሞ በዕምነት ነው።ሐጢአተኛ ስለሱ በፈሰሰው ደም አምኖ ሲጸልይ ከእግዚአብሔር ጋር ይታረቃል።እግዚብሔር የሐጥያት ማስተስሪያ አድርጎ ደሙን ካቆመው እኛ ለምን
የራሳችንን ማስተስሪያ መንገድ ለማቆም እንፈልጋለን ?እግዚአብሔር ይቅር የሚለን ስለፈሰሰው ስለ ልጁ ደም
ሲል ብቻ ነው።
የመሲሑ ደም ዛሬም ላመኑት ማራቸው እያለ ይጮሃል።
751 views19:49