Get Mystery Box with random crypto!

የተንዚህ መከታ ተጨባጭ መረጃ መሰረታዊ ግንዛቤ እና እውነታ፣ ክፍል 5 | የ ኡስታዝ ሀቢብ ኑሩ የድምፅ ፋይሎች

የተንዚህ መከታ ተጨባጭ መረጃ
መሰረታዊ ግንዛቤ እና እውነታ፣
ክፍል 5
==========

የነብያችንን ቀብር በ ፍንዳታ ሙከራ ሥለ ማድረጋ ቸው አልተሳካላቸውም እንጀ!! ።
ቀብሩን በቦምብ የመቱበትም ምክንያት ጣኦት ነው ብለው ነበር።
አላህ ከሸራቸው ይጠብቀንና።
ቂም ቀ·4
የኢስላም ከሊፋት ለመንኮታከት እጅግ ጥቂት በቀረው ግዜ ላይ
የመካ ሙፍቲ የነበሩት ታዋቂው አሊም ሙፍቲ አህመድ ዘይኒ
ደህላን "ፊትነቱል ወሀብያ " በሚለው መፀሃፋቸው ገፅ 77 ላይ
እንዲህ ገልፀዋል
"ወሀብያዎች ከአዛን በሁዋላ ጮክ ብሎ ሰይዳችን ላይ ሰለዋት
ማውረድን ቢድአ ነው ብለው አጥብቀው ከልክለው ነበር። አንድ እውር የነበረ
ለሰለዋት ፍቅር የነበረው ሷሊህ
ሙአዚን ግን ይህን የወሀብያ ህግጋት ከቁብ ሳይቆጥረው ወሀብያዎች
እየሰሙት አዛን
አድርጎ ከጨረሰ በሁዋላ ፣ በጀግንነት ሰይዳችን ላይ ጮክ ብሎ
ሰለዋት አወረደ።
# በዚህ_ግዜ_ወደ_መሐመድ_አብዱልወሀብ_አመጡት
# _እሱም_ሙአዚኑን_እንዲያርዱት_ተከታየቹን_አዞ_አሳረደው ።
እንግዲህ መ/አብዱልወሀብ ከእውሩ ሙአዚን ጋር የቆየ ቂም አልነበረውም!
እንደው ሙአዚኑ የታረደው ነብያችን ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም ላይ ሰለዋት
ስላወረደ ብቻ ነበር ። ይህ ማለት መ/አብዱል ወሀብ ነብያችን ሰለላሁ አለይሂ
ወሰለም ጥላቻ ስለነበረበት ነው እነጂ ሚስኪኑን ሙአዚኑን በማስጠንቀቅያ
ብቻ ማለፍ በቻለ ነበር!
ንቀት ቁ·5
የወሀብያው መሪ ኢብኑ ባዝ እንዲህ ብሎ ፈትዋ ሰጥቶ ነበር።
ነብያችን ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም ዋህይ የወረደበትን ሂራ ዋሻን ለመጎብኘት
ከተራራው የወጣ ሰው ከአላህ ሌላ እያመለከ ስለሆነ ሙሽሪክ ነው ብሎ
ፈትዋ ሰጥቷል።
እንደው ሂራ ዋሻ መሄድ ሙሽሪክ ቢያደርግ ኖሮ መቸ ሰይድ ጂብሪል እዛ ዋሻ
መጥቶ ነብያችን ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም ላይ ቁርአንን ያወርደላቸው ነበር?

ጥላቻ ቁ·6
ሰለፊ ተብየዎች ነብያችን ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም ሚያወድስ ነገር ሲነሳ
አላርጂካቸው አብሮ ይነሳል። ለዚህም ዋና ማሳያው መንዙማ ነው! ።
ባለፈው በለጠፍኩት ፅሁፍ ላይ በሰፊው ስለ መንዙማ አትቼ ነበር።
ወሀብያዋች መሐመድ አወልን ሙሽሪክ ያሉበት ምክንያት ነብያችን ሰለላሁ
አለይሂ ወሰለም ስለሚጠሉ መሆኑን በሰፊው ዘግቤ ነበር።
"አህያውን ፈርቶ ዳውላውን" የሚለውን ተረት በማስደገፍ ጭምር አስረድቼ
ነበር።
ምክንያቱም ቀጥታ ነብያችን ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም ማጥቃት ፈርተው
ሙሪዳቸውን ሚያጠቁበት ምክንያት ለሰይሳችን ካላቸው ጥላቫ መሆኑነም
ዘግቤ ነበር።
ጥላቻ ቀ·7
ነጅዲዮች ሰይዳችን ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም እንደሚጠሉ ሌላው ማስረጃ
ደግሞ አንድም የሳቸው አሳር ወይም ንብረት ሳውዲውስጥ አለመኖሩ ነው።
ጥምጣማቸው፣ ጋሻቸው፣ ልብሳቸው፣ ጫማቸው፣ቀለበታቸው ፣ለነገስታት
የላኩት ደብዳቤዋቻቸው፣ከዘራቸው፣ኩታቸው፣የውዱእ እቃቸው፣ አንድም ነገር
ሳውዲ ውስጥ ማግኘት አይቻልም።
እንግዲህ ራስህን አንድ ጥያቄ እዚህ ጋር ጠይቅ!! ነብያችን ሰለላሁ አለይሂ
ወሰለም ሳውዲ ውሰጥ ተልከው ሳለ ለምንድነው አንድም ንብረታቸው እዛ
ያልተገኘው?
መልሱ እጅግ ቀላል ነው!!
ወሀብያዎች ከነጅድ ተነስተው በ1924 ላይ ሳውዲን ሲቆጣጠሩ 90%
የሚጠጋውን የነብያችን ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም ቅርሶች ጣኦት ነው ብለው
አቃጥለው አጥፍተውታል!!!
የቀረው ንብረታቸው በሙስሊሞች ርብርብ ከሳውዲ ወጥቶ ቱርክ፣
ግብፅ፣ሲርያ እና ሌሎች ሀገሮች ላይ ተበትኖ ይገኛል!
ከዚህ በሁዋላ ፣ ከወሀብያ ጋር ያለው ፀባችን በመውሊድ ብቻ እንዳልሆነ
እንደተገነዘብክ ተስፋ አለኝ!
ባለቤቱን ካልናቁ አጥሩን አይነቅንቁ ነውና ነገሩ ፣ወሀብያ መውሊድን መቃወሟ የነብያችን ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም ጥላቻ ስላለባት መሆኗን ግልፅ
እንደሆነልህ እገምታላው።
ጥላቻ ባይኖርማ ታድያ ከነብያችን ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም 11 ሰይፎች
መካከል ቢያንስ አንዱ እንኳን ሳውዲ ውስጥ ታገኘው ነበርና ነው መልካም መውሊድ!

••••••••••••••••••••••••••••••••••••
ዒልሙዲን ኢስላማዊ ስቱድዮ
ክፍል 6 ይቀጥላል……
https://t.me/elmudinIslamicstudio/13760