Get Mystery Box with random crypto!

የተንዚህ መከታ ተጨባጭ መረጃ መሰረታዊ ግንዛቤ እና እውነታ፣ ክፍል 4 | የ ኡስታዝ ሀቢብ ኑሩ የድምፅ ፋይሎች

የተንዚህ መከታ ተጨባጭ መረጃ
መሰረታዊ ግንዛቤ እና እውነታ፣
ክፍል 4
=======
ታላቁ ሶሀብይ ኢብኑ አባስ ረዲየላሁ ዐንህ
إذا إشتبه عليكم شيء من القرآن فاطلوبه من الشعر فإنه ديوان العرب
አንድ ቁርአን አልገባችሁ ካለ ግጥም ውስጥ ፈልጉት… ግጥም የ አረቦች መዝገበ ቃላት ነው ይሉናል ስለዚህ ወደ ግጥም ሄደን የቁርአኑን ትርጉም እንይ
ገጣሚው
قد استوى بشر على العراق
من غير سيف و دم مهراق
ቢሽር ኢራቅን ያለ ምንም ጦርነት እና ደም መፋሰስ ተቆጣጠረ እንጂ ኢራቅ ላይ ከፍ አለ አይባልም… ስለዚህ ኢስተዋ contextual meaning /አገባባዊያዊ ትርጓሜ ነው ያለው ተቀመጠ ሆኖ ይመጣል… ተቆጣጠረ የሚል ትርጉምም አለው… የቁርአኑን ጥበብ መጨረሻ ላይ እመጣበታለሁ አሁን አንድ የ ወሀብያን ቅስም የሚሰብር መረጃ ልንገርህ… በአረብኛ ቋነቋ ህግ መሰረት በላጋ የሚባል የትምህርት ዘርፍ አለ… እዛ ውስጥ ኢንቲሳብ /ሙራአቱ ነዚር የሚል የወሬ ቀመር ቁጭ ብሎልሀል… አንድ ንግግር ነግግር ለመባል ከ ርእስ መውጣት የለበትም ስለ ትምህርት እያወራህ ስለ ቤትህ አስቤዛ ከቀላቀልክ ወሬህ እጅ እጅ ይላል ትባላለህ
ወንድሜዋ አሁን ሱረቱ ጧሀን እንየዉ
تنزيلا ممن خلق الأرض والسموات العلى ٤ الرحمن على العرش استوى ٥ له ما في السموات وما في الأرض وما بينهما وما تحت الثرى ٦
በቀጥታ ከተተረጎመ: _ቁርአን የወረደው ምድርን እና ሰማይን ከፈጠረው ጌታ ነው, ከ አርሽ በላይ ከፍ አለ/ተቀመጠ,በሰማይም ሆነ በምድር ያሉ ነገሮች ሁሉ የ እርሱ ንብረቶች ናቸው…
ጉድ በል ወንድም እውነት አላህ ስለመፍጠር እና የሁሉ ነገር ባለቤት ስለመሆኑ አየነገረን በመሀል አርሽ ላይ ተቀመጥኩ ይላል? ?? መዘባረቅ ከ ፈጣሪ ይጠበቃል ትላለህ… ትክክለኛዉ አተረጓጎም ፈጠረ_ተቆጣጠረ_የግሉ አደረገ አንጂ
ፈጠረ_ቁጭ አለ_የግሉ አደረገ አይደለም
ቁርአን ማለት በውስጡ ብዙ ጥበብ የያዘ ነው አላህ አቡ ለሀብን በ nic name ለምን የጠራው ይመስልሃል? አይዋ ተቀፅላ ስም ከ ዋና ስማችን ያነሰ ክብር ስላለው አላህ በዋና ስሙ አልጠራውም… ቁርአንን እንደ ወሀብያ በቀጥታ አትየው ሊያስተምረን የፈለገው ጉዳይ እኮ አለው… በ 6ቀን ሰማይ እና ምድርን አላህ ለምን ፈጠረ ብትል መረጋጋትን ሊያስተምረን ነው ቁርአኑ ለሁሉ ነገር አትቸኩሉ ሰከን በሉ እኔ ጌታችሁ በ አንዴ መፍጠር እየቻልኩ ለናንተ ትምህርት ነው 6ቀን ማቆየቴ እያለን ነው, አርሽን ተቆጣጥሬያለሁ ሲለንም 7ሰማይ እና 7ምድር ቢጣልበት ሜዳ ላይ የወደቀ ቀለበት የሚያሳክላቸውን ያን ትልቅ አለም የተቆጣጠርኩ ጌታ እናንተን መቆጣጠሬ አያጠራጥራችሁ ነው ጥበቡ አየህ ወንድሜዋ አለል አርሺ ኢስተዋ የ አላህ የ ፈጣሪነት ክብር መገለጫ እንጂ አርሽ ላይ የተቀመጠበት ቃሉ አይደለም… ከፈጠረው ፍጡር ከማንም አይፈልግም ከ 73 በላይ የ ኢስላም አባቶችን መጥቀስ ይቻል ነበር ሰአቱም ቦታውም አይፈቅድም…
በመጨረሻም ኢማሙ አህመድ ሙስነድ ኪታባቸው ላይ እንደዘገቡት ነብዩ ሶለሏሁ አለይሂ ወሰለም "ወደፊት ቱርክን የሚከፍታት መሪ ምርጥ መሪ ነው ወታደሮቹም ምርጥ ናቸው" ብለዋል …ሶሀበቶች ሊከፍቷት ሞከሩ አቡ አዩብ ቱርክ ድንበር ላይ ሞቱ የከፈታት ግን የ 18 አመቱ ወጣት ሙጃሂድ ሙሀመዱል ፋቲህ ነበር, በቦታው የነበረውን ቤት በከራማው በ እጁ ወደ ቂብላ ያዞረ ልጅ ነው ነብዬ የመሰከሩለት ምርጥ ወታደር እምነቱ አላህ ያለ ቦታ እና ያለ አቅጣጫ ነው ያለው የሚሉት የማቱሪዲያ እምነት ነበር… ሁሌም የሚያኮራ እምነት ነው ያለህ ወንድሜዋ ለ ሸይኽ አብዲላህ አል ሀረሪይ ትልቅ ደረጃ አላህ ይስጣቸው ሸይኽ ኡመር እና አሁን ያሉትን ምርጥ ምርጥ ተማሪዏቻቸዉን ከምቀኛ ይጠብቃቸው ወላሂ ቢገባን ትልቅ ዉለታ ነው የ ጀነት ዉለታ
ከስድስቱም ጀሃት ኻሊቃችን ጠራ
ከፊትም ከኃላም ከቀኝም
ከግራ
ጌታ የጠራ ነው ከታችም
ከላይ
ጃሂል ያንጋጥጣል መስሎት
በሰማይ
ጌታ ወርዶ ይፍረድ የሚሉት
ሲጣሉ
ጥርጥርም የለው በውነት
ይከፍራሉ
የጌታ ረህመቱ መፍሰሻው
ከላይ ነው
ለዱዓችን ማንሳት ለረህመት እንጅ ነው
ጌታ ወዴት ይሆን በማለት አትሞኝ
እንደ ነበረ ነው ፍጥረቱ
ሳይገኝ
የኛ መኖርና ሰማይና ምድሩ
ያመላክታሉ ጌታ ለመኖሩ
ጌታ የለም ማለት የለሁም
ማለት ነው
ፍጥረቱን ፈጣር ጌታችን ያለ ነው

ሸይኽ ሙሀመድ ደሴ
ስለ መውሊድ ማክበር የተክፊሮች ጭጋግ ስለጋረደኝ ፣ በዥታየን
አስወግድልኝ! ካልከኝ የሚከተለውን መረጃ ላቀብልህ።
ኢኽዋኖች መውሊድ አታክብር ብለው አስቸገሩኝ ካልከኝ, ራስህን ትከላከል
ዘንድ መሳርያ ላውስህ።

እኛ ከ ኸዋሪጆች ጋር እየተጣላን ያለነው በመውሊድ ጉዳይ ብቻ ከመሰለህ፣
እጅጉኑ ተሳስተሀል።
እኛ ከ ኢኽዋኖች ጋር ያለን ፀብ ለምን የነብያችን ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም
መውሊድ ትቃወማላቹ ሚለው ብቻ አይደለም።
ፀባችን፣ ለምን ነብዩን ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም ትጠላላቹ? የሚል ነው።
ምናልባት ይህ ጥያቄ አሁን ሊያሰቆጣህ ይችላል!! ። ነገር ግን መጣጥፉን
አንብበህ ከጨረስክ በሁዋላ እውነትም ኸዋሪጆች ነብያችንን ሰለላሁ አለይሂ
ወሰለም እንደሚጠሉ ትረዳለህ።
ነገሩ ምን መሰለህ አንተ የምትወደው ሰው ከሞተ በሁዋላ እንኳን ቅርሱን
ጠብቀህ ታቆያለህ። ያንን ቅረስም ለልጆችህ እያሳየህ የሰውየውን ጀብዱ
ለልጆችህ ትተርካለህ።
ለምሳሌ ያህል እኔ ጋር የቅድመ አያቴ ጦርና ሰይፍ ይገኛል።
ይህ ጦርና ሰይፍ አባቴ በአግባቡ ተንከባክቦ አስረክቦኛል፣ እኔም አላህ ካለ
ለልጄ አስረክባለው እንጂ , ጦርና ሰይፉ ጣኦት ነው ብየ አላቃጥለውም! ።
ነገር ግን ወሀብያዎች ነብያችንን ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም ቅርስ ለትውልድ
ለማስተላለፍ ፋንታ አብዛኛውን ጣኦት ነው ብለው አጥፍተውታል።
ይህንንም እንደሚከተለው በማስረጃ እገልፅልሀለው
ጥፋትቁ፣
1·1)ነብያችንን ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም የተወለዱበት ቦታ ወሀብያዎች መካን
በ1920 ዎቹ ሲቆጣጠሩ አፍርሰውታል።
ካፈረሰቱም በሁዋላ ያቦታ እንዲረሳ ለማድረግ በቦታው ትልቅ ላይብረሪ
አሰርተውበታል።
እንግዲህ ከከሊፋዎቻችንም አንዱም ነብያችንን ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም
የተወለዱበትን ቦታ ለማፍረስ የሞከረ አልነበረም።
ሁሉም በተረከበው ሁኔታ ነው ለትውልድ ሲያስተላልፍ የነበረው።
አረ እንዴትስ አሚናን መላአካዎች ያባሸሩባት ቦታ እንዴትስ ተደርጎ ይደፈራል??
ወከባ ቀ·2
ነብያችንን ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም ለረጅም አመታት የኖሩት ከእናታችን ኸዲጃ
ረድየላሁ አንሁ ጋር ነው።
ለ28 አመታት የኖሩትም እሷ ቤት ውስጥ ነው።
በአጭሩ ነብያችንን ሰለላሁ አለይሂ ወሰለምኸድጃን ካገቡ በሁዋላ ቤቷ
የሳቸው ንበረት ነበር።
እንግዲህ ወሀብያዎች ይህን ሰይዳችንን
ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም ለ28 አመታት የኖሩበትን ቤታቸውን አፍርሰውታል፣።
አፍርሰው ብቻ አላበቁም፣ በፈረሰው ቦታ ላይ የህዝብ ሽንት ቤት
አሰርተውበታል ።
እንግዲህ የመለስ ቀብር ላይ ሽንት ቤት ቢሰራ ምን አይነት ንቀት እንደሆነ
ይገባሀል።
ነገሩ ባለቤቱን ካልናቁ አጥሩን አይነቀንቁ ነው!
እንግዲህ ቁጠርልኝ ፣ ወሀብያ መጀመርያ ነብያችን ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም
የተወለዱበትን ቤት አፈረሰች፣ ከዛም የኖሩበትን ቤት ሽንት ቤት አደረገችው።
•••••••••••••••••••••••••••••••
ዒልሙዲን ኢስላማዊ ስቱድዮ
ክፍል 5 ይቀጥላል……
https://t.me/elmudinIslamicstudio/13759